TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሞያሌ‼️

በሞያሌ ከተማ በተከሰተ ግጭት 21 ሰዎች #መሞታቸውንና 61 ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን የሶማሌ ክልል  መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ  ገለጸ።

በሞያሌ ከተማና አከባቢዋ የሚከሰቱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ውይይት እየተደረገ ነው።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ #ሱረው_መሐመድ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት በዜጎች ላይ ጉዳቱ የደረሰው ባለፉት ሁለት ቀናት በደረሱ ግጭቶች ነው።

በግጭቱ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ወገኖችን ለመርዳት ሁለት ቡድኖች ወደ አካባቢው ተልከው ሕክምና መስጠት መጀመራቸውን ገልጸዋል።

በግጭቱ ከተፈናቀሉት ወገኖች የተወሰኑት ወደ ኬንያ #መሰደዳቸውንም አቶ መሐመድ ተናግረዋል።

በመከላከያ ሠራዊት ካምፕ ለተጠለሉ ተፈናቃዮች ደግሞ የክልሉ መንግሥት እርዳታ ለማቅረብ እንቅስቃሴ ጀምሯል ብለዋል።

በሞያሌ ከተማና አከባቢዋ የሚከሰቱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የፌዴራል፣የሶማሌና የኦሮሚያ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮችና ባህላዊ መሪዎች እየተወያዩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የክልሉ መንግሥት በሞያሌ ከተማና አካባቢውና የሚታዩ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን ምክትል ኃላፊው አስታውቀዋል።

ሕዝቡ የሁለቱ ክልሎችን ሕዝብ ወደ አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ ለማስገባት የሚንቀሳቀሱ አካላትን እንቅስቃሴ ለማክሸፍ እንዲረባረብ አቶ መሐመድ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia