TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የደህንነት ካሜራዎቹ ስራ ጀመሩ‼️

በአዲስ አበባ ከተማ ከቦሌ እስከ መስቀል አደባባይ ባለው ጎዳና ላይ የተተከሉ #የደህንነት_ካሜራዎች ስራ መጀመራቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ካሜራዎቹ የተተከሉት ከቦሌ ውስጠኛው አደባባይ እስከ መስቀል አደባባይ ባለው መንገድ ግራና ቀኝ በኩል የተተከሉ መሆናቸውን በኮሚሽኑ የአይሲቲ ኢንፍራስትራክቸር ዲቪዥን ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር #አንድነት_ሲሳይ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም በመዲናዋ የተለያዩ ጎዳናዎች ካሜራዎችን የመትከል እቅድ መኖሩን የጠቀሱት ሃላፊው ከቦሌ እስከ መስቀል አደባባይ ያሉት ካሜራዎች ከሶስት ቀናት በፊት ስራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።

የካሜራዎቹ ቀረፃና የቁጥጥር ስራውም ያለምንም መቆራረጥ ሌት ከቀን እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።

የኮሚሽኑ የቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ዳይሬክተር ተወካይ ኮማንደር ሁነኛው አየነው ከዚህ በፊት በመዲናዋ ውስን አካባቢዎች የነበሩ ካሜራዎች ከመንገድ ስራ ጋር ተያይዞ መነሳታቸውን አስታውሰዋል።

ሆኖም አገልግሎቱ ዳግም መጀመሩ አዲስ አበባ የበርካታ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት መቀመጫ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የተጠናከረ ጥበቃ ለማድረግ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

የደህንነት ካሜራ አገልግሎት የብዙ ተቋማትን ቅንጅትና በርካታ መዋለንዋይ የሚፈልግ በመሆኑ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በአንድ ጊዜ ማዳረስ አዳጋች ቢሆንም በቀጣይ ግን በተለይ የኢንዱስትሪ መንደሮች ባሉባቸው ከተሞች ማስፋፋት ያስፈልጋል ብለዋል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia