TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት፤ ጅዳ #ለኢትዮጵያውያን የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል። ለፅ/ቤቱ ከትላንት ምሽት ጀምሮ እየደረሱ ባሉት መረጃዎች መሠረት የሳዑዲ የፀጥታ አስጠባቂ አካላት ፦ - በጄዳ ፣ - መዲና ፣ - ጂዛን እና መካ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ዜጎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት ጉዳዩ እስኪጣራ ኢትዮጵያውያን…
#Update #SaudiArabia #Attention

"...የአካል ወይም ንብረት ጉዳት የደረሰባችሁ ዜጎች ያላችሁን ማስረጃ በመያዝ ለቆንስላ ጽ\ቤቱ ማቅረብ ትችላላችሁ" - በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ

የሳዑዲ ዓረቢያ የፀጥታ ኃይሎች በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ተከትሎ ዜጎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ማስተላለፉ ይታወቃል።

በዚህ ሂደት በተለይ ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ኖሯቸው በህግ አስከባሪ አካላት ከመጠን ያለፈ ኃይል አጠቃቀም ምክንያት የአካል ወይም የንብረት ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ያላቸውን ማስረጃ በመያዝ ለቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

አሁንም #ኢትዮጵያውያን ተገቢውን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንዲቀጥሉ የቆንስላ ጽ\ቤቱ በድጋሚ የጥንቃቄ መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አስቸኳይ የሳዑዲ አረቢያ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነና ዜጎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፎ ነበር። የሳዑዲ ፀጥታ ኃይሎች በሰሩት ኦፕሬሽን ተይዘው በሹሜሲ የማቆያ ጣብያ የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ የውሃ የምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች እጥረት እንዳጋጠማቸው ተሰምቷል።…
#Update #SaudiArabia

በሹሜሲ የማቆያ ጣብያ ለሚገኙ ዜጎች የሚደረገው የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲቆም ተወሰነ።

ውሳኔው የተላለፈው ማህበረሰቡ ባለፉት ጥቂት ቀናት እጅግ በሚያኮራ መልኩ ፈጣን ድጋፍ በማድረግ በቂ የሆኑ ቁሳቁሶች በመለገዙ፤ ለግዜው እነዚህን ቁሳቁሶች በአግባቡ መጠቀም ስለሚያስፈልግ መሆኑን በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅህፈት ቤት አሳውቋል።

ነገር ግን እንደ አስፈላጊነቱ ቆንስላው በድጋሜ የቁሶች ድጋፍ ካስፈለገው ጥያቄውን ሊያቀርብ እንደሚችል ጠቁሟል።

በቀጣይ ቀናት በማቆያ ጣብያ ለሚገኙ ዜጎች #የምግብ አገልግሎት ሲያስፈልግ ከቁጥጥር ከደህንነትና ከተገቢ የስራ ዕቅድና አፈፃፀም አኳያ አመቺ እንዲሆን ከቆንስላ ጽ/ቤቱ እና ከኮሚኒቲው ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ብቻ ድጋፉ እንዲቀርብ ጥሪ ቀርቧል።

የሳዑዲ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነና በዚህ ኦፕሬሽን ተይዘው በሹሜሲ የማቆያ ጣብያ ለሚገኙ ዜጎች የውሃ የምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች እጥረት በመከሰቱ ዕርዳታ ማድረግ የሚችሉ ካሉ እንዲያቀርቡ መጠየቁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#SaudiArabia

'በሳዑዲ አረቢያ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ድምጽ እንሁን' በሚል የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ወጣቶች ህብረት ባዘጋቸው የበይነ መረብ ውይይት ኢትዮጵያዊያኑ ''ድምጻችሁን አሰሙልን በጣም እንግልታችን እየበዛ ነው። ህጻናቱ እየሞቱብን ነው እህት ወንድሞቻችን እየተሰቃኑ ነው ነፍሰጡር ሴቶች እየተሰቃዩ ነው'' ሲሉ ችግራቸውን አስረድተዋል።

''ገንዘባችንን ከፍለን ወደ ሀገር ቤት መመለስ የምንችል ዜጎች በህጋዊ መንገድ እንድንወጣ የኢትዮጵያ መንግስት ህጋዊ መንገዶችን ያመቻችልን'' ሲሉም ጠይቀዋል።

በሳዑዲ አረቢያ የስደተኞች ህግ መቀየሩ ችግሩን አወሳስቦታል ሲሉ በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ በውይይቱ ላይ ገልጸዋል።

ስምንትና ዘጠኝ ዓመት ከህግ ውጪ የሰሩ ሰዎች ወደ 100 ሺ ሪያል የሚጠጋ ካልከፈሉ መውጣት አይችሉም፤ ይህንን የሚከፍሉ ከሆነ ራቁታቸውን ነው የሚወጡት ሲሉ የገለፁት አምባሳሰር ሌንጮ ፥ ምህረት እንዲደረግ በመጠየቁ ባለፈው ሳምንት ምህረት መደረጉን ንጉሱ ማሳወቃቸውን አንስተዋል። ነገር ግን ወከባውና አሰሳው ካላቆመ በስተቀር ዜጎች ኤምባሲ ድረስ መጥተው ሊመዘገቡ እንደማይችሉ አስረድተዋል።

ዜጎችን ወደሃገር የመመለስ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያስገነዘቡት አምባሳደሩ ፥ ''ሴቶችና ህጻናትን ቅድሚያ መስጠት አለብን ይሄ ካልሆነ ሦስት ወር ስድስት ወር ሬሳ በሬሳ ነው የሚሆነው ለዚህ ደግሞ የሚጠየቁት እነሱ ብቻ አይደሉም እኛም ተጠያቂ ነን'' ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#SaudiArabia

በጄዳ የሹሜሲ ዲፖርቴሽን ማዕከል ከገቡ በኃላ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በተለያዩ ሆስፒታሎች ውስጥ ህይወታቸው ያለፈ የኢትዮጵያ ዜጎችን የሚያውቃቸው ቤተሰብ ፣ ዘመድ እና ጎደኞች ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠየቀ።

ከዚህ በታች የሟቾች ስም አስክሬናቸው የሚገኝበት ሆስፒታል የተገለፀ ሲሆን የምታውቋቸው ሰዎች በቢሮ ቁጥር 13 ቀርባችሁ ሪፖርት እንዲያደርጉ በጄዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት አሳውቋል።

- ሂክመት መሀመድ (የአስክሬን መገኛ👉 ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል)
- ከዲጃ ማህመድ (የአስክሬን መገኛ👉ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል)
- ሮዳስ ሙሉ (የአስክሬን መገኛ 👉 ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል)
- ጀማል ከማል (የአስክሬን መገኛ 👉 ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል)
- ቢንያም ምሩፅ ሃጎስ (የአስክሬን መገኛ 👉 ሰግር ሆስፒታል)
- የኢንዲያ ተማም /ህፃን ልጅ/ (የአስክሬን መገኛ 👉 ሰግር ሆስፒታል)
- መሃሪ ኃይሌ (የአስክሬን መገኛ 👉 ንጉስ አብዱላአዚዝ ሆስፒታል)
- ሱልጣን ሙሀመድ (የአስክሬን መገኛ 👉 ንጉስ አብዱላአዚዝ ሆስፒታል)
- በህታ ነጋሲ አፈወርቂ (የአስክሬን መገኛ 👉 ንጉስ አብዱላአዚዝ ሆስፒታል)
- ሰለሞን ሀዱሽ ተካ (የአስክሬን መገኛ 👉 ንጉስ አብዱላአዚዝ ሆስፒታል)

በዚሁ አጋጣሚ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ስራ ዳግም የተጀመረ መሆኑ ቢታወቅም አሁንም ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ያሉ ዜጎች በርካታ በመሆናቸው ልዩ ትኩረት ሊደረግ ይገባል።

@tikvahethiopia
#SaudiArabia

ሃውቲዎች በርካታ የሳዑዲ ከተሞች ላይ ያነጣጠሩ የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃቶች መፈፀማቸውን ገለፁ።

የየመን ሃውቲ ተዋጊዎች ቅዳሜ እለት በርካታ የሳዑዲ ከተሞች 14 የሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮን) ጥቃት መሰንዘራቸውን የሳውዲ አረቢያ መንግስት የዜና ወኪል ዘግቧል።

ጥቃቱ በጅዳ የሚገኘውን የሳዑዲ አራምኮ ተቋም ላይም ያነጣጠረ እንደነበር የተዘገበ ሲሆን በሳዑዲ የሚመራው ጥምረት በየመን በቡድኑ ላይ ባካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ በ13 ኢላማዎች ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ተሰምቷል።

የሃውቲ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሬ ቅዳሜ በቴሌቭዥን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ቡድኑ በጄዳ የሚገኙትን የአራምኮ ማጣሪያዎችን እንዲሁም በሪያድ ፣ጄዳህ ፣አብሃ ፣ጂዛን እና ናጃራን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት አድርሷል።

ሳሬ፥ ጥቃቱ እየተባባሰ ለመጣው በሳዑዲ የሚመራው የአረብ ጥምር ጦር ወረራ እና የመን ለሚፈፀሙ ወንጀሎችና ከበባ ምላሽ ለመስጠት ነው ብለዋል።

ይሁን እንጂ በሳሬ መግለጫ ስህተቶች ነበሩ ይኸውም ፦ በጄዳ የሚገኘው ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተሳሳተ ስም እና ለንጉስ ካሊድ ቤዝ የተሳሳተ ቦታን ጠቅሰዋል፤ ሳሬ ሪያድ ያሉ ሲሆን ነገር ግን ቦታው በስተደቡብ በኩል የሚገኝ ነው።

በሳውዲ አረቢያ የሚመራው ጥምር ጦር በድሮን ጥቃቱ ላይ የሰጠው አስተያየት ባይኖርም የሳውዲ ፕሬስ ድርጅት ቅዳሜ ጥምር ጦሩ በየመን መዲና ሰንዓ እንዲሁም ሰዓዳ እና ማሪብ ግዛቶች በፈፀመው ጥቃት የጦር መሳሪያዎች ማከማቻዎች፣ የአየር መከላከያ ዘዴዎች እና የሰው አልባ አውሮፕላኖች የመገናኛ ዘዴዎች ላይ ጉዳት አድርሷል ብሏል።

@tikvahethiopoa
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hajj1445 ዘንድሮ #ምን_ያህል የእስልምና እምነት ተከታዮች #ሐጅ አደረጉ ? እንደ ሀራሜይን መረጃ ከሆነ ዘንድሮ በ1445 (AH) 1,833,164 (ከ1.8 ሚሊዮን በላይ) የእስልምና እምነት ተከታዮች ከመላው የዓለም ክፍል የሐጅ ጉዞ አድርገዋል። ከአጠቃላዩ የሐጅ መንፈሳዊ ጉዞ ተጓዦች 221,854 የእስልምና እምነት ተከታዮች ከዛው ከሳዑዲ አረቢያ ሲሆኑ 1,611,310 የሚሆኑት ዓለም አቀፍ የሐጅ…
#Hajj1445

የዘንድሮው የሐጅ ስነ ስርዓት ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ዕለት ማጠቃለያውን አግኝቷል።

በሃይማኖታዊ ስርዓቱ ከመላው ዓለም ከ1.8 ሚሊዮን በላይ የእስልምና እምነት ተከታዮች  ተሳትፈዋል።

በሚያሳዝን ሁኔታ ግን በሳዑዲ አረቢያ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

የሚበዙት ከግብፅ የሄዱ ሑጃጆች ሲሆኑ የሌሎችም 9 ሀገራት ዜጎች ከሟቾቹ ውስጥ ይገኙበታል።

እስካሁን ባለው መረጃ 1,126 ሑጃጆች ህይወታቸው አልፏል።

ከኢትዮጵያ ሑጃጆች በሙቀት ህይወታቸው ያለፈ አለ ?

የፌደራል መጅሊስ በሳዑዲ በተፈጠረው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት በኢትዮጵያውያን ሃጃጆች ላይ ጉዳት አልደረሰም ብሏል።

ምንም እንኳን በሙቀቱ ሳቢያ ህይወቱ ያለፈ ባይኖርም በመኪና አደጋ አንድ አባት እንደሞቱ ፤ እዚሁ አዲስ አበባ ኤርፖርት አንድ ሰው እንዲሁም በሳውዲ አረቢያ 3 ኢትዮጵያውያን በህመም ህይወታቸው እንዳለፈ ገልጿል።

በዘንድሮው የሐጅ ስነስርዓት ላይ ከኢትዮጵያ 12,000 ምዕመናን የተሳተፉ ሲሆን ሑጃጆቹ የሐጅ ኢባዳቸውን አገባደው ወደሀገራቸው ለመመለስ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን መጅሊሱ ለ " ሀሩን ሚዲያ " በሰጠው ቃል አሳውቋል።

#Hajj1445 #SaudiArabia #Harun

@tikvahethiopia