TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አሳዛኝ_ዜና! 5 የሜቆዶንያ የአእምሮ መርጃ ማዕከል ህመምተኞች በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው አለፈ። ዛሬ ጠዋት የሜቆዶንያ ማዕከል በሚገኘው መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ፀበል ውስጥ ሲጠመቁ የነበሩ 5 ፀበልተኞቸ ደራሽ ውሃ መጥቶ ይዟቸው በመሄድ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሎል፡፡

ነብስ ይማር!

ምንጭ፦ ተሻገር ጣሰው
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና⬇️

በሶማሊያ የፑንትላንድ የንግድ ከተማ በሆነችው ቦሳሶ ውስጥ ሦስት #ኢትዮጵያዊያን #በአይሲስ ታጣቂዎች #ሲገደሉ ቢያንስ አንድ መቁሰሉ ተዘገበ።

ስለጥቃቱ በቀዳሚነት የወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት ታጣቂዎቹ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ይኖሩበታል በሚባለው ሳንቶስ ተብሎ በሚጣራው የከተማዋ ክፍል ውስጥ ባገኟቸው አራት ኢትዮጵያዊያን ላይ #ተኩስ ከፍተው ነው ጥቃቱን የፈፀሙት።

አንድ ስማቸውን ያልጠቀሱ የአካባቢው ባለስልጣን ኢትዮጵያዊያኑ በተፈፀመባቸው ጥቃት መገደላቸውንና መቁሰላቸውን ለቢቢሲ ሲያረጋግጡ፤ አፍቃሬ አይኤስ የሆነ ቡድንም በትዊተር ገጹ ላይ ስለጥቃቱ አስፍሯል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ ሃገራት የኤደን ባህረ ሰላጤን በትናንሽ ጀልባዎች በማቋረጥ ወደ የመንና የመካከለኛው ምሥራቅ ሃገራት በህገ ወጥ መንገድ ለመሻገር የሚፈልጉ ስደተኞች #የቦሳሶን የባህር በር ይጠቀማሉ።

በአካባቢውም በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እንደሚገኙ ተገልጿል።

እነዚህ በጥቃቱ የሞቱትና የቆሰሉት ኢትዮጵያዊያንም በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች አማካይነት ባህሩን ተሻግረው በጦርነት ወደ የምትታመሰው #የመን ለመጓዝ በቦታው የነበሩ ስደተኞች እንደሆኑ ይታመናል።

አይሲስ ከቅርብ ወራት ወዲህ በጉልህ የሚታዩ በርካታ ጥቃቶችን በሶማሊያ ውስጥ እየፈፀመ ሲሆን በተለይ ደግሞ በፑንት ላንድ ግዛት ውስጥ የአይኤስ ቡደን ከሌሎች አካባቢዎች በበለጠ ሰፊ እንቅስቃሴ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል።

ፑንትላንድ በሰሜን ሶማሊያ የምትገኝ ከፊል ራስ ገዝ የሆነች ግዛት ናት።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና በምሥራቅ አፍሪካ ሃገራት ውስጥ ስኬታማውና በኢትዮጵያ ገበያም ለመሳተፍ ፍላጎት ያሳየው ግዙፉ የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ቦብ ኮሊሞር ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ድርጅታቸው አስታደቀ። ሳፋሪኮም የዋና ሥራ አስፈጻሚውን ዜና እረፍት ይፋ ባደረገበት መግለጫው ላይ እንዳመለከተው፤ ቦብ ኮሊሞር በ61 ዓመት እድሜያቸው በካንሰር ምክንያት ዛሬ ጠዋት ቤታቸው ውስጥ ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል።

Via #BBC
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

በሱዳን በተካሂደ የተቃውሞ ሰልፍ የሰባት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ከ180 በላይ በሚሆኑት ላይ ደግሞ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የሀገሪቱ ዜና አገልግሎት አስታውቋል፡፡ ከባለፈው ሚያዝያ ወር ጀምሮ በኃይል ከሥልጣን የወረዱት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ዘመን ወዲህ ሱዳን መረጋጋት ተስኗታል። ትናንት በመዲናዋ በተካሄደ ሰልፍም በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፤ ወታደራዊ የሽግግር መንግሥቱ ለጥቃቱ ራሳቸውን ‹የነፃነትና የለውጥ ኃይል› ብለው የሚጠሩ ብድኖችን እና ሰርጎ ገቦችን ወንጅሏል፡፡ ተኩስ ከፍተዋል ያላቸውን ሰርጎ ገቦች ማሠሩንም አስታውቋል፡፡

Via ቢቢሲ
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

የአስራ ስምንት አመት እድሜ ያለው ሰለሞን ተካ እስራኤል ውስጥ ሐይፋ በሚባለው አካባቢ ፖሊስ በጥይት ደብድቦ የገደለው ሲሆን በዛሬው ዕለትም ስርአተ ቀብሩ እንደሚፈፀም ጀሩሳሌም ፖስት ዘግቧል።

በትናንትናው እለት በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላውያን አሟሟቱን በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።

ሰልፈኞቹ በፖሊሶች ላይ ድንጋይ በመወርወርና እሳት በማቀጣጠል ተቃውሟቸውን የገለፁ ሲሆን በዚህም ሶስት ፖሊሶች ተጎድተዋል። ፖሊስ በበኩሉ አፀፋዊ ምላሽ የሰጠ ሲሆን በዚህ ቁጥራቸው ትንሽ የማይባሉ ሰልፈኞች ተጎድተዋል።

ሰለሞንን ገደለ የተባለው ፖሊስ በነፍስ ግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር እንደዋለም ሀሬትዝ ዘግቧል።

Via #bbc
🗞ቀን ሰኔ 25/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

በህንድ ሙምባይ የወሰን ግንብ ተደርምሶ የ13 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ አደጋው የደረሰው በህንድ የንግድ ከተማ ሙምባይ በጣለ ከባድ ዝናብ ነው፤ በዚህም ቢያንስ የ13 ሰዎች ሕይወት እንዳለፈና መኖሪያዎችም እንደፈራረሱ ታውቋል፡፡ ከአደጋው በርካታ ሰዎችን ማትረፍ ተችሏል፤ የነፍስ አድን ሠራተኞች ሰዎችን ከጉዳት የማትረፍ ሥራቸውን እንደቀጠሉም ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡ በአደጋው የባቡር እንቅስቃሴ እና የአየር በረራ ተቋርጧል፡፡ ሀገሪቱም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ እንደምትገደድ ባለስልጣናቱ እየገለጹ ነው፡፡

Via ሲ ጂ ቲ ኤን
🗞ቀን ሰኔ 25/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

ዛሬ ማለዳ በሊቢያ የስደተኞች እስር ቤት ላይ በተፈጸመ የአየር ድብደባ በትንሹ 44 ሰዎች #መገደላቸውን የአገሪቱ መንግሥት አስታወቀ። በትሪፖሊ ከተማ ታጁራ በተባለ አካባቢ በሚገኘው የስደተኞች እስር ቤት ላይ ባነጣጠረው የአየር ድብደባ 130 በላይ ስደተኞች መቁሰላቸውን በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈው የሊቢያ መንግሥት የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በትንሹ 6,000 #ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያን፣ ሶማሌያውያን፣ ሱዳናውያን እና የሌሎች የአፍሪካ አገራት ዜጎች በሊቢያ ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር በሚገኙት እስር ቤቶች ታጉረው ይገኛሉ። አብዛኞቹ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ የተያዙት የአውሮፓ ኅብረት በገንዘብ በሚደግፋቸው እና ባሰለጠናቸው የባሕር በር ጠባቂዎች ነው።

Via #DW
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

በሶማሊያ በአንድ ሆቴል ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ታዋቂ ጋዜጠኛን ጨምሮ 26 ሰዎች ሞቱ። በደቡባዊ ሶማሊያ በተሰነዘረ ጥቃት ከሞቱት 26 ሰዎች መካከል ታዋቂ ጋዜጠኛ ፣በርካታ የውጪ ዜጎች እንደሚገኙበት ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከጥቃት አድራሾቹ መካከል አንድ አጥፍቶ ጠፊ ፈንጂዎችን የጫነ ተሸከርካሪ በኪስማዩ ወደብ ወደ ሚገኘው አሳሴይ ሆቴል በሃይል ጭኖ የገባ ሲሆን ሌላ ታጣቂም ወደ ህንፃው በመግባት ጉዳት አድርሰዋል፡፡

የ43 አመቷ ጋዜጠኛ ሁዳን ናላሂ እና ባለቤቷ ፋሪድ ከሟቾቹ መካከል ይገኙበታል፡፡ አልሻባብ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን እኤአ በ2012 ከኪስማዩ ተገዶ ከወጣ በኋላ የፈፀመው አስከፊ ጥቃት ተብሏል፡፡

የሃገሪቱ ባለስልጣናት እንዳሉት የአካባቢው ፖለቲከኞች ፣ሶስት ኬንያውያን፣ሶስት ታንዛኒያውያን ፣ሁለት አሜሪካኖችና አንድ ብሪታኒያዊ በጥቃቱ ህይወታቸው አልፏል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

በሶሪያ የአማፂያን ይዞታ በሆነ በገበያ ቦታ በተፈፀመ የአየር ጥቃት በትንሹ የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ የአየር ድብደባው በሰሜን ሶሪያ ኢድልብ ግዛት ሰዎች በሚበዙበት የገበያ ቦታ በተፈፀመው በዚህ ጥቃት በትንሹ 16 ሰዎች ሲገደሉ 30 ያህል መቁሰላቸው ተነግሯል፡፡

የአየር ጥቃቱ በሶሪያ ወይንም በሩሲያ የጦር አውሮፕኖች እንደተካሄደ የሶሪያ ተቃዋሚ አክቲቪስቶች ገልጸዋል ነው የተባለው፡፡ በአየር ጥቃቱ ከተማዋ በጭስ ታፍና የነበር እና የጥቃቱ ሰለባዎች የእርዳታ ጥሪ ሲያሰሙ እንደነበረ የአይን እማኖች ተናግረዋል፡፡

የኢድልብ ግዛት በተቃዋሚዎች ቁጥጥር ስር ሲሆን፣ በሩሲያ የሚደገፈው የበሻር አል አላሳድ መንግስት ተደጋጋሚ የአየር ጥቃት የሚፈጽምበት እንደሆነ ዘገባው ያስረዳል፡፡

የአላሳድ መንግስት ይህን ጥቃት ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር ከጀመረ ጊዜ አንስቶ ከ2ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውን እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውም ይነገራል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

ሶማልያ ዋና ከተማ #ሞቃዲሾ ውስጥ ዛሬ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ፣ በትንሹ 17 ሰዎች #መሞታቸውን የሆስፒታል ምንጮችን ጠቅሶ ቪኦኤ ዘገበ። የሞቃዲሾ ትልቁ ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶ/ር ሞሓመድ ዩሱፍ እንደገለፁት፣ ሌሎች 28 ቁስለኞች ሆስፒታል ገብተዋል። አደጋው የደረሰው አንድ ተጠርጣሪ አጥፍቶ ጠፊ፣ ይጓዝባት የነበረችውን ተሽከርካሪ፣ ሕዝብ በሚበዛበት የሞቃዲሾ አውራ-ጎዳና መጋጠሚያ ላይ በማፈንዳቱ እንደሆነም ተገልጿል። ለፍንዳታው አል-ሻባብ ኃላፊነት መውሰዱንም አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሜ ቱሉ ጅዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ዳሎ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል።

አደጋው የደረሰውም ከሻሸመኔ ወደ ቡታጂራ በማቅናት የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሰበታ ወደ ሻሸመኔ ለቀስተኞችን ይዞ ይጓዝ ከነበረ ሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ ነው ተብሏል።

በተከሰተው አደጋም የስድስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን የወረዳው ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሳጅን አህመድ ቃለቶ ተናግረዋል። በአደጋው ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በባቱ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ተገልጿል። የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ሳጅን አህመድ ጠቁመዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

በጅማ ዞን ኦሞናዳ ወረዳ በጊቤ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ላይ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ባህላዊ ጀልባ መስጠሟ ተሰማ። ከጣውላ የተሰራችው ጀልባ ከቀኑ 5 ስአት ከ30 አካባቢ ወደ አሰንዳቦ ገበያ የሚመጡ 18 ሰዎችን አሳፍራ በመጓዝ ላይ እያለች ተሰብራ መስጠሟን ነው የወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፉአድ ከሊፋ የተናገሩት። አደጋው እንደተከሰተም የወረዳው አስተዳደር አካላት፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ጠላቂ ዋናተኞች ደርሰው የ13 ሰዎችን ህይወት ማትረፍ ተችሏል ብለዋል።

ቀሪዎቹ 5 ሰዎች ግን እስካሁን አልተገኙም፤ ፍለጋውም መቀጠሉ ነው የተነገረው።የጀልባዋ ቀዛፊም በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። አደጋው የደረሰባቸው የጀልባዋ ተሳፋሪዎች ከሰኮሩ እና ኦሞናዳ ወረዳ ወደ አሰንዳቦ ገበያ ሲያመሩ የነበሩ ናቸው የተባለ ሲሆን÷ ህብረተሰቡ ደህንነታቸው አስጊ በሆኑ ጀልባዎች ከመጓዝ በመቆጠብ ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia