TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሀዋሳ⬇️

በሀዋሳ ከተማ ሁለት ወጣቶች ህይወታቸው አልፎ መገኘታቸውን ነዋሪዎች ገለፁ። የመጀመሪያው የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ 4ኛ አመት ተማሪ የሆነው ተማሪ ደሳለኝ በናና በ23/12/2010 ገብርኤል አካባቢ ተገድሎ ተገኝቷል። ሌላኛው ወጣት ነኸምያ ጌታቸው ነሀሴ 24/2010 ዓ.ም በአላሞራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካባቢ ተገድሎ ተግኝቷል።

ወጣቶቹ በምን ምክንያት እንደተገደሉ አልታወቀም። እንዲሁም የወጣት ነኸምያ ግድያ ከተማሪ ደሳለኝ ጋር ግንኙነት እንዳለውም የታወቀ ነገር የለም። ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል እየሰራሁ ነው ብሏል።

ለቻናላችን አስተያየታቸውን የላኩ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት ይህን ወንጀል ይፈፀሙ አካላት #በአስችኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። የከተማው ፖሊስም የዜጎችን #ደህንነት የማስጠበቅ ስራውን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1