TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"መያዣ መጨበጫ የሌላቸው #ሐሰተኛ መረጃዎች በማሠራጨት የወጣቶችን አዕምሮ መበከል፣ ለዚህ ዘመን የማይመጥን #ኋላቀርነት ነው፡፡ ለአገር ዕድገትና ብልፅግና የሚያግዝ ለጋ አዕምሮን በሐሰተኛ ወሬ ማበላሸት አሳፋሪ ነው!" #ሪፖርተር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አንጎለላና ጠራ ወረዳ‼️

በአንጎለላና ጠራ ወረዳ #ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከመንግሥት ካዝና ከ466 ሺህ ብር በላይ ለግል ለጥቅሟ ያዋለችው ግለሰብ በ18 ዓመት ጽኑ እሥራትና የገንዘብ ቅጣት ተጣለባት።

በሰሜን ሸዋ ዞን ፍርድ ቤት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ወይዘሪት ዘርትሁን ያዘው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ፍርድ ቤቱ በግለሰቧ ላይ ቅጣቱን የወሰነው በወረዳው ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽህፈት ቤት ገንዘብ ያዥ ሆና ስትሰራ የመንግሥትን ገንዘብ ለግል ጥቅሟ ማዋሏ በመረጋገጡ ነው።

ተከሳሿ ወይዘሮ #አበበች_ጽጌ ከ2007 እስከ 2009 ዓ.ም ድረስ በጽህፈት ቤቱ ስትሰራ ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና መንግሥታዊ ሰነድ በመደበቅ የሙስና ወንጀል መፈፀሟ በሰውና በሰነድ ማስረጃ እንደተረጋገጠባትም አስረድተዋል።

ግለሰቧ በአገር አቀፍ ደረጃ በውሃና በአካባቢ ንጽህና ፕሮጀክት (ዎሽ) ግዢ ከአቅራቢዎች ላይ የተሰበሰበ ሁለት በመቶ ገንዘብ 171ሺህ 417ብር ለግል ጥቅም ማዋሏ ተረጋግጦባታል ነው የተባለው።

እንዲሁም በ56 ደረሰኞች ላይ በበራሪው ትክክለኛዉን የገንዘብ መጠን በመመዝገብና የከፋዮችን ስም በመቀያየር የገቢ መጠኑን በመቀነስ ለመንግሥት መግባት የነበረበት 94ሺህ 90 ብር ሰነድ በማበላለጥ መጠቀሟም ነው የተገለፀው።

በተጨማሪም በራሪ ደረሰኞችን ለከፋይ በትክክል ቆርጣ ከሰጠች በኋላ በሁለተኛና ሦስተኛ ካርኒዎች ላይ አቀናንሳ 181ሺህ 16 ብር ለግል
ጥቅማቸው ማዋላቸው መረጋገጡን ባለሙያዋ ገልጸዋል።

ግለሰቧ ወንጀሉን ከፈጸሟ በኋላ ከአካባቢው በመሰወሯ ፖሊስ ወንጀለኛዋን አድኖ በመያዝ ለማረሚያ ቤት እንዲያስረክብም ትዕዛዝ
ተሰጥቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለአምስት ዓመታት ከማንኛውም የእንቅስቃሴ መብቷ እንደታገደችም ተወስኖባታል።

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሜቴክ ሃለፊዎች ላይ ክስ ተመሰረተ‼️

#ሐሰተኛ_የማስተርስና_የዶክትሬት ዲግሪዎች እንዲሰጡ አድርገዋል የተባሉት የሜቴክ ኃላፊዎች ላይ ክስ ተመሠረተ።

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ላላስተማራቸውና ባልተቀረፀ የትምህርት ካሪኩለም ሐሰተኛ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪዎች እንዲሰጡ አድርገዋል የተባሉት፣ የቀድሞ የሜቴክ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ በስምንት ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሠረተ፡፡

በአሜሪካ መንግሥት ከሚታወቀውና በዓለም ላይ አሉ ከሚባሉ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ዋነኛ ከሆነው ካሊፎርኒያ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ጋር ተቀራራቢ ስም ያለው ተቋም፣ ነገር ግን በማንም የማይታወቅ በማስተርስና በዶክትሬት ዲግሪዎች ለማስተማር መኮንን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) በተባለ ተጠርጣሪና ባልተያዘ ግለሰብ መቋቋሙን ክሱ ያስረዳል፡፡

ግለሰቡ ራሱን የሐሰተኛ ተቋም ሥራ አስኪያጅ አድርጎ በማቅረብ፣ ከቀድሞ የሜቴክ ኃላፊዎች ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው፣ ብርጋዴር ጄኔራል ጥጋቡ ፈትለ፣ ሻለቃ ገብረ ሥላሴ ገብረ ጊዮርጊስ፣ ሻለቃ ፋሲልአበራ፣ መቶ አለቃ ቶማስ ደረሰ፣ ወሰን የለህ ኃይለ ሚካኤልና ሀድአት ወልደ ትንሳይ በተባሉ የሜቴክ የተለያዩ ክፍል ኃላፊዎች ጋር በጥቅም በመመሳጠር፣ ሐሰተኛው ተቋም ከሜቴክ ጋር ከፍተኛ ትምህርት ለማስተማር የውል ስምምነት መፈራረሙንና ዋና ዳይሬክተሩ እንዲፀድቅ ማድረጋቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

ግለሰቡ ድርጊቱ በኢትዮጵያ መንግሥት እንዳይታወቅ የተለያዩ የውጭ አገር ዜጎችን በቱሪስት ቪዛ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ፣ ክፍያው በውጭ ምንዛሪ እንዲፈጸምላቸው ስምምነት ማድረጉን ክሱ አክሏል፡፡ ግለሰቦቹ ትምህርቱን ሳያስተምሩ ተመራቂዎች ዲግሪ በሕገወጥ መንገድ በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ እንዲሰጥ ማድረጋቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡

#በሐሰት የተቋቋመው ኮሌጅ በታዳሽ ኃይል፣ በኦፕሬሽን ማኔጅመንትናበኢንዱስትሪያል ኢኮኖሚክስ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪዎች ለመስጠት አራት ውሎችን በመፈጸም፣ በአጠቃላይ 3,901,140 ዶላር ወይም 75,114,030 ብር ሐሰተኛ ተቋሙ አሜሪካ ውስጥ በከፈታቸው የሒሳብ ቁጥሮች ገቢ ማድረጋቸውንና በእጅ አዙር የጥቅሙ ተካፋይ በመሆናቸው፣ ሥልጣንን ያላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ክስ ዓቃቤ ሕግ መሥርቶባቸዋል፡፡

በተጨማሪም ሜጀር ጄኔራል #ክንፈ #ማርዳ_መለስ ለተባለች ግለሰብ በሁለት ዙር 56,205 ዶላር ወይም 1,250,886 ብር ክፍያ ከሜቴክ እንዲከፈል በማድረጋቸው፣ ሥልጣናቸውን ያላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ ተከሳሾቹ በመንግሥት ላይ 76,364,916 ብር ጉዳት ማድረሳቸውን የቀረበባቸው ክስ ያሳያል፡፡   

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 19/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያስገነባው ስካይ ላይት ሆቴል ዛሬ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡
.
.
#ሐሰተኛ_የማስተርስና_የዶክትሬት ዲግሪዎች እንዲሰጡ አድርገዋል የተባሉት የሜቴክ ኃላፊዎች ላይ ክስ ተመስርቷል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ #የድሬዳዋ ተወላጆች በዛሬው ዕለት በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተገኝተው ያላቸው ተቃውሞ እና ቅሬታ አሰምተዋል። የፌደራሉ መንግስት ለድሬዳዋ ከተማ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥና ያሉ ችግሮችን እንዲፈታ ጠይቀዋል።
.
.
#የሰላሌ_ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትናንት ቅዳሜ "አንድ ቀን ለማህበረሰቤ" በሚል መሪ ሀሳብ #ፍቼ ከተማን ሲያፀዱ ውለዋል።
.
.
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን ቆላማ አካባቢ የስንዴ ግብርና ልማት የሙከራ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።
.
.

4ኛው የኢህአዴግ የወጣቶች ሊግ ድርጅታዊ ጉባዔ #በሃዋሳ_ከተማ ዛሬ ተጀምሯል። ጉባዔው "በተጠናከረ የወጣቶች ትግል ሀገራዊ ለውጡን ወደፊት" በሚል መሪ ቃል እስከ ጥር 19 እስከ 21 በተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ይቆያል፡፡
.
.
በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን አጎራባች ወረዳዎች በተከሰተው #ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች መልሶ በሚቋቋሙበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።
.
.
በጅማ ከተማ "ንግዳችንን እናዘምን" በሚል መሪ ቃል የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በዛሬ ዕለት ተካሂዷል።
.
.
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር ሼህ መሃመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ከእስር መፈታታቸው ተሰምቷል።
.
.
የቀድሞ ጦር ማህበር #የምስረታ_ጉባዔ ዛሬ #በደብረማርቆስ ፖሊስ ኮሌጅ ተካሂዷል።
.
.
ለአራት ቀናት በመቀለ ሲካሄድ የቆየው የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የአምስተኛው ዘመን 14ኛው መደበኛ ጉባኤ አዋጆችንና ሹመቶችን በማጽደቅ #ተጠናቋል
.
.
የድሬዳዋን ሰላምና ፀጥታ #አስተማማኝ በማድረግ የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱ እንደሚሰራ #በምስራቅ_ዕዝ_መከላከያ የሚመራው ጊዜያዊ የፀጥታ ጥምር ኮሚቴ አስታውቋል።
.
.
ምንጭ፦ ኢዜአ፣ DW፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ የጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ የምክትል ጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ etv፣ ዋልታ፣ ፋና፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
የነገ ሰው ይበለን!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አብዛን_ንግድ

20 ሺ ሠራተኞችን #ለመቅጠር ገንዘብ እያስከፈለ በመመዝገብ ላይ የነበረው ግለሰብ ከእነ ጓደኞቹ ታስሮ ፍርድ ቤት ቀርቧል። አብዛን የተሰኘ የንግድ ሥራ ድርጅት ባለቤት መሆኑ የተገለጸ ግለሰብ 20 ሺሕ ሠራተኞችን ለመቅጠር በነፍስ ወከፍ 2,477 ብር በማስከፈል፣ በርካታ ወጣቶችን በመመዝገብ ላይ እያለ ከጓደኞቹ ጋር በቁጥጥር ሥር ውሎ ታሰረ፡፡ግለሰቡ አቶ አብርሃም ዘሪሁን የሚባል ሲሆን፣ የሥራ ማስታወቂያውን በቃና ቴሌቪዥንና በሌሎች ሚዲያዎች በማስተዋወቅ፣ ከሐምሌ 1 እስከ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ እያንዳንዱ ተመዘጋቢ የ2,477 ብር ሲፒኦ አሠርቶ እንዲመዘገብ ጥሪ ማድረጉ ታውቋል፡፡
.
.
ተጠርጣሪዎቹ ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀምና በተለይ የ2011 ዓ.ም. ተመራቂ ወጣቶችን በማማለል ከሦስት ሺሕ ብር በላይ ደመወዝ እንደሚከፍል፣ #ሐሰተኛ ማስታወቂያ በማስነገር ከእያንዳንዱ ተመዝጋቢ 2,744 ብር መቀበላቸውን ፖሊስ ገልጿል፡፡ ስለማስታወቂያውና ስለሥራው የተጠራጠረው ፖሊስ ከአሥር ተመዝጋቢዎች ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ጥርጣሬውን ይበልጥ ስላጎላው፣ ግለሰቦቹን ሐምሌ 13 ቀን 2011 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር አውሎ እየመረመረ መሆኑንና ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ABZAN-07-24

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ምርጫ2013

'ከሀሰተኛ ምስሎች ተጠንቀቁ'

የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ምን እንደሚመስሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለማስተማሪያ ባዘጋጃቸው ወረቀቶች አሳይቷል።

ከዚህ ውጪ በሌላ ይዘቶች የሚሰራጩ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች #ሐሰተኛ እና ለማደናገር የሚፈበረኩ ናቸው።

ውድ የቲክቫህ አባላት የምርጫው መቃረብ ተከትሎ የሀሰተኛ መረጃ ዝውውር ከወትሮው በርከት ሊል ስለሚችል አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ አደራ እንላለን።

የምርጫ ጉዳይ መረጃዎችን ቀጥታ ከ "ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ" ውጭ ካልሆነ ለሰው ከመናገራችሁ እና ከማጋራታችሁ በፊት ደጋግማችሁን እንድታጣሩ/እንድታረጋግጡ ይሁን።

www.tikvahethiopia.net

@tikvahethiopia
" ዳሽን ባንክ ላይ የሲስተም ችግር አጋጥሟል  " የሚለው መረጃ ሐሰተኛ ነው ሲል ባንኩ ገለጸ።

ትላንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጋጥሞኛል ባለው ሲስተም ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው አገልግሎቱ ዳግም መስተካከሉ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ዳሽን ባንክም ተመሳሳይ አይነት የሲስተም ችግር ማለትም ሰዎች፦
- ያለገደብ ገንዘብ ከኤቲኤም የማውጣት
- በሞባይል ባንኪንግ ገደብ የሌለው ገንዘብ የማስተላለፍ ችግሮች ገጥሞታል በሚል እየተሳራጨ ይገኛል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይም ሰዎች ወደ ዳሽን ኤቲኤሞች በመሄድ ያለ ገደብ ገንዘብ ማውጣት እንደሚችሉ የሚገልጹ መልዕክቶች እየተዘዋወሩ ነው።

ባንኩ ግን "  ይህ ፍፁም #ሐሰተኛ መረጃ ነው " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ገልጿል።

የባንኩ ኤትኤሞች እና የዲጂታል አውታሮች ሁሉ ደህንነታቸው በአስተማማኝ ሁኔታ የተጠበቀ እንደሆነ ገልጾ ደንበኞቹ ምንም አይነት ስጋት ላይ እንዳይወድቁ አስገንዝቧል።

@tikvahethiopia
" በየቤቱ የቁም እንስሳት ማረድ / በየአካባቢው ቅርጫ አድርጎ መከፋፈል አልተከለከለም " - የአዲስ አበባ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ፥ ከትንሳዔ በዓል ጋር በተያያዘ " ህብረተሰቡ በየቤቱ የቁም እንስሳት እርድ በማካሄድ ወይም በየአካባቢው ቅርጫ በማድረግ የሚከፋፈልበት አሰራር ተከልክሏል " በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ #ሐሰተኛ ነው ሲል አሳወቀ።

ከዚህም ጋር በተያያዘ #ምንም_ዓይነት_ክልከላ ያልተደረገ መሆኑን አረጋግጧል።

ነገር ግን በየአካባቢው #በሕገወጥ_መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ድርጊቱ በከተማው ነዋሪዎች ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ብሏል።

የከተማዋ ነዋሪዎችም ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia