TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ለሳምንታት ተዘግቶ የቆየው የምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል የኢንተርኔት አገልግሎት በዛሬው ዕለት መስራት ጀምሯል።

#አሰበ
#ሀረማያ
#ድሬዳዋ
#ጅግጅጋ
#ሀረር...እንዲሁም በሁሉም የምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል የምትገኙ ቤተሰቦቻችን እንኳን በደህና መጣችሁ! እንኳን በሰላም ተገናኘን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሶማሌ ክልል⬇️

በቅርቡ በሶማሌ ክልል #ጅግጅጋ ከተማና ሌሎች የክልሉ አከባቢዎች ተከስቶ በነበረው #ግጭት ምክንያት የስራ ገበታቸውን የለቀቁ ከ350 በላይ የጤና ባለሙያዎች ወደ ነበሩበት ለመመለስ የሚያስችል ውይይት በጅግጅጋ ከተማ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚ/ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰሃርላ አብዱላሂ፣ የክልሉ ም/ፕሬዝደንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር የሱፍ መሀመድ፣ የሀይማኖት መሪዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የማህበረሰብ ተወካዮች በተገኙበት ውይይት ተደርጎ የጤና ባለሙያዎች ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ ስምምነት ተደርሷል። ለዚህም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለባለሙያዎችንና የሀይማኖት አባቶችን ምስጋና አቅርቧል።

©ዶክተር አሚር አማን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ሁለት ቀናት በድምሩ 1,506,260 ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ #ጅግጅጋ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ በቁጥጥር ስር የዋለው ኮንትሮባንድ ኬሚካል፣ ስኳር እና የቁም እንስሳት የሚያካትት ነው፡፡ በዚህ መሰረት በእግር እየተነዱ ከሀገር ሊወጡ የነበሩ ግምታዊ ዋጋቸው 112,500 ብር የሆነ ዘጠኝ በሬዎች የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ሌሊት 7፡00 ጅግጅጋ ውስጥ በሚሊሻና በጉምሩክ አባላት ሲያዙ ተጠርጣው ለጊዜው ማምለጡን ነው የተገለፀው፡፡

Via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

የኦሮሚያና ሶማሌ ክሎሎች የህዝብ ለህዝብ መድረክ ነገ በጅግጅጋ ከተማ ይካሔዳል፡፡ ነገ በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ የሚካሔደው የህዝብ ለህዝብ መድረክ የሁለቱን ክልሎች ህዝቦች ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡ የሁለቱን ክልሎች ህዝቦች ግንኙነት የሚያጠናክር ተመሳሳይ መድረክ በአዳማ መካሔዱ የሚታወስ ነው።

Via #OBN
ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶችን እየተቀበለች ነው። #የኦሮሚያ እና #የሶማሌ ክልል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ #ነገ ይካሄዳል።

ፎቶ፦ Mame/TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

በነገው እለት #በጅግጅጋ ለሚደረገው የኦሮሚያ ክልልና የሱማሌ ክልል ህዝቦች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ ላይ ለመሳተፍ በኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሚመራ የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች ቡድን ዛሬ ጅግጅጋ ገብቷል፡፡ ቡድኑ ጅግጅጋ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ የሁለቱ ህዝቦች የወንድማማችነት መድረክ ከዚህ ቀደም በአዳማ ከተማ መደረጉ ይታወሳል፡፡

Via #ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

የኦሮሞና የሱማሌ ህዝቦች የወንድማማችነት የምክክር መድረክ ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ተጀምሯል፡፡ በመድረኩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ መሐመድ ኡመር፣ የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ አባገዳዎች እና የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የሁለቱ ክልል ህዝቦች ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

#የኦሮሞና #የሶማሌ ክልል ህዝቦች ሰላምና አብሮነት ከኢትዮጵያ አልፎ ለምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ሚናው የጎላ በመሆኑ ትስስሩን ወደሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰሩ የሁለቱ ክልል ርዕሰ መስተዳደሮች ተናገሩ። የሁለቱ ክልል ህዝቦች ግንኙነትን መልሶ ለማጎልበት ያለመ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ እየተካሄደ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

"#የሁላችንም የሆነች #ኢትዮጵያን ለመፍጠር ቀን ከሌት እንሰራለን" የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

"ወንድማማችነትን በማጠናከር የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች ለኢትዮጵያ ዋልታና ማገር ለመሆን እንሰራለን" የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሙስጠፌ_መሀመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ_ዩንቨርስቲ

‹‹2012 የሰላምን ምንነት የምናሳይበት እንዲሆን እየሰራን ነው›› - ዶክተር #አብዲ_አህመድ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት
.
.
የ2012 የትምህርት ዘመን በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ብቻ ሳይሆን የሰላምን ምንነት ለማሳየት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገለጸ። በትምህርት ዘመኑ 3ሺ612 አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል መዘጋጀቱም ተጠቁሟል። የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር አብዲ አህመድ ሀሰን እንደተናገሩት፤ የ2011 የትምህርት ዘመን የጎላ ችግር አይታይበት እንጂ ለዩኒቨርሲቲው አመራር፣ መምህራንና አጠቃላይ ሰራተኛው ፈተና ሆኖ አልፏል። ከዚህ ሂደት በመማርም የ2012 የትምህርት ዘመን ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ ሲሆን፤ ተግባሩም ዩኒቨርሲቲው የሰላምን ምንነት የሚያሳይበት፤ ህብረተሰቡም ሰላምን የሚያስተምርበት እንዲሆን ታስቦ እየተሰራ ነው ብለዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia