TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ /የትምህርት ሚኒስትር/፦

•አዲሱ የትምህርት እና ስልጠና ፍኖተ ካርታ የፌደራል የስራ ቋንቋን ማስተማር የሚለው ምክረ ሀሳብ እንጂ #አስገዳጅ ህግ አይደለም።

•ፍኖተ ካርታው ከ1ኛ ክፍል እስከ 8ኛ ክፍል በአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት እንዲሰጥ #የሚፈቅድ ነው።

•የፌደራል የስራ ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንዲሰጥ በፍኖተ ካርታው የተመለከተው ምክረ ሀሳብ ነው። ይሁን እንጂ ይህ #በክልሎች ስልጣን የሚወሰን እንጂ ፍኖተ ካርታው ለትግበራዉ #አያስገድድም

•አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ምክረ ሀሳብ መሰረት ቋንቋንዎችን ይበልጥ #የሚያሳድግ እና የዜጎችን ተግባቦት ይበልጥ የሚያሳልጥ ነው።
 
•የትምህርት እና ስልጠና ፍኖተ ካርታው ኢትዮጵያ የምትመራበትን የፌደራሊዝም ስርአት በምንም መንገድ አያፈርስም፤ ይህንን የማድረግ አቅመም የለውም።

•በሁሉም ትምህርት ቤቶች ቢያንስ ለ1 ዓመት የቅድመ መደበኛ ትምህርት እንዲሰጥ #አስገዳጅ መሆኑ ፍኖተ ካርታውን ከዚህ ቀደሙ ልዩ ያደርገዋል።
 
•አዲሱ ፍኖተ ካርታ የተሟላ የትምህርት ስርአትን ይከተላል፥ እንደ ጆኦግራፊ እና ታሪክ ያሉ የትምህርት አይነቶች በሀገር በቀል እውቀት እንዲቃኙ ያደርጋል።

•የትምህርት እና ስልጠና ፍኖተ ካርታው ሊተገበር የሚችለው የኢትዮጵያ ህዝቦች ሲያምኑበት ብቻ ነው።

#FBC #TIKVAH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስገዳጅ በሆነ መልኩ የትምህርት ማስረጃዎች ህጋዊነት ሊጣራና ሊረጋገጥ ነው !

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ በማንኛውም የትምህርት መስክ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው የትምህርት ማስረጃቸውን ህጋዊነት ሳያረጋግጡ በተለያዩ የስራ ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙ ምሩቃኖች #አስገዳጅ በሆነ መልኩ የትምህርት ማስረጃቸው ህጋዊነት እንዲጣራ እና እንዲረጋገጥ ለማድረግ ጉዳዩ ይመለከታቸው ካላቸው አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ዛሬ አሳውቋል።

- ቀጣሪ እና የሙያ ፍቃድ የሚሰጡ አካላት
- ወላጆች
- ተማሪዎች
- የሚመለከታቸው ሁሉ ህገወጥ የትምህርት ማስረጃን በመከላከል ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን ይወጡ ሲል ኤጀንሲው በጥብቅ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ በአዲሱ ረቂቅ የትምህርት እና ጥናት ፖሊሲ ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ከፍል የሚሰጥ ትምህርት #ነፃ እና #አስገዳጅ እንደሚሆን አስታውቋል።

በሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሸዋረገድ ለኢቢሲ በሰጡት ቃል " በአዲሱ የትምህርት ፍኖታ ካርታ ግኝት መሰረት ዜጎች ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል በግዴታ እንዲማሩ ለማስቻልና የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን የተሳለጠ ለማድረግ አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ ተግባራዊ ይደረጋል " ብለዋል።

ፍኖተ ካርታውን ለማዘጋጀት ሲሞከር የትምህርት ዘርፉ ያለበትን ሁኔታ ሊያሳይ የሚያስችል ጥናት መደረጉን ገልፀው መንግስት ለትምህርት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአዲስ መልክ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ገብቷል ሲሉ አስረድተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/MoE-08-16 (ኢቢሲ)

@tikvahethiopia