TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢንተርኔት...

የሞባይል ኢተርኔት በሌሎች ስፍራዎች "ቀስ በቀስ" ይጀምራል ሲሉ የኢትዮ ቴሌኮም ሴክረተሪ ዳይሬክተር ወ/ሪት ጨረር አክሊሉ ተናገሩ። ዳይሬክተሯ ከጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ጋር ባደረጉት የስልክ ቆይታ ከሰሞኑን ኔት ብሎክስ -- ኢትዮ ቴሌኮም ኢንተርኔት በመዝጋቱ በቀን 4.5 ሚሊዮን ዶላይ ያጣል ሲል ስላወጣው ሪፖርት ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል፦ "ድርጅቱ ከእኛ መረጃ አልጠየቀም። ስለዚህ ስሌታቸው በምን እንደሆነ አናውቅም። ወደፊት ግን ያስከተለውን የገንዘብ እጦት እኛ ይፋ እናደርጋለን" ብለዋል። በመጨረሻም ወ/ሪት ጨረር ፓኬጅ ገዝተው ይጠቀሙ የነበሩ ደንበኞች ላልተጠቀሙበት ግዜ ተመላሽ/መራዘም ይደረግላቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።

Via #EliasMeseret
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰኔ 15 ጦር ሀይሎች አካባቢ ምን ተከሰተ?
/ከአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/

ሰኔ 15 ቀን አመሻሽ ላይ በአማራ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ውስጥ ቦሌ አካባቢ የተከሰተው ግርግር እና ግድያ ብዙ ትኩረት ቢስብም #ጦር_ሀይሎች በተለምዶ ሲግናል (በድሮ አጠራሩ #መኮ) የተከሰተው ሁነት ግን እስካሁን ይፋ አልሆነም።

ጋዜጠኛ ኤልያስ ቢያንስ ሶስት ምንጮች አረጋገጡልኝ እንዳለው ጦር ሀይሎች አካባቢ በነበረው ግጭት ሁለት ወይም ሶስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። እስከ ለሊቱ ስድስት ሰአት ገደማም የጥይት ተኩስ ይሰማ ነበር። ይህ ክስተት በእለቱ ከነበሩት ሌሎች ግድያዎች ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ግልፅ አይደለም።

በቅርቡ ስለ ጉዳዩ በAPው ጋዜጠኛ የተጠየቁ አንድ የመንግስት የስራ ሀላፊ "ስለ ጉዳዩ መረጃ የለኝም። አጣርቼ መልስ ልሰጥህ እሞክራለሁ" የሚል ምላሽ ሰጥተው ነበር።

በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ አለኝ ያለ አንድ ግለሰብ ለጋዜጠኛው ተከታዩን መረጃ አቀብሎ ነበር፦

"ስለ ሰኔ 15ቱ (የጦር ሀይሎች አካባቢ ጉዳይ) የተወሰነ መረጃ አለኝ። መረጃውን ላገኝ የቻልኩት ደግሞ በዛ ምሽት ከሞቱት ሶስት የፌዴራል ኮማንዶዎች አንዱ የአክስቴ ልጅ ስለነበር ሬሳ ለመቀበል ከቤተሰብ ጋር በሄድንበት ጊዜ የአሟሟቱ ጉዳይ ስለተነገር ነው። እናም ጉዳዩ ከጀነራሎቹ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠረ አንድ ኮሎኔል ለመያዝ በሄዱበት ጊዜ በተፈጠረው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ነው። ግን እስካሁን አንድ የመንግሥት አካል ስለ ጉዳዩ ምንም ነገር አለማለታቸው እጅግ በጣም አሳዝኖኛል።"

Via #EliasMeseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ የፈተና ውጤት ይፋ እንደማይሆን ተገለፀ!

ከቀናት በፊት በተለያዩ የመንግስት ሀላፊዎች የፈተና ውጤት ዛሬ ነሀሴ 5 እንደሚለቀቅ ሲገለፅ ነበር። የፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሔር ከደቂቃዎች በፊት እንደገለፁት፦ "ውጤቱን ለማውጣት #ትንሽ ተጨማሪ ስራ መስራት አስፈልጎናል። ዛሬ ሳይሆን ከሁለት ቀን በሁዋላ አካባቢ ይለቀቃል። ይህ መራዘም ያስፈለገው ከዛሬው በአል ጋር በተገናኘ ሳይሆን ትንሽ ሌላ የምንሰራው ስራ ስላጋጠመን ነው" ብለዋል።

Via #EliasMeseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ ሲሰራጭ በነበረው ቪድዮ ዙርያ ነገ መግለጫ ይሰጣል ተብሏል።

Via #EliasMeseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚር አብይ ነገ ጠዋት🛫እስራኤል ያመራሉ!

የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለጋዜጠኞች በላከው መረጃ የኢትዮጵያው መሪ ከእስራኤሉ ጠ/ሚር ቤንጃሚን ኔታናያሁ እና ከፕሬዝደንቱ ሬኡቨን ሬቭሊን ጋር ሰኞ ይገናኛሉ።

Via #EliasMeseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የሀሳብ ማዕድ" #EliasMeseret #AddisAbeba

PHOTO: TIKVAH FAMILY
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EliasMeseret Tikvah Eth family!

የምናከብረው እና የምንወደው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ለቤተሰባችን የተመረጡ መረጃዎችን ማቅረብ ይጀምራል።

ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት የተመረጡ መረጃዎችን ለቤተሰባችን ከማቅረብ በተጨማሪ ወጣቶች፣ ተማሪዎች፣ መላው የማህበረሰቡ በሀሰተኛ ዜናዎች እንዳይደናገር እና እንዳይታለል አሁን እያደረገ ካለው በተጨማሪ ጊዜውን መሥዕዋት በማድረግ የአቅሙን አስተዋፆ ያደርጋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ "የሀሰተኛ ዜናዎች መድሃኒት" የሆነው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በማህበራዊ ሚዲያዎች በትዊተር፣ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም ላይ ባሉት ትክክለኛ የግል ገፆቹ በርካታ ስራዎችን ሰርቷል። በሀሰተኛ መረጃዎች እንዳይታለሉ ለበርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች፣ ለቴሌቪዥን እና ሬድዮ ጣቢያዎች፣ ለጋዜጠኞች ባለውለታም ጭምር ነው።

ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ አክቲቪስቶችን እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን በማሰባሰብ ለውይይት በአንድ ጠረጴዛ እንዲቀመጡ ለማድረግ እያደረገ ያለውን ስራም በመላው የቤተሰባችን አባላት የሚታወቅ ነው።

ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ የቤተሰባችን አባል በመሆኑ ትልቅ ደስታ ይሰማናል፤ ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ደግሞ የመረጣቸውን መረጃዎች ለቤተሰባችን ከመፃፍ በተጨማሪ፣ ማህበረሰቡን እንዲሁም እዚህ ለተሰባሰብነው ከ442,000 በላይ ለምንሆነው የቲክቫህ ቤተሰቦች ስለማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራም ይሰራል።

Tikvah Eth family!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EliasMeseret #TikvahFamily

የሀሰተኛ ዜናዎች መድሃኒት "ኤልያስ"!

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰባችን አባል የሆነው ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ነገ ከምሽቱ 12:00-1:00 ለናተ ለውድ ቤተሰቦቻችን የተመረጡ መረጃዎችን ያደርሳችኃል።

STOP FAKE NEWS!

@tsegabwolde @tikvahethiopia