TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሞያሌ‼️

ኢትዮጵያን ከኬንያ የሚያዋስነዉን የሞያሌ ከተማን ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ ሲያብጥ የነበረዉ ግጭት ከትናንት ጀምሮ #ጋብ ማለቱን የዞኑ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

በገሪ (ሶማሌ) እና በቦረና (ኦሮሞ) ታጣቂዎች መካከል ካለፈዉ ዕሮብ ጀምሮ ዳግም ባገረሸዉ ግጭት ቢያንስ 41 ሰዎች ተገድለዋል። ከ84 ሺሕ በላይ ሕዝብ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሏል።

የቦረና ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ #ጴጥሮስ_ዋቆ ዛሬ ለDW እንደነገሩት ትናንት የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር ጣልቃ ከገባ ወዲሕ በከተማይቱ አንፃራዊ ሠላም ሰፍኗል። መደብሮች፣ አገልግሎት መስጪያ ተቋማት እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች ዛሬም ዝግ ናቸዉ። መስተዳድራቸዉ ለተፈናቃዩ ሕዝብ አስቸኳይ ርዳታ ለማከፋፈል እየጣረ ነዉ። አብዛኛዉ ተፈናቃይ ድሬ፣ሜጋ፤ሚዮ እና ሠርባ በተባሉት የሞያሌ አጎራባች ከተሞች እና ወረዳዎች መጠለሉን ምክትል አስተዳዳሪዉ ገልጠዋል።

ግጭቱ በሰዉ ሕይወት እና አካል ላይ ካደረሰዉ ጥፋት በተጨማሪ የሞያሌ ሆስፒታልን ጨምሮ ግምቱ በዉል ያልታወቀ ንብረት አዉድሟል።

የሞያሌ ከተማን ለመቆጣጠር በተቀናቃኝ ጎሳ ታጣቂዎች መካከል ባለፉት ሁለት ዓመታት በተደረገዉ ግጭት በመቶ የሚቆጠር ሕዝብ ተገድሏል። በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ወደ ኬንያ ተሰድዶም ነበር።

ሰሞኑን እንዳዲስ ያገረሸዉ ግጭት ትክክለኛ መንስኤ እስካሁን በዉል አልታወቀም።ታዛቢዎች ግን ከዚሕ ቀደም የነበረዉ ግጭት ሁነኛ መፍትሔ ባለማግኘቱ የቀጠለ ነዉ ይላሉ።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia