TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር #በየነ_ጴጥሮስ የተካተቱበት አዲስ ቦርድ ተሰየመለት።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ዘጠኝ አባላትን ያቀፈ የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ተሰይሟል።

በዚህም መሰረት፦

1. ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከአ/አ ዩኒቨርሲቲ

2. ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ከአ/አ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ

3. ዶ/ር ኢ/ር ብርሀኑ አሰፋ ከአ/አ ዩኒቨርሲቲ

4. ዶ/ር ታቦር ገ/መድህን ከአ/አ ትምህርት ቢሮ

5. ዶ/ር ፍሬህይወት ገ/ህይወት ከ አ/አ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ

6. ዶ/ር ቶላ በሪሶ ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ

7. ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ ከአ/አ ጤና ቢሮ

8. ወ/ሮ መስከረም ታምሩ ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር

9. አቶ ዮሀንስ ምትኩ ከአ/አ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ሆነዋል።

ዶ/ር ፍሬህይወት ገ/ህይወት የቦርዱ #ሰብሳቢ እና ዶ/ር ኢ/ር ብርሀኑ አሰፋ ም/ ሰብሳቢ ሆነው ተሰይመዋል።

ምንጭ ፦የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኮ/ሌ በዛብህ ጉዳይ...‼️

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

"ኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስን ሰኔ ላይ ኤርትራ ውስጥ በአካል አግኝቻቸዋለሁ። በመጪው ሰኔ ላይ እንደሚፈቱ መረጃ አለኝ" -- ኢንጅነር #ታደሰ

"እኔ ምንም መረጃ የለኝም። በግሌ የተሻለ (more powerful) የሆኑ መንገዶችን ሄጄ #ማረጋገጫ ያጣሁበት ጉዳይ ነው"-- ፕ/ር #በየነ_ጴጥሮስ
.
.
ኢንጅነር ታደሰ ይባላሉ። ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ወደ ኤርትራ ተጉዘው እንደነበር እና በቆይታቸው ወቅትም በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ወቅት የሚያበሩት ጀት ተመትቶ የተማረኩትን ኢትዮጵያዊውን ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስን እንዳገኟቸው ለጋዜጠኛ #አልያስ_መሰረት ተናግረዋል፤ አክለውም "በአሁን ሰአት እንደ ሌሎች የጦር ምርኮኞች በቀይ መስቀል ስር ይገኛሉ። እኔም እዛ አግኝቻቸዋለሁ። ትንሽ ከእድሜ መግፋት ውጪ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ። ሰኔ ወር ሲመጣ እንደሚፈቱ መረጃ አለኝ። ዝርዝሩን የመንግስት ሰዎች ያውቃሉ" ብለዋል።

የኮ/ሌ በዛብህ ጴጥሮስ ታላቅ ወንድም ወደሆኑት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ስለጉዳዩ በሰጡት ምላሽ፦ "እኛ ይህ መረጃ የለንም። እኚህ ያልካቸው ግለሰብ እንዴት access ሊኖራቸው እንደቻለ አላውቅም። በግሌ የተሻለ (more powerful) የሆኑ መንገዶችን ሄጄ ማረጋገጫ ያጣሁበት ጉዳይ ነው። ወንድሜ በህይወት አለ ወይስ የለም የሚለውን ለማረጋገጥ እንኳን ካደረግነው ጥረት አንፃር ሲታይ የዚህ ሰውዬ መረጃ በጣም extreme ነው። በኤርትራ በኩል ያለው ሁኔታ ሲጠቃለል በኮሎኔል በዛብህ ዙርያ መነጋገር አንፈልግም የሚል ነው። ከዚያም አልፎ ጉዳዩን sensitive አርጎ መናደድ አለ። እኛን አትጠይቁን አይነት ነገር ነው ያየነው። በህይወት ተይዞ የአስመራ መንገዶች ላይ parade የተደረገ ሰው ነው። የኛ አቋም ህይወቱ አልፏል ከተባለ ታውቃላችሁ እና አካሉ የት ነው እያልን ነው። ግን ይህንን ጉዳይ መወያየት አይፈልጉም። ከኢትዮጵያ መንግስት ወገን ደሞ አሁን የተጀመረውን ንግግር ያበላሽብናል የሚል ነገር አለ። ለማንኛውም ያልካቸውን ሰውዬ አገናኘኝ። ይህ ለኛ ትልቅ development ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“አማራ፣ ኦሮሞ... እንዲህ በሚል የሚደራጁ ፓርቲዎች የርዕዮተ ዓለም ስብሰብ ሳይሆኑ ብሶት፤ ቂም በቀልና ምሬት የወለዳቸው ፓርቲዎች ናቸው።” ፕሮፌሰር #በየነ_ጴጥሮስ
.
.
- “የኢትዮጵያ ፖለቲካ መቼም ተቃንቶ አያውቅም። ምክንያቱም መተማመን የለም። አንዱ ሌላኛውን በበላይነት መግዛት ነው የሚፈልገው”

- “አሁንም የጎበዝ አለቆች በአገሪቱ ዴሞክራሲ እናመጣለን ብለው ከዲሞክራሲ ጋር የማይገናኝ ፍጹማዊ አምባገነን አስተዳደር ጫኑብን።”

- “በኢትዮጵያ ያለው ፖለቲከኛ፤ ጠባብና የተደበቀ አጀንዳ ያለው ነው”

- “ዶ/ር ዐቢይ ከዚህ በፊት ታፍኖ የነበረው ህዝብ ትንሽ ይተንፍስ ነው የሚሉት፤ መተንፈሱ ግን ወደ ጋጠ-ወጥነት ተሻገረ።”

- “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይዘው የመጡት ጉዳይ፤ ትንታኔ ለየት ያለ አቀራረብ ነው። ህብረተሰቡ ተስፋ እንዲያድርበት አድርጓል።”

- “ኢህአዴግ ቀደም ብሎ ቢዋሀድ ኖሮ ህውሓት አኩርፎ ጠርዝ ላይ አይሆንም ነበር።”

- “ኢህአዴጎች ፍቱን መድሃኒት ብለው ያዘዙት መርዝ አሁን ላይ ለመሰብሰብ አስቸጋሪ ሆኗል።”

- “በአዲስ የፖለቲካ ፍላጎት አዲስ አበባ ፊንፊኔ ነው፤ በረራ ነው እያሉ ወዲያና ወዲህ የሚላገው ነገር ቅንነት የሌለው ክርክር ነው።”

Via አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia