TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 5 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,047 ላቦራቶሪ ምርመራ አምስት (5) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ አርባ አምስት (145) ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ75 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ #የሌላቸው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት በመጣራት ላይ ያለ (በጤና ተቋም ተኝተው ከሚታከሙ ህሙማን ከተወሰደ ናሙና የተገኘ)

ታማሚ 2 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ የመኖሪያ ቦታ አፋር ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 3 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ የመኖሪያ ቦታ አፋር ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 4 - የ8 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #ያላት

ታማሚ 5 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊት የመኖሪያ ቦታ ኦሮሚያ #ባቱ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #ያላት

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት 16 ሰዎች (15 ከአዲስ አበባ እና 1 ከአማራ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና አንድ (91) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኦሮሚያ ክልል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ 308 ሲሆን ከእነዚህ መካከል ነው ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ36 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሰንዳፋ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት #በመጣራት ላይ ነው።

ታማሚ 2 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊት የሱሉልታ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላት ግንኙነት #በመጣራት ላይ ነው።

ታማሚ 3 - የ23 ዓመት ኢትዮጵያዊት የቡራዩ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት #ያላት

Via @tikvahethAFAANOROMOO (Biiroo Fayyaa Oromiyaa)

#TikvahEthiopia
@tikvhhethiopiaBot @tikvahethiopia