TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቡራዩ⬇️

በዛሬው እለት ቡራዩ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ አከባቢዎች ወደ ሰላምና #መረጋጋታቸው ተመልሰዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሙዪኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በሰጡት መግለጫ፥ ችግሩን በመፍጠር ህዝብን #ለአደጋ በማጋለጥ የፖለቲካ አላማቸውን ከግብ ለማድረስ ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ ከአዲስ አበባ ጀምሮ የተንቀሳቀሱ ካላት መኖራቸውን አስታውቀዋል።

የዚህ ጥፋት ሀይል አካል የሆነ 99 አባላት ካለው ቡድን ውስጥ ስድስት ሰዎች የጦር መሳሪያ ማለትም፥ 3 ክላሽ እና 8 ሽጉጥ ሁለት መኪና፣ የባንክ እንዲሁም ደብተር እና የቡራዩ ከተማ መሬት አስተዳደር #ሀሰተኛ ማህተም ይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ያስታወቁት።

የሀሰት ገንዘብን ጨምሮ መጠኑ ከፍ ያለ ገንዘብ መያዙን እና በተጨማሪም በተያዙት ሰዎች የባንክ ሂሳብ ውስጥ 8 ሚሊየን ብር ተገኝቷል ብለዋል።

በዛሬው ዕለትም የቀሩትን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ እየተከታተለ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ከህብረተሰቡ ጋር በመወያየት እስካሁን ከ300 በላይ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው አንዲመለሱ ማድረጉን አስታውቀዋል።

የቀሩትንም ለመመለስ አስፈላጊው ድጋፍ የፌደራል መንግስትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የክልሉ መንግስት በጋራ እየሰሩ ይገኛሉም ብለዋል።

በግድያና ዝርፊያ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት 200 ሰዎች መካከል በ23 ሰዎች ላይ መረጃ ተመርምሮ እየተጠናቀቀ በመሆኑ
ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ዶክተር ነገሪ ተናግረዋል።

ንብረታቸው የተዘረፈ ሰዎች ንብረታቸው ከዘራፊዎች ተሰብስቦ ተመልሷል ያሉት ሀላፊው፥ የክልሉ መንግሰት አስፈላጊውን ድጋፍ አድርጎ የተዘረፈውን ንብረት በቦታው ለመመለስ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሊቢያ‼️

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር #በሊቢያ ህይወታቸው #ለአደጋ ተጋልጦ የነበሩ #ኢትዮጵያውያን ዛሬ ምሽት ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ አስታወቀ።

#ካይሮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሊቢያ ከሚኖሩ ሌሎች በጎ አድራጊ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት (አይ.ኦ ኤም) ጋር በመተባበር 15 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ምሽቱን ከትሪፖሊ ወደ ሀራቸው እንዲመለሡ ይደረጋል።

Via~fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አደጋ ለመቆጣጠር የተንቀሳቀሰው ተሽከርካሪ እራሱ #ለአደጋ ተጋለጠ። ዛሬ ማለዳ ላይ ቁስቋም በተለምዶ ሳንባ ነቀርሳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተነሳውን እሳት ለመቆጣጠር ሲንቀሳቀስ የነበረው የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ተሽከርካሪ አሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ከቤት መኪና ጋር ተጋጭቶ የመገልበጥ አደጋ ደርሶበታል። የዓይን እማኞች እንደዳሉት አሽከርካሪዎችን ጨምሮ ተሳፋሪዎች ወደ ህክምና የተወሰዱ ሲሆን ለህይወት የሚያሰጋ አደጋ እንደዳልደረሰባቸው ገልጸዋል።

via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Afar #Tigray #UNHCR #IOM

UNHCR ከትግራይ ክልል ውስጥ #ለአደጋ_ተጋላጭ ናቸው ያላቸውን 55 ኤርትራዊያን ስደተኞችን በIOM Ethiopia እገዛ ወደ አፋር ክልል ማዛወሩን አስታውቋል።

ወደአፋር ክልል ከተዘዋወሩት ስደተኞች መካከል ከግማሽ በላዩ ህጻናት ናቸው።

UNHCR ስደተኞቹ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለወራት ከኖሩ በኃላ አሁን ላይ ምቹ ወደሆነ መጠለያ እንደሚገቡ እና አስፈላጊውን ሁሉ እርዳታ እንደሚያገኙ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከቀናት በፊት በኦሮሚያ ክልል፤ " ገብረ ጉራቻ " በ9 ቻይናውያን ላይ ጥቃት ተከፍቶ የአንድ ቻይናዊ ህይወት ማለፉ ይታወቃል።

ይህንን ጥቃት በተመለከተ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ማረጋገጫ ሰጥቶ ለጥቃቱ መንግስት በህ/ተ/ም/ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀውን " ሸኔ " ቡድንን ተጠያቂ አድርጓል።

የክልሉ ኮሚኒኬሽን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በሰጠው ቃል የሽብር ቡድኑ በቀን 22/05/2015 ዓ/ም ማታ በገብረ ጉራቻ ከተማ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ በነበሩ ሰዎች ላይ በተጠና ሁኔታ በፈፀመው ጥቃት አንድ ቻይናዊ ሲገደል ፤ አንድ ኢትዮጵያዊ በቡድኑ #ታፍኖ መወሰዱን ገልጿል።

የገብረ ጉራቻውን ጥቃት በተመለከተ አዲስ አበባ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ፤ በ9 ቻይናውያን ላይ ጥቃት ተከፍቶ አንድ ቻይናዊ መገደሉን መግለፁ ይታወሳል።

ኤምባሲው ጉዳዩን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ስለጥቃት አድራሾቹ ማንነት ምንም ያለው ነገር አልነበረም።

ጥቃቱን ተከትሎ የቻይና ኤምባሲ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩና ኢትዮጵያን የሚጎበኙ ዜጎቹ #ለአደጋ_ከሚያጋልጡ ቦታዎች ለቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ መስጠቱ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia