TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

“ በእኛ የህግ አማካሪ በኩል ጥፋት ነበረ ” - ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው

በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ የሚገኘው፣ 90 ዓመት ያስቆጠረ፣  በታሪካዊ ቅርስነት መመዝገብ አለበት በሚል በፍርድ ቤት በኩል ጉዳዩ ተይዞ ነበር የተባለለት ሎሞባርዲያ ሬስቶራንት ሳይፈርስ እንዲቆይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቢሰጥም ሰሞኑን በግብረ ኃይሎች እንዲፈርስ መደረጉ ብዙዎቹን ቅር አሰኝቷቶ ተስተውሏል።

ሎሞባርዲያ እንዳይፈርስና እንዲቆይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ካስተላለፈ የፈረሰበት ምክንያት ምን እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣንን ጠይቋል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ “በእኛ የህግ አማካሪ በኩል #ጥፋት ነበረ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

አክለውም፣ “ምክንያቱም የፍርድ ሂደቱ እንዴት ፕሮሰስ እንዳደረገ አላሳወቀንም። ከዚህ በፊት ሰበር እስከሚቀርብ ድረስ አሁን ያለን የህግ አማካሪ ነው ሲከራከር የነበረው። መመሪያ ስናጸድቅና ይህን ዲስከስ ስናደርግ፣ ለማኔጅመንት፣ ለውይይት ለባለሙያ ሲቀርብ ሁሉ ነበር” ብለዋል።

“መጨረሻ ላይ እኔን #‘ታስሮ ይቅረብ’ የሚል ፍርድ መጣ (አፈጻጸም ላይ ደርሶ ማለት ነው)። መጨረሻ ላይ ‘ምንድን ነው?’ ስንል ዶክሜንት ሲመጣ የህግ አማካሪው ያሉት ‘የተቋሙ ኃላፊ ናቸው እንጂ #መመሪያውም አይፈቅድም’ የሚል ነው” ሲሉ ሁነቱን አስረድተዋል።

ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አክለውም፣ “መሀል ላይ ገባንና እኛ፣ ለፍርድ ቤት ይሄ ሁሉ አልደረሰም አንድ፣ ሁለተኛ አዋጁን ተንተርሰን በወጣ መመሪያ መሠረት ነው ውሳኔ የሰጠነው። ይሄ የዋና ዳይሬክተሩም ሳይሆን የባለሙያ ውሳኔ ነው” ብለው እንዳስረዱ ገልጸዋል።

“እሱን ከኬዙ ለጊዜው አስወጥተነዋል። ምክንያቱም አንድ የተቋም አማካሪ ወይም ነገረ ፈጅ የተቋሙን ውሳኔ ነው አይደል ማስከበር ያለበት!? መከራከር ያለበት!?” ያሉት አቶ አበባው፣ “እሱ በእኛ የሚሆነው ይሆናል” ነው ያሉት።

ዋና ዳይሬክተሩ የሎሞባርዲያን መፍረስ በተመለከተ ማብራሪያ በሰጡበት አውድ፣ “ለባለሙያ አውርደን አምና በዚህ ሰሞን ተመዘነ። ስለዚህ አላሟላም። ከመቶ ነው የሚመዘነው። ሲመዘን 38 ነጥብ ነው ያመጣው። ይሄ ማለት ቅርስ ብለን ልንይዝ አንችልም ማለት ነው” ብለዋል።

በቅርስነት እንዲቆይ (ላለመፍረስ) ሲመዘን ስንት ነጥብ ማምጣት ነበረበት? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ “ከ50 በላይ መሆን አለበት። ከ49 በታች ቅርስ ሊሆን አይችልም” የሚል ምላሽ ሰጥተው፣ የአቶ ጌትነትን ሞት በተመለከተ ተቋሙ ከለላ የማድረግ ኃላፊነት እንደደሌለው፣ በግለሰብ ደረጃ በሟቹ ሀዘን እንደተሰማቸው ተናግረዋል።

(ሬስቱራንቱ ከ100/38 አምጥቷል ያሉባቸውን እያንዳንዱን መለኪያ መስፈርቶች እንዲያስረዱና ሌሎች ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠይቋቸው የሰጡበትን የአቶ አበባውን ዝርዝር ሀሳብ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።)

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia