TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሶማሌክልል : በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በኩል ሀገርን ሊዳፈር የሞከረው የአልሸባብ የሽብር ቡድን በክልሉ ልዩ ኃይል የማያዳግም ፣ ሁሌም የማይረሳው አስተማሪ ቅጣት መቀጣቱ ይታወቃል።

ባለፉት ቀናት በአፍዴር ዞን ቆህሌ ወረዳ በሁልሁል ንዑስ ቀበሌ ላይ ሰርጎ በገባው አልሸባብ ላይ በተካሄደው ጠንካራ ኦፕሬሽን ድል ያደረገው የሶማሌ ልዩ ኃይል ለሌላ ግዳጅ ደግሞ ወደ ሀገሪቱ ድንበር ተሸኝቷል።

በሌላ መረጃ ፦ የሶማሊያ ፌዴራሉ መንግስት ባልፈው ሳምንት የአልሸባብ የሽብር ቡድን ከባኮል ግዛት ከፍቶት በነበረው ጥቃት ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች የምግብ እና የመድሃኒት ድጋፎችን ልኳል። አካባቢው በድርቅም የተጎዳ ነው። ባኮል በ420 ኪ/ሜ ከሞቃዲሹ የሚርቅ ሲሆን ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጋር የሚዋሰን የሀገሪቱ ክፍል ነው።

Photo Credit : Somali Region Communication

@tikvahethiopia
#ሶማሌክልል

በሶማሌ ክልል በተከሰተው የጎርፍ አደጋ እስካሁን 28 ሰዎች ሲሞቱ ከ300,000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተጠቆመ።

በሶማሌ ክልል ከ33 ወረዳዎች በላይ ተከሰተ የተባለውን የጎርፍ አደጋ በተመለከተ ተጎጂዎችና ተፈናቃዮች በምን ሁኔታ እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው እርዳታ እያደረገ የሚገኘውን Save the Childrenን ጠይቋል።

የድርጅቱ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አብዲራዛቅ አሕመድ በጎርፉ የተጎዱት ከ600,000 በላይ ሰዎች እንደሚሆኑና ከ300 ሺሕ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንና የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸዋል።

" ምግብም፣ መድኃኒት የሚበቃ የላቸውም ችግሩ ከፍተኛ ነው። የተፈናቀሉት ሰዎች እርዳታ ይፈልጋሉ። ...ትንሽ ከፍ የሚል ቦታ  ከውሃ ትንሽ ወጣ ብለው ነው የተቀመጡት። ሰው በእግር ውሃው ውስጥ ሂዶ አህያም ያላቸው ለትራንስፖርት እየተጠቀሙ ከፍ ወዳለ ቦታ እየሄዱ ነው አሁን ከከተማው ብቻ ነው የወጡት እጂ ብዙም ከወንዙ አራቁም " ነው ያሉት።

ሴቶችና ህፃናት በምን ሁኔታ ይገኛሉ ?

አቶ አብዲራዛቅ በሰጡን ማብራሪያ፥ "እደዚህ አይነት ችግር ሲመጣ መጀመሪያ የሚጎዱት ሴቶችና ልጆች ናቸው። እስካሁን የሞቱት ጠቅላላ 28 ሰዎች ሲሆኑ ከ28ቱ ወደ ስምንት የሚሆኑት ሴቶች ናቸው" ብለዋል።

ለተፈናቃዮች የሚደረገው ድጋፍ ምን ይመስላል ?

ዳይሬክተሩ ይህንን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፥ " ያለነውን ሪሶርስ ተጠቅመን ከመንግሥትና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ሆነን የምንችለውን ድጋፍ እያረግን ነው። ግን ችግሩ በጣም ትልቅ ስለሆነ ለሁሉም ሰው መድረስ የሚያስችለን ሪሶርስ የለም። ከሁሉም አቅጣጫ የተሰበሰበ ገንዘብም ራሱ እስካሁን ሊበቃ አልቻለም " ብለዋል።

ለተፈናቀሉት ሰዎች ጥሬ ገንዘብ እየሰጠን ነው ያሉት አቶ አብዱራዛቅ፥ እደፍላጎታቸው እዲጠቀሙ 300 ሺሕ ለሚሆኑ አባውራዎች ለእያንዳንዳቸው 7 ሺሕ 700 ብር፣ ለ1 ሺሕ 200 አባውራዎች የእቃ ድጋፍ እንዳደረጉ ጠቅሰዋል።

አሁን ላይ በጣም የሚያስፈልጋቸው ምግብ እንዲሁም የሚያድሩበት ቤት እንደሆነም ጠቁመዋል።

የጎርፍ አደጋው እየጨመረነው ወይስ እየቀነሰ ?

ይህ ጥያቄ የቀረበላቸው ዳይሬክተሩ፣ "#የመቀነስ ነገር የለም፣ ዝናቡ እየዘነበ ነው በጣም የወንዙ ውሃ ከፍተኛ እየሆነ ነው። አሁን #ስጋቱ እዳለ ነው የሚቀንስም አይመስልም። ዝናቡም የወንዙ ውኃም አንድ ላይ ተጨምሮ ችግር እየሆነ ነው መንገዶች ሁሉም ተዘጋግተዋል" ሲሉ አስረድተዋል።

ድጋፉን ለማድረስ በጣም ፈተና የሆነው ጉዳይ ምንድን ነው ?

" ፈታኝ የሆነው ነገር መቀሳቀስ አልቻልንም።
ሁሉም ቦታ ውሃ ነው። ልጆቹ [ድጋፍ ሰጪዎቹ] በብዛት በጋሪ ነው የሚንቀሳቀሱት። ሕዝቡም እደዛ ነው የሚንቀሳቀሰው። ሰው የሚበላ አዞም ይኖራል፤ይፈራሉ። በመኪና መሄድ አይቻልም። ውኃው በጣም እየጨመረ ነው። በጣም አስቸጋሪ ነው አይደርስም ያልንበት ቦታ ጎርፉ እየደረሰ ነው " ሲሉ ለጥያቄው ምላሽ ሰጥተዋል።

አክለውም፥ " ብዙ ሰውም በዚህ ምክንያት እየተፈናቀለ ነው። እደዚህ አይነት ጎርፍ አይተን አናውቅም። ህዝቡ ራሱ እደዚህ አይነት ጎርፍ አላየንም የሚል ነገር ነው ያለው። በሜትሮሎጅ መረጃ መሠረት ጎርፍ እንደሚኖር ለህዝቡ መነገር ነበረበት። በሚያስፈልገው ልክ አልተሰራም መሰለኝ። ለወደፊትም ከተማው በወንዙ በኩል ሳይሆን በሌላኛዉ በከፍታው በኩል ቢያድግ ጥሩ ነው" ሲሉ አቶ አብዲራዛቅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

በመጨረሻም፣ መንግሥትና ከሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች ድጋፍ እየተደረገ ቢሆንም፣ ጉዳቱ በጣም ከባድ ስለሆነ ድጋፍ ተፈናቃዮችን መዳረስ እንዳልቻለ፣ ርብርብ በማድረግ ሕዝቡን መታደግ እንደሚገባም ጥሪ ቀርባል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሶማሌክልል

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ካለፈው ሰኞ ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በሱማሌ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰቢያ የምክክር መድረክ እያደረገ ይገኛል፡፡

ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)  ፥ ከጥቅምት 4-6/2017 ዓ.ም በክልሉ ሶስት ማዕከላት ፦
- በጅግጅጋ ፣
- በጎዴ
- በዶሎ አዶ ማዕከላት ከ 1 ሺ በላይ የማህበረሰብ ወኪሎችን በማመካከር አጀንዳዎቻቸውን እንዲለዩ ማድረግ ተችሏል ሲሉ ጠቁመዋል።

" በሶስቱም ማዕከላት በነበረው የምክክር መድረክ የማህበረሰብ ተወካዮች የነበራቸው ተሳትፎ እጅግ የሚደነቅ እንደሆነ ለማረጋገጥ ችለናል " ሲሉ አክለዋል።

ዛሬ ደግሞ የተመረጡ 100 የህብረተሰብ ወኪሎችን ጨምሮ የክልሉ አራት  የምክክር ባለድርሻ አካላት ማለትም ፦
° የፖለቲካ ፓርቲዎች፣
° የክልሉ መንግስት፣ 
° የልዩ ልዩ ማህበራትና ተቋማት
° የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ወኪሎች የሚሳተፉበት የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ መጀመሩን ገልጸዋል።

" ለተከታታይ 3 ቀናት በሚካሄደው የባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ከላይ ከተጠቀሱ አምስቱ ባለድርሻ አካላት የተመረጡ ከ1 ሺ 200 በላይ ተወካዮች የሚሳተፉ ይሆናል " ብለዋል።

" ተወካዮች በዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ ወኪሎችን ይመርጣሉ፤ ክልላዊና ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎላ አጀንዳዎችንም ለይተው ለኮሚሽኑ የሚያስረክቡ ይሆናል " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ የምክክር መድረክ እጅግ መሰረታዊ የሆኑ ጉዳዮች የሚለዩበት ወሳኝ ምዕራፍ እንደሆነ ጠቁመው ወኪሎች በንቃት በመሳተፍ ክልላዊና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን አጀንዳዎች በመለየት በተጀመረው ዘላቂ የሀገራዊ መግባባት የማረጋገጥ ጉዞ አሻራቸውን እንዲያስቀምጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ሙሉ ቃላቸው ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-10-20

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሶማሌክልል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ካለፈው ሰኞ ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በሱማሌ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰቢያ የምክክር መድረክ እያደረገ ይገኛል፡፡ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)  ፥ ከጥቅምት 4-6/2017 ዓ.ም በክልሉ ሶስት ማዕከላት ፦ - በጅግጅጋ ፣ - በጎዴ - በዶሎ አዶ ማዕከላት ከ 1 ሺ በላይ የማህበረሰብ ወኪሎችን በማመካከር አጀንዳዎቻቸውን እንዲለዩ ማድረግ…
#ሶማሌክልል

" መሳሪያ አንግበው በጫካ እየታገሉ ያሉ ሰዎች በሌሉበት ምክክሩ የተሳካ ይሆናል የሚል ግምት የለንም  "- ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በሶማሌ ክልል ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር አጀንዳ የመሰብሰብ የምክክር ምዕራፍ እያደረገ ነው።

ከባለድርሻ አካላት መካከል የፓለቲካ ፓርቲዎች ተጠቃሽ ሲሆኑ፣ በውይይት መድረኩ የተገኘው ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ከቲክቫህ ኢትዮጵያና ሌሎች ሚዲያዎች ጋር ቆይታ አድርጓል።

ስለውይይቱን ሂደት፣ የኮሚሽኑን አካታችነት፣ የታጠቁ ኃይሎች፣ የባሕር በርን በተመለከተ ጥያቄዎች የቀረቡላቸው የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ኢሴ ባናሃጂ አቡቦከር ምላሽ ሰጥተዋል።

ምን አሉ?

" የኢትዮጵያዊያን ግጭትን የምናስወግድበት የራሳችን ባህሎች አሉን። ባህሎቻችንን ባለመከተል በአገራችን ብዙ ችግሮች እየተከሰቱ ስለሆነ እነዚህን ችግሮች ይቀርፋል ተብሎ ነው መድረኩ የተዘጋጀው።

በመድረኩ የሶማሌ ህዝብን ወክለን መጠየቅ ያለብንን ነገር እየተወያዬን ነው።

(ለምሳሌ ህዝቡ ከዚህ በፊት በነበሩት መንግስታት የደረሰበት በደል፤ ቅሬታ፣ ቁስል አለው)፤ በቅድሚያ ህዝቡ ያለበት ቁስል ይታከም። ብዙ አጀንዳዎች አሉ።

ከአካታችነት አንጻር እኛ እንደ ፓለቲካ ፓርቲ አገራዊ ውይይቱ የበለጠ ውጤታማ ይሆናል ብለን የምንጠብቀው በመድረኩ ያልተካተቱ ሰዎች ቢካተቱበት ነው።

መሳሪያ አንግበው በጫካ እየታገሉ ያሉ ሰዎች በሌሉበት ምክክሩ ሰክሰስፉል ይሆናል የሚል ግምት የለንም። 

እነርሱ እንዲካተቱ ነው እንደ ፓለቲካ ፓርቲ ደጋግመን እየጠየቅን ያለነው። መድረኩ ለማንም የሚጠቅም እንጂ ማንም የሚከስርበት አይደለም። 

መሳሪያ አንግበው በጫካ እየታገሉ ያሉ አካላትም ወደ መድረኩ መጥተው ሀሳባቸውን አቅርበው በሚያግባባን ሀሳብ እንድንግባባ፣ በማያግባባ ሀሳብ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ተሰብስቦ ሪፈረንደም እንዲያደርግ ነው አስተያየት የምንሰጠው
" ብለዋል።

በመድረኩ የተዳሰሱ ጉዳዮችን በተመለከተም፣ " የፓለቲካ ፓርቲዎች እንደ ጥያቄ ያቀረቡት አጀንዳ፣ ለምላሌ የኛ ፓርቲ፣ አሁንም አገራችን እየተመራችበት ያለውን ፌደራሊዝም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ሌላው የኢትዮጵያ ባንዲራን በተመለከተ ነው። ስለኢትዮጵያ ባንዲራ የኛ ፓርቲ ያለው አመለካከት ባንዲራው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ አይወክልም የሚል ነው " ብለዋል።

" ስለዚህ አሁን ያለው ባንዲራ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ሁሉ አንድ ላይ በመሆን ሁሉንም የሚወክል ምልክት ተደርጎበት ባንዲራ ላይ ለውጥ እንዲደረግ የሚል አስተያየት ነው ያቀረብነው " ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ መንግስት ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የባሕር ወደብ በተመለከተ ተጠይቀው ባደረጉት ገለጻ፣ " እንደ ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ኢትዮጵያ የባሕር ወደብ እንድታገኝ በጣም እንፈልጋለን " ብለዋል።

" ግን እንደ ፓርቲነት ይሄን ባሕር የምንፈልገው ከዚህ በፊት የባሕር በር የሌላቸው ብዙ የአፍሪካ አገሮች ባሕር ያገኙበትን መንገድ ተከትለን ኢንተርናሽናል ሕግ በሚፈቅደው ሁኔታ እንዲሆን ነው " ሲሉ አክለዋል።

ኢትዮጵያ ከሱማሌላንድ ጋር ባደረገችው የባሕር በር ሥምምነት ክልሉ ያደረበት ስጋት አለ? ተብሎ ለቀረበላቸው በምላሻቸው፣ " አዎ። ኢትዮጵያ መንግስት ከሱማሌላንድ ጋር ያደረገው ሥምምነት እኛ ላይ አንዳንድ ስጋት ፈጥሮብናል " ነው ያሉት።

" ባሕር ያልነበራቸው አገሮች ከጎረቤት አገሮች ጋር ኢንተርናሽናል ሕግን መሠረት ባደረገ መንገድ ተፈራርመው ባሕር እየተጠቀሙ ነው። የነርሱን ልምድ በተከተለ መንገድ የባሕር በር ብናገኝ ፍላጎታችን ነው " ብለዋል።

የኦጋዴን ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ከሀገራዊ  ምክክሩ እንዳገለለ በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ያስታወቀ ሲሆን፣ ፓርቲው በዝርዝር ምላሽ እንዲሰጥ ለማድረግ ያደረግነው ጥረት ፓርቲው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለጊዜው አልተሳካም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia