TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ገና ሥጦታ ሎተሪ ወጣ!!!
==========
ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና በዓል) አደረሳችሁ፡፡ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው #የገና_ሥጦታ ሎተሪ ታህሳስ 29/2011 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል፡፡

1ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር ---1181826

2ኛ. 2,500,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር--1217
997

3ኛ. 1,250,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር---0300615

4ኛ. 600,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር---1208339

5ኛ. 300,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር---1259473

6ኛ. 150,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር--1355808

7ኛ. 75,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር---1207871

8ኛ. 15 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 3,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር--95710

9ኛ. 15 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር---54931

10ኛ.150 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 600 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር--- 6574

11ኛ. 150 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 300 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር---8186

12ኛ. 150 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 150 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-- 5988

13ኛ. 1,500 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 120 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር---979

14ኛ. 1,500 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 90 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር----764

15ኛ. 15,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 45 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር----97

16ኛ.150,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 30(የማስተዛዘኛ) ዕጣ ቁጥር ---4

አስተዳደሩ ሎተሪው ለደረሳቸው ዕድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ እያለ ዜናውን ለጓደኞቻችሁ በማጋራት (share በማድረግ) ለሌሎች እንዲደርስ አድርጉ፡፡ እናመሰግናለን!! መልካም በዓል!

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጋቦን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ #መክሸፉን ተከትሎ በርካታ ባለስልጣናት #በቁጥጥር ስር ዋሉ። የምዕራብ አፍሪቃዊቷ ሀገር ጋቦን ወታደሮች በዛሬዉ ዕለት በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን መቆጣጠራቸዉን ገልፀዉ ነበር። ወታደሮቹ ለጥቂት ሰዓታት ተቆጣጥረዉት በነበረዉ የሀገሪቱ የሬዲዮ ማሰራጫ ጣቢያ እንደተናገሩት፣ መፈንቅለ መንSስቱን ያደረጉት ከጎርጎሮሳዉያኑ 2009 ዓ/ም ወዲህ በስልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ አምባገን አገዛዝ ለማብቃት እና በምትኩ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ነበር። ይሁን እንጅ፣ ይኸው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሸፉን የሀገሪቱ የጋቦ መንግስት ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ገልጿል። ይህን ተከትሎም የመፈንቅለ መንግስቱ መሪ እና ሌሎችአራት የጦር መኮንኖች በመዲናዋ ሊብረቪል በሚገኘው የሀገሪቱ ብሄራዊ የሬዲዮ ጣቢያ አጠገብ በቁጥጥር ስር ውለዋል ሲሉ የሀገሪቱ መንግስት ቃል አቀባይ ገልፀዋል። የአፍሪቃ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መህመትና የፈረንሳይ መንግስትn የመፈንቅለ መንግስቱን ሙከራ አዉግዘዉታል። የጋቦ ፕሬዚደንት ቦንጎ ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ በሞሮኮ ውስጥ በህክምና ላይ ይገኛሉ።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦነግ/ABO/~ወቅታዊ መግለጫ‼️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦነግ/ABO/‼️

ሰላም ይስፈን ዘንድ ጦርነቱ ቆሞ ስምምነታችን #ልታደስና ልጠናከር ይገባል!!

ኦነግ በመራዉ የኦሮሞ ሕዝብ የነጻነት ትግልና ሕዝባችን (በተለይም ቄሮ) በከፈለዉ ዉድ መስዋዕትነት ኢሕአዴግ ተገዶ ለሰላም ጥሪ መልስ እንድሰጥ በመደረጉ ላለፉት 8 ወራት ለሁሉም የሚጠቅም የሰላም መስኮት/ዕድል የተከፈተ ወይም የተፈጠረ መስሎ ነበር።

የኦሮሞ ነጸነት ግንባርም መታደሱንና ለሰላም ዝግጁነቱን ከተናገረዉ የኢሕአዴግ መንግስት ጋር በሰላም አብሮ ለመስራት ከስምምነት ደርሶ፣ ሁሉንም ወገኖች በሰላማዊ መንገድ አብሮ ለመስራት በሚያስችል ስርዓት ዉስጥ የበኩሉን አስተዋጽዖ ለማበርከት ወሰነ። በዚህም የኢትዮጵያ መንግስትና ኦነግ በመካከላቸዉ የነበረዉን ጦርነት ለማቆም የጋራ ዉሳኔ ላይ ተደረሰ።

ይሁን እንጂ እስካሁን ኢሕአዴግና የመንግስት ስርዓቱ ከጸረ-ዴሞክራሲ ኣቋምና ኣካሄዱ ፈቀቅ ባለማለቱ እዉነተኛ መስዋዕትነት የከፈሉት ወገኖች ለዉጡን ለማሳካትና ስርዓቱንም ለማሻሻል ተሳታፊ እንድሆኑ ኣልተደረገም። በመሆኑም በስርዓቱ የሚካሄዱ ኣፈናዎች፣ እስራት፣ ግድያ፣ እና ሌሎችም የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዛሬም ድረስ እንደቀጠሉ ናቸዉ። ለዚህም ማሳያ ልሆኑ ካሚችሉት በጥቂቱ:

1) በተደጋጋሚ በኦሮሞ ሕዝብና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ላይ (በተለይ በምዕራብ ኦሮሚያ) በኢሕአዴግ ሠራዊት እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች

2) ከድንበር ጉዳይ ጋር ተያይዞ በሓረርጌ፣ በባሌ፣ በቦረና፣ በጉጂ፣ በወሎና በወለጋ በኩል በሰላማዊ (ትጥቅ-ኣልባ) ሕዝባችን ላይ እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች

3) በመላዉ ኦሮሚያ በሰፊዉ እየተካሄዱ ያሉ ኣፈና፣ እስራት፣ ግድያና የተለያዩ ኢ-ሰብዓዊና ኢ-ዴሞክራሲያዊ ድርጊቶች

4) በተደጋጋሚና በስፋት (የመንግስት ከፍተኛ አመራር አባላት ሳይቀሩ እየተሳተፉበት) በኦነግና በኦሮሞ ነጻነት ትግል ላይ የሚካሄዱ የስም ማጥፋት ዘመቻና ፕሮፓጋንዳዎች

5) በኦነግና በመንግስት መካከል የተደረሰዉ ስምምነት እንዳይተገበር ሆን ተብሎ የኦነግ ከፍተኛ ኣመራር ፍንፍኔ ከገባበት ዕለት ጀምሮ በርካታ የተለያዩ ዓይነት እንቅፋቶችን በመፍጠርና ኦነግ ጽ/ቤቶቹን ከፍቶ በኣግባቡ እንዳይንቀሳቀስና እንዳይሰራ ለማደናቀፍና ለመገደብ እየተሰሩ የቆዩና ያሉ ደባዎች

የኦሮሞ ሕዝብ ትግልና የኦነግ ጥላቻ የተጠናወታቸዉን ሓይሎችና ሚዲያዎችን በመታገዝ የሚካሄዱት እነዚህ ኣፍራሽ ድርጊቶች የኦሮሞን ሕዝብና የነጻነት ትግሉን ለከፍተኛ የአደጋ ስጋት ኣጋልጠዉት እንደሚገኙ በግልጽ ይታያል። ይህ ደግሞ ለሃገሪቷ ሰላምም በጎ ኣስተዋጽዖ ይኖረዋል ተብሎ ኣይታሰብም። ስለሆነም ይህን ችግር በጊዜና በኣግባቡ ለመፍታት፣ ብሎም ስምምነቱና ለዉጡ መንገዱን እንዳይስት ለማድረግ፥

1) ሁሉም ሰላም ወዳድ ወገኖች፣ በተለይ ደግሞ የኦሮሞ ሕዝብ ይህ መንግስት እያካሄደ ያለዉን ጦርነት እንድያቆም ኣስፈላጊ ጫና ማድረግና

2) በኦነግና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የተደረሰዉን ስምምነት (በተለይ ደግሞ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን የሚመለከት) ኣሁን የተፈጠረዉን ኣድስ ሁኔታ ለማስታረቅና ለመፍታት በሚያስችል ሁኔታ ለማሳደስና ለማጠናከር (to consolidate)፣ ሦስተኛ ወገን በሚገኝበት በአድስ እንድንወያይበት ጥሪ እናቀርባለን።

ኦነግ በበኩሉ በማንኛዉም ሁኔታ ዉስጥ በሰላማዊ መንገድ መሥራቱን እንደሚቀጥልበት በድጋሚ ያረጋግጣል።

ድል ለኦሮሞ ሕዝብ !
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
ጥር 07, 2019 /ታሕሳስ 29 2011 ዓም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ይኸ አገር የሁላችንም ነው። ጸሎት የሚያስፈልግም ከሆነ ተባብረን ጸሎት ማድረግ አለብን። ስንጣላም አገርን #የማስቀጠል ኃላፊነት እንዳለበት ትውልድ ሆነን እንጣላ" ድምፃዊ #አብርሐም_ገብረመድሕን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ‹‹ሰላም #ዋናው ትኩረታችን ነው፡፡›› ሲሉ የሽግግር አካል ኦነግ ሊቀመንበር አቶ #ገላሳ_ዲልቦ አስታወቁ፡፡ ለውጡ በመልካም መንገድ ላይ ነው የሚል እምነት እንዳላቸውም ገለጹ፡፡ ሊቀመንበሩ አቶ ገላሳ ዲልቦ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤በሀገሪቱ ችግሮች ቢስተዋሉም፤ የሚታይ ለውጥም አለ፡፡ ችግሩን ደግሞ ታግሎ መፍታት ይቻላል፡፡ ‹‹ህዝቡ ምን ይዛችሁ መጣችሁ የሚለን ከሆነ የህዝቡ ጥያቄ እንዳለ ሆኖ አንዱ ዋና ትኩረታችን ሰላም መሆኑን እገልጻለሁ፡፡ ሲሉ ሊቀመንበሩ አስታውቀዋል፡፡

via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ‹‹የወልቃይትና የራያ ጉዳይ ህዝብ እየሞተበት ያለ ጥያቄ እንደመሆኑ #በቀላሉ የሚታይ አይደለም›› ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ሚኒስትር ዶክተር #አምባቸው_መኮንን አስታወቁ፡፡ ለኢፌዴሪ ፕሬዚዳንትነት መታጨታቸውን ህዝቡ ባለመፈለጉ በፖለቲካ ተሳትፏቸው መቀጠላቸውንም ተናግረዋል፡፡ አማካሪ ሚኒስትሩ ዶክተር አምባቸው መኮንን በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በወልቃይትና በራያ አካባቢ የሚታየው ችግር በአዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን፣ ለአገሪቱም የሰላም #መናጋት ምክንያት እየሆነ ያለ ጥያቄ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ ካልተፈታ ሁለቱ ክልሎችም ሆኑ አገሪቱ ሰላም አያገኙም ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች #የሰላም_ሳምንት ማወጃቸው ተነግሯል። የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች ያወጁት የሰላም ሳምንትም ከታህሳስ 29 ቀን 2011 ዓ.ም እስከ ፊታችን እሁድ ጥር 5 ቀን  2011 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ መሆኑም ተገልጿል። በዚህ የሰላም ሳምንት ወቅትም የሰላም እና የመቻቻል የውይይት መድረኮቸን ጨምሮ  የተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚካሄዱ መሆኑንም ነው ያስታወቁት። በኢትዮጵያ መረጋጋት እና ዘላቂነት ያለው ሰላም እንዲሰፈን የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም ነው የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች ያስታወቁት።

via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሼር!! የ2011 ዓ.ም #ገና_ሥጦታ_ሎተሪ ማውጫ ነው፡፡ ሼር አድርጉ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ኢትዮጵያ ለአገራቸው እያደረገች ያለውን አስተዋፅኦ አደነቁ። ፕሬዝዳንቱ በደቡብ ሱዳን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር የነበሩትን ፍስሀ ሻውልን ጁባ ውስጥ ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ጠንካራ ግንኙነትን አድንቀው መንግሥታቸው የሁለቱን አገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ከፍታ ለማድረስ ቁርጠኛ መሆኑንም ገልጸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ቅንነት ብዙ ጥቅም አለው፡፡ ፀሐይ በረዶን እንደሚያቀልጥ ሁሉ #ቅን መሆንም እንዲሁ አለመተማመን ፣ ጥላቻን እና አለመግባባትን ያተናል፡፡" ኢ/ር #ታከለ_ኡማ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድከር በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ አመሻሹን አዲስ አበባ የሚገቡ ሲሆን፥ በኢትዮጵያም የሶስት ቀናይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ መንግሥት ነው፣ ያለው #እኔ የምመራው መንግሥት። አንድ ዓመት ተኩል በኋላ እኔ እና ድርጅቴን ካልመረጣችሁ አቅፌ ስሜ እሰጣችኋለሁ። ከምርጫ በፊት በ 3 ወር በ 5 ወር መንግሥት እሆናለሁ የሚል #ቅዠት ኢትዮጵያ ውስጥ #አይሰራም። ይሄ ቅዠት የማይሰራበት ምክንያት እኔ እንኳን ብፈቅድ አንድ ዓመት ተኩል ታግሶ ማሸነፍ ያልቻለ ፓርቲ ነገ መጥቶ እዚህ ቢገባ ያምሰናል እንጂ እንዴት ይመራናል? 30 ዓመት 20 ዓመት የኢትዮጵያን ምድር መርግጥ ያልቻሉ ሰዎች ይብቃ ብለን ሕግ ቀይረን፣ ባሉበት አናግረን፣ ለምነን አምጥተን ስናበቃ #ልንወጋ አይገባም” ጠ/ሚ #ዐብይ_አሕመድ (ዶ/ር)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በመከላከያ ሰራዊቱ የተደረገው ሪፎርም ሰራዊቱ የሚሰጠውን ግዳጅ በአግባቡ እንዲወጣ የሚያደርግ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ተናገሩ። የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር #አይሻ_መሀመድ በዛሬው እለከት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የ6 ወር አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅሬታ‼️

ቀን 08/04/2011 ዓ.ም

ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
አዲስ አበባ

አቤቱታ አቅራቢዎች፡የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተቀጣሪ ቴክኒካል ረዳቶች

ጉዳዩ ፡ የቴክኒካል ረዳቶች የእርከን አድገት፤የትምህርት እድልና ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞች ችግሮች መፍትሄ እንዲሰጠን ስለመጠየቅ፡፡

ከላይ በርእሱ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ አቤቱታ አቅራቢዎች በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ካምፓሶች ተቀጥረን በመስራት ላይ የምንገኝ የቴክኒካል ረዳቶች ስንሆን ስራችንን በቅንነት እና በታማኝነት በማገልገል ላይ እንገኛለን፡፡

በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ዉስጥ የተግባርና የንድፈ ሀሳብ ትምህርትና ስልጠና በመስጠት ለትምህርት ጥራት መጎልበት የራሳችንን ጥረት በማድረግ ለሀገሩና ለራሱ የሚጠቅም በተግባር ትምህርት የተደገፈ ብቁ ዜጋን በማፍራት ረገድ የበኩላችንን አስተዋፆ በማድረግ የመማር ማስተማር ስራ በተሳለጠ ሁኔታ እንዲካሄድ የበኩላችንን አስተዋፆ ብናደርግም ለረጅም ጊዜያት መንግስትም ሆነ ዩኒቨርሲቲዉ በአሁኑ ወቅት ካለዉ ነባራዊ የኑሮ ሁኔታ አንፃር ምንም አይነት ድጋፍ ሊደርግልን ባለመቻሉ ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋልጠን እንገኛለን፡፡

የቴክኒክ ረዳቶች ጉዳይ ሲነሳ በዋናነት የትምህርት ጥራት ጉዳይ ይነሳል፡፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት መንግስት ለትምህርት ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በሰጠበት እንዲሁም በዋናነት የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ ያለ የተደራጀ ላብራቶሪ እና ያለ ቴክኒካል ረዳት የትምህርት ጥራት የማይታሰብ መሆኑ ግልጽ ነዉ፡፡ ከሁሉ በላይ በጥቅሉ ስንገመግመው የሚኒስትር መ/ቤቱ ይህንን ከግምት ዉስጥ ያስገባ አይመስለንም፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆኑ አብነቶቸ እንደሚከተለው በዝርዝር አቅርበናል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 650/2001 በትርጉም ክፍሉ አንቀፅ 2(1) ስር “የአካዳሚክ ማህበረሰብ” ማለት በተቋም ውስጥ በመደበኛም ሆነ በጊዜያዊነት በመማር ማስተማርና በምርምር ስራ ተሰማርተው የሚገኙ ሰዎችን ያቀፈ ነው በሚል ትርጉም የሰጠው ሲሆን እኛም ቴክኒካል ረዳቶች እንደ ማንኛውም የአካዳሚክ ማህበረሰብ በመማር ማስተማር ስራ ውስጥ ያለን ቢሆንም እንደ አካዳሚክ ሰራተኛ ተቆጥረን የደመወዝ ደረጃ፤ የእርከን እድገትና የትምህርት እድልና ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም ያለ ምንም ገደብ ሊሰጠን ሲገባ በዩኒቨርሲቲው ግን በየትኛው መደብ እንደምንመደብ ግልፅ ባለመሆኑ መብታችን ተገድቦ ይገኛል፡፡

ቴክኒካል ረዳት አካዳሚክ ወይም አስተዳደር ሠራተኛ ናቸው ተብለው ወደ አንዱ ወጥ በሆነ መንገድ ባለመመደባችን በዚህ ምክንያት አስፈላጊውን ጥቅም ያለማግኘት፤ ደሞዝ ጭማሪ፡ የቤት አበል፡ የትምህርት ዕድል ካለው ቴክኒካል ረዳት ብዛት ጋር ፍጹም ተመጣጣኝ አለመሆን፡ የደረጃ እርከን ካለው የስራ ጫና አንጻር ተመጣጣኝ አለመሆኑ እና የወጪ መጋራት እንደ መምህራን በአገልግሎት ሳይሆን ወይም በክፍያ ብቻ መሆኑ የጎዳን ሲሆን ከቀድሞው ትምህርት ሚኒስቴር የተላከውም መመሪያም ቢሆም የቴክኒካል ረዳቶችን መብት የሚገድብና ፍትሀዊነት የሌለው ከመሆኑም በተጨማሪ በመመሪያው መሰረትም በተግባር አለመሰራቱ ከፍተኛ በደል እየተፈፀመብን በመሆኑ ሚኒስትር መ/ቤቱ ጉዳዩን በጥሞና እንዲመለከትልን እንጠይቃለን፡፡

ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠን የትምህርት እድል የመወዳደሪያ መስፈርቱ በየጊዜው የሚቀያየርና በኮታ የተገደበ መሆኑ ለምሳሌ በአመት አምስት ተማሪ ብቻ የትምህርት እድል እንዲያገኝ መደረጉ በእጅጉ መብታችንን የገደበ አሰራር ከመሆኑም በላይ የአካዳሚክ ሰራተኞች በመጀመሪያ ዲግሪ ሲቀጠሩ ወዲያውኑ ያለ ምንም ገደብ በግዴታ ጭምር የማስተርስ ትምህርት እንዲማሩ እየተደረገ ባለበት የቴክኒካል ረዳቶች የትምህርት እድል በቁጥር መገደቡ ካለው የመማር ፍላጎት ጋር የማይመጣጠንና በኢ/ፌ/ድ/ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 25 ስር የተደነገገውን የዜጎችን የእኩልነት መብት የሚፃረር በመሆኑ በአስቸኳይ ማሻሻያ ሊደረግበት ይገባል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በዓሉን ምክኒያት በማድረግ ለቲክቫህ ቤተሰቦች ብቻ 10% ቅናሽ!!

የሚፈልጓቸውን እና የሚወዷቸውን ምግቦች እየተመገቡ የሰውነት ክብደትዎን ማስተካከል ይፈልጋሉ?

አሁኑኑ ይመዝገቡ!!

95% ስኬት ያስመዘገበው ኒድ የስነምግብ ማማከር አገልግሎት/ ሰውኛ ቲቪ ሾው የአመጋገብ ሁኔታዎን በማስተካከል ሙሉ የህይወት ዘይቤዎን ቀይረው ጤናማና ደስተኛ እንዲሆኑ ይረዳዎታል፡፡

በፋና ቲቪ የሚተላለፈው በስነምግብ ዙሪያ የሚያጠነጥነውን ሰውኛ የተሰኘው የቲቪ ፕሮግራማችንንም ይከታተሉ!

አድራሻ፦ Morning star mall 1st floor/ no 35
0942-18-43-18
0953-11-93-29

https://t.iss.one/Neednutrition
#update ከኢትዮ-ኤርትራ ድንበር አከባቢ ከባድ የጦር መሳርያ ይዘው የሚንቀሳቀሱ የመከላከያ ሠራዊት መኪኖች ሽሬ ከተማ አቅራቢያ በነዋሪዎች መንገድ ተዘጋባቸው።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia