TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update በሲዳማና በወላይታ ሕዝቦች መካከል ያለውን #ትስስር ለማጠናከር የሚያግዝ የዕርቅና የሠላም ኮንፈረንስ ትላንት በሀዋሳ ሲዳማ ባህል አዳራሽ ተካሂዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ~ሲዳማ!

የሲዳማ ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች በሰኔ 8 2010 ዓ.ም በሀዋሳ እና አከባቢው በተከሰተው ግጭት ሕይወታቸውን ያጡ የወላይታ ብሔር ተወላጆች ቤተሰብ ላይ ለቅሶ በመድረስ #አጽናንተዋል፡፡

ረጅም ዘመናትን የዘለቀው የሁለቱ ህዝቦች #ትስስር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የሟች ቤተሰቦች ገልጸዋል፡፡

የሲዳማ ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች በሐዋሳና አከባቢዋ በተፈጠረው ግጭት ልጆቻቸውንና ዘመዶቻቸውን በሞት ለተለዩ ቤተሰቦች ላይ ለቅሶ በደረሱበት ወቅት ከሟች ቤተሰቦች አንዳንዶቹ እንደተገለጹት ሁለቱ ህዝቦች ለረጅም ዘመናት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ተሳስረው፣ ተቻችለውና ተከባብረው የኖሩ ህዝቦች ናቸው፡፡

በሁለቱ ህዝቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር የሚቀሰቅሱ አካላት ሊገስጹ ይገባል ብለዋል፡፡

በሰኔ 8 2010 ዓ.ም በሀዋሳ እና አከባቢው በተከሰተው ግጭት የሰው ህይወት በመጥፋቱ እጅግ ማዘናቸውን የሟች ቤተሰቦች ገልፀው እርቀ ሰላም እንዲወርድ ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ በየደረጃው የሚገኙ አመራር አካላት፣ አስታራቂ ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #ዳጋቶ_ኩምቤ እንደተናገሩት የወላይታ እና የሲዳማ ህዝቦች ለዘመናት ተከባብረውና ተቻችለው አብረው የኖሩ ህዝቦች ናቸው፡፡

የሁለቱ ህዝቦች ታሪካዊ ትስስር በአንድ መድረክ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በሁለቱ ህዝቦች መካከል በተከሰተው ግጭት ክቡር የሆነው የሰው ህይወት ከመጥፋቱም በላይ በሰው አካል ላይ ጉዳት ያደረሰ፣ በርካታ ንብረት የወደመበት እና በርካታ ሰው የተፈናቀለበት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ይህ ጥፋት ሁለቱንም ህዝቦች የማይወክል ጥቂት ቡድኖችና ግለሰቦች የራሳቸውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅም ለማግኘት ሆን ብለው ግጭቱ የብሔር ይዘት እንዲኖረውና የህዝቦቹ ትስስር #እንዲሻክር ያደረጉት ነው ብለዋል፡፡

#የሲዳማ_ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች እንደተናገሩት በወላይታ ሶዶ በመገኘት ወገኖቻቸውን በሞት ላሰጡ ቤተሰቦች ላይ ለቅሶ ለመድረስና ለማጽናናት የመጡበት ዋናው ዓላማ የሁለቱ ህዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ግንኙነታቸውንና አብሮነታቸውን ለማደስ ነው፡፡

የወላይታ እና የሲዳማ ህዝቦች ረጅም ዘመን የቆየው አንድነትና አብሮነት ቀጣይነት አንዲኖረው ለማድረግ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ የሀገር ሽማግሌዎቹ አስታውቀዋል፡፡

የሁለቱ ህዝቦች አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ የሟች ቤተሰቦችን የማጽናናት ሥራ በባህላዊ የዕርቅ ስርዓት ተከናውኗል፡፡

በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት ታህሳስ 25 ቀን 2011 ዓ.ም የወላይታ ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች ወደ ሐዋሳ በማቅናት በሲዳማ ብሔር በኩል በግጭቱ ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ላይ ለቅሶ በመድረስ እንደሚያጽናኑ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ Wolaita ZONE Culture,tourisim and Governmental Communication Affairs Office
@tsegabwolde @tikvahethiop
እኛስ

የጥንት አባቶቻችን ያለብሄር፣ ያለዘር፣ ያለቋንቋ፣ ያለሀይማኖት ልዩነት ወራሪውን የጣልያን ጦር አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው፤ በደም በአጥንታቸው ይህቺን ሀገር #አስከብረው ለኛ #አስረክበውናል

የዛሬዎቹ ትውልዶች እኛስለቀጣዩ ትውልድ ምን ይሆን የምናወርሰው? የትኛዋን ሀገር ነው የምናወርሰው?

ወገኖቼ ለመጪው ትውልድ ክፍፍል እናውርስ? አንድ የሚያደርገንን ሰውነትን ረስተን በብሄር መቧደንን ለልጆቻችን እናውርስ? ንገሩኝ...በዘር መከፋፈልን እናውርስ? አለመከባበርን እናውርስ?? መሰዳደብን እናውርስ? ቁጭ ብሎ ማውራትን እናውርስ? አለመደማመጥን እናውርስ?

ቆይ ምን ሰርተን አለፍን እንበል

አድዋ የነፃነት ምልክት ብቻ አይደልም፤ አድዋ የኢትዮጵያዊያን #አንድነት እና ጠንካራ #ትስስር መገለጫም ጭምር ነው።

አድዋን ስናከብር...እኛስ ለቀጣዩ ትውልድ ምን እናውርስ? እኛስ ለኢትዮጵያ ምን ሰርተን እንለፍ? የሚሉትን ጥያቄዎች እራሳችንን #እየጠየቅን መሆን አለበት።

በTIKVAH-ETH ስም ሁላችሁንም እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ!

ሰላም፤ ፍቅር፤ አንድነት!
#Adwa123 #አድዋ123
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደስታ መግለጫ--ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው!

የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ለአዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው የደስታ መግለጫ ላኩ። የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ አምባሳደር ማህቡብ ማሊም በትናንትናው ዕለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ለተሾሙት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የደስታ መግለጫ መልዕክት ልከዋል። ሹመቱ ተገቢ መሆኑን የገለጹት ዋና ጸሃፊው፣ አቶ ገዱ የወቅቱ የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀመንበር መሆናቸውን በመጥቀስ በቀጣይም ከእርሳቸው ጋር በቅርበት ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በኢጋድ ቀጣና ሰላም፣ ልማትና የኢኮኖሚ #ትስስር እንዲመጣ እያከናወነች ያለችውን ጥረትም #አድንቀዋል ዋና ጸሃፊው።

ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia