TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጊዳሚ ከተማ ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው ተገደሉ !

ከትናንት በስቲያ (ቅዳሜ) ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማ በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ከተማ ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ ይህን መሰሉ ግድያ ነዋሪ የዕለት ተዕለት ሰቆቃ ከሆነ ሰነባብቷል።

"ቅዳሜ ምሽት ተኩስ ነበር። በዚያ ተኩስ ሳቢያ ነው ሁለቱ ነዋሪዎች የተገደሉት። እነሱን የገደለው አካል የቱ እንደሆነ ደግሞ መለየት አልቻልንም" በማለት ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን የማንጠቅስ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ተናግረዋል።

ከተገደሉት ሁለቱ ግለሰቦች አንዱ የጊዳሚ ከተማ ቀበሌ 01 ነዋሪ የነበሩት አቶ ነጋሽ ፉፋ ሲሆኑ ሌላኛው ሟች ደግሞ፤ "ከቄለም ገጠራማ ስፍራ የመጡ ናቸው፤ ማንነታቸውን አለየንም" በማለት የከተማዋ ነዋሪ ተናግረዋል።

የጊዳሚ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ #ደሳለኝ_ቱጁባ በበኩላቸው ሟቾቹ አቶ ነጋሽ ፉፋ እና አቶ ያዕቆብ ቶላ እንደሚባሉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

"አቶ ነጋሽ ፉፋ ቤት አቅራቢያ በቅኝት ሥራ ላይ በነበሩ የልዩ ፖሊስ እና የሃገር መከላከያ አባላት ላይ ቦንብ ተወረወረ፤ #ተኩስም ተከፈተ" የሚሉት የወረዳው አስተዳዳሪ፤ ቦንምቡን የወረወረው እና ተኩስ የከፈተው አካል አሁን ድረስ እንደማይታወቅ ጠቅሰው፤ ድንገተኛ ጥቃቱ የተሰነዘረው ግን በመንግሥት ኃይሎች ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

#ቢቢሲ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-16-5