TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፌደራል ፖሊስ‼️

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የኢፌዲሪ ህገመንግስት መሰረት በማድረግ የህግ የበላይነት እንዲሰፍን ፤ የዜጎች #ሰላምና ደህንነት #እንዲረጋገጥ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በ2011ዓ/ም የከፍተኛ ትምህርት የመማር ማስተማር ሂደት #በሰለማዊ መንገድ እንዲቀጥል ከወትሮ በተለየ በሁሉም ሀገሪቱ #ዩንቨርሲቲዎች እና #ኮሌጆች በተለያዩ አከባቢዎች ጥብቅ ቁጥጥርና ጥበቃ እያካናወነ ሲሆን የመማርና ማስተማር ሂደትም እንዳይስተጓጎል ከሌሎች ጥምር ኮሚቴዎች ጋር ተቀናጅቶ በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ እየሰራ ይገኛል፡፡

ስለሆነም በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች የተመደባችሁ አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋም በመሄድ #ያለምንም የፀጥታ #ስጋት ትምህርታችሁን መማር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ደህንነታችሁ በተመለከተ በሁሉም ዩንቨርሲቲዎችና አካባቢዎች ከወትሮ በተለየ ጥብቅ ቁጥጥርና ጥበቃ እያደረግን እንደምንገኝ በድጋሜ እናሳውቃለን፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ቦታ ሲሆዱም ሆነ ግቢ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ስጋት እንዳይኖር አስቀድመን ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቂ ዝግጅት በማድረግ እየሰራን እንደምንገኝና ምንም ዓይነት የደህንነት ስጋት እንደሌለ ለተማሪዎችና ለቤተሰቦቻቸው እንገልፃለን፡፡

©የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሩጫው በሰላም ነው የተጠናቀቀው‼️

የኢትዮ ኤርትራ የሰላም የአንድነትና የፍቅር ሩጫ #ያለምንም እንከን በሰላም መጠናቀቁን የሩጫው አስተባባሪ ኮሚቴ ገለጸ፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የተሳተፉበት ሩጫ የሁለቱን ሃገራት ህዝቦች በማስተሳሰር በኩል ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም ተገልጿል፡፡

የሩጫው አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈረ እንዳሉት ሩጫው የኢትዮ ኤርትራ የፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እንዲጎለብት መሰል መርሃ ግብሮች የሚያበረክቱት አስተዋዕኦ ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቴሌብር ኢንጌጅ ምንድነው ?

(ኢትዮ ቴሌኮም)

ኩባንያችን የዲጂታል ሕይወትን በማቅለል እልፍ ጉዳይ በአንድ መተግበሪያ መከወን በሚያስችለው " ቴሌብር ሱፐርአፕ " ደንበኞች ከመገበያየት እና ገንዘብ ከማስተላለፍ ባሻገር መረጃን በነጻ በመለዋወጥ ማህበራዊ ግንኙነታቸውን እና ቢዝነሳቸውን የሚያጠናክሩበት ቴሌብር ኢንጌጅ የተሰኘ አገልግሎት አስጀመረ፡፡ 

አዲሱ ቴሌብር ኢንጌጅ የቢዝነስ እና ግለሰብ ደንበኞች #ያለምንም_ተጨማሪ_የኢንተርኔት_ክፍያ ለተናጠል ወይም ለጋራ ፦
- የጽሁፍ፣
- የፎቶ፣
- ድምጽ፣
- ቪዲዮ እና ፋይሎችን ለማጋራት የሚያስችል ሲሆን ከዚህም ባሻገር ለበዓል ወይም ለተለያዩ ማህበራዊ ሁነቶች የተናጠል ወይም የቡድን መልካም ምኞት መልእክት ከገንዘብ ስጦታ ጋር መላክ የሚያስችላቸውን አዲስ ገጽታ አካቷል፡፡

በተጨማሪም በጭውውቶች ወቅት ገንዘብ ለመጠየቅ፣ ለመላክ እና ለመቀበል፣ ቢል ለማጋራት እንዲሁም ጥቅል ወይም የአየር ሰዓት መግዛትን ጨምሮ በርካታ የዲጂታል አገልግሎቶችን በአንድ መተግበሪያ እንዲያከናውኑ ያስችላል፡፡

ኩባንያችን ለክቡራን ደንበኞቹ አዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አማራጮችን በማስተዋወቅ የቢዝነስ ተሞክሮአቸው እና የዕለት ተዕለት ኑሮአቸው ላይ ተጨማሪ ምቾት እና ቅልጥፍና በመጨመር ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን ሁሉን አቀፍ ጥረት ማድረጉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

ለተጨማሪ ማስፈንጠሪያውን https://bit.ly/3W3291x ይጠቀሙ፡፡

#telebirrEngage
#Ethiotelecom