TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፕሮፌሰር #ፍቅሬ_ቶሎሳ እንዲህ ብለዋል...

"ጀርመን ሄጀ የወለድኩት ልጅ ጀርመነኛ ቢናገር፣ እንግሊዝ የወለድኩት ልጅ እንግሊዘኛ ተናጋሪ ቢሆን፣ ጣሊያን ሀገር የወለድኩት ጣሊያንኛ ተናጋሪ ቢሆን ልጆቼ የተለያየ ቋንቋ ስለተናገሩ ወንድማማችነታቸው ይፋቃል ወይ? እኔስ ኦሮሞኛ፣ አማርኛና ትግርኛ ተናጋሪ በመሆኔ ወይም ልጆቼ የሚናገሩትን ቋንቋ ስላልተናገርኩ አባትነቴ ይፋቃል ወይ? የሚያዛምደን ስጋና ደማችን እንጅ #ቋንቋችን አይደለም፤ ስለዚህ እኛ #ኢትዮጵያውያን የተለያየ ቋንቋ መናገራችን ሊከፋፍለንና ሊያጋጨን አይገባም"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
”ወጣቱ ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ ስልጣኔዋ ለመመለስ ለሰላም ዘብ መቆም አለበት”-ፕሮፌሰር #ፍቅሬ_ቶሎሳ
.
.
.
ወጣቱ ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ ስልጣኔዋ ለመመለስ ታሪኩን አውቆ #ለሰላም ዘብ መቆም እንዳለበት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ገለጹ፡፡

“የአስተሳሰብ አብሮነት መልካም ነገርን ለማየት” በሚል መሪ ቃል የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና መምህራን ከታዋቂው ደራሲና ገጣሚ ጋር ተወያይተዋል።

ፕሮፌሰር ፍቅሬ ወጣቱ የአገሩን የቀደመ ታሪክ ማወቅና ለአብሮነትና አንድነት የሚጠቅሙ እሴቶችን እንዲያጠናክር አስገንዝበዋል፡፡

የተጀመረው አራዊ የለውጥ ጉዞ ውጤታማ የሚሆነው ወጣቱ በሰከነ መንገድ የአገሩን ሰላም ሲጠብቅና ሲያከብር ነው ብለዋል፡፡

በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችና አለመግባባቶች የግለሰቦች የጥቅም ግጭት እንጂ ፤ የኢትዮጵያ ህዝቦች መገለጫዎች አለመሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

የተረጋጋ ሰላም እንዲኖርና የኢትዮጵያውያን አንድነት በጠንካራ መሰረት ላይ እንዲጸና ወጣቶች በአስተውሎ ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባም ፕሮፌሰር ፍቅሬ# አሳስበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia