TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #ETHIOPIA " ለኢትዮጵያ አንድነት ፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ቁርጠኛ ነን " - አሜሪካ አሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛዋ አምባሳደር ማይክ ሀመር ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች፣ ከአፍሪካ ህብረት እና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር #ውጤታማ ውይይት አድርገዋል ስትል አሳወቀች። ሀገሪቱ ይህን ያሳወቀችው ዛሬ አዲስ…
አምባሳደር ማይክ ሐመር ምን አሉ ?

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ ከነበራቸው የ10 ቀናት ቆይታ በኃላ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም የተለያዩ ሃሳቦችን አንስተዋል።

ኤርትራን በተመለከተ ፦

" የኤርትራ ሠራዊት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ለጦርነት መሰለፉ ያሳስበናል፤ እንቃወማለንም። የትኛውም የውጭ ተዋናይ የኢትዮጵያን የግዛት ሉዓላዊነት ማክበር ጦርነቱ እንዳይቀጣጠል ያግዛል። ስለዚህ ጉዳይም #ከአስመራ ጋር ቀጥታ የምንወያይ ነው የሚሆነው። ጦርነቱ በኢትዮጵያ የትግራዋይ፣ አማራ እና አፋር ህዝብን ሰቆቃ ያበዛል። ይባስ ብሎ የኤርትራ ሠራዊት በዚህ ላይ መሳተፍ ሌላኛውን አስከፊ ሁኔታ እንዳያስከትል እንሰጋለን። "

የጦርነቱን ዘላቂ መፍትሄ በተመለከተ ፦

" የጦርነቱን #ዘላቂ የሆነ መፍትሄ መምጣት ያለበት ከኢትዮጵያውያን ከራቸው ነው። ሀገራቸው እኮ ነው። በዚህ ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ ሚና ይህን ከባድ ጊዜ እንዲያልፉ በጠንካራ ዲፕሎማሲ ማገዝ ነው። ተስፋ የምናደርገውም ተፋላሚ ኃይላቱ ከአውዳሚ ጦርነት ወጥተው ተስፋና ብልጽግና ወደ ሚያመጣው ሰላም ይመጣሉ የሚለውን ነው። "

ማዕቀብን በተመለከተ ፦

" ቀዳሚው ትኩረታችን ዲፕሎማሲ ነው። ተፋላሚዎቹ ወደ ሰላም እንዲመጡ አሜሪካ የተለያዩ አማራጮችን ትመለከታለች፤ ለጊዜው ግን ዋነኛው ትኩረታችን በዲፕሎማሲ አብዝተን መስራት ነው። እንደ የአውሮፓ ህብረት እና የአፍሪካ ህብረት ያሉ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጋር እየሠራን ያለነውም ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ነው። "

መተማመንን በተመለከተ ፦

" የተፋላሚዎች ቁልፍ ልዩነት እርስ በርስ መተማመም አለመዳበር ነው። ተፋላሚዎችን ወደ አንድ ለማምጣት ዋናውና መሰረታዊው ጉዳይ መተማመንን በሂደት መገንባት ነው። በጦርነቱ በተሰቃየው ህዝብ መካከልም ይህን የመተማመን ስሜት ማስረጽ ያስፈልጋል። ያን መተማመን የሚያመጡ ሂደቶችት ላይ ነን አሁን። "

የኢትዮጵያን አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነትን በተመለከተ ፦

" አሜሪካ የኢትዮጵያን አንድነት፣ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ታከብራለች፤ ኢትዮጵያውያንን ሚጠቅም ዘላቂ ሰላም እንዲኖር ነው የምትሻው "

ያንብቡ : https://telegra.ph/USA-09-20-2