TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ከወሊሶ_ቤተሰቦች

"በወሊሶ ከተማ በነገው ዕለት የሀምሌ 22/2011 ዓ/ም የአረንጓዴ አሻራን የማስቀመጥ ቀንን በማስመልከት በከተማዋ በተመረጡ ቦታዎች #ከ50 ሺህ በላይ ችግኞች እንደሚተከሉና ህብረተሰቡም #በንቃት እንዲሳተፍ የከተማው አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ጥሪውን እያስተላለፈ ይገኛል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ደቡብ

በ2011 ዓ.ም. በደቡብ ክልል በነበረ አለመረጋጋት በጉራጌ፣ ሲዳማ፣ ከፋ፣ ጎፋና በጌድዖ #ከ50 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ በመዘጋታቸው ከ40 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጣቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተሰማ ዲማ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። «አሁንም ሎካ ብላቴ ዙሪያ ወረዳና ምሥራቅ አርሲ ድንበር አካባቢ ላይ ግጭቶች አሉ፤ ወደ 7 የሚጠጉ የተቃጠሉ ትምህርት ቤቶች አሉ። እዛ አካባቢ አሁንም ተመልሰን ለማስተማር እና የማካካሻ ፕሮግራም ለመስጠት እንቸገራለን የሚሉ ወረዳዎች አሉ» ብለዋል።

Via #DW
@tsegawolde @tikvahethiopia
#MoE

106 ሺህ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ የትምህርት ፕሮግራም ተካተዋል፡፡

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው #ከ50_በመቶ በታች ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለአራት ወራት ያህል በሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ይሳተፋሉ፡፡

#Remedial ፕሮግራሙ ከአ/አ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ውጪ ባሉ ሁሉም የመንግስት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች እና ፕሮፌሰሮች ኮሚቴ በማዋቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉት የትምህርት አይነት ይዘቶችን መለየቱን በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራሙ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ እንግሊዘኛ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና ሂሳብ የትምህርት አይነቶችን የሚወስዱ ሲሆን፤ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ እንግሊዘኛ፣ ማህበራዊ ሳይንስና ሂሳብ ትምህርት አይነቶችን እንደሚወስዱ መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ይዘቶቹን መሰረት አድርጎ በተቋማት የሚዘጋጅ (ከ30 በመቶ) እና በማዕከል የሚዘጋጅ (ከ70 በመቶ) የሚያዝ ፈተና በመፈተን በድምሩ 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ የሚያገኙ ተማሪዎች መደበኛ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመንግስት እና በግል ዩኒቨርሲቲዎች መቀጠል ይችላሉ ብለዋል፡፡ #EPA

More : @tikvahuniversity