ዮናስ ጋሻው‼️
‹‹የፍትህ ሰቆቃ›› በሚል በተሰራጨው ዘጋቢ ፊልም ላይ በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ በደረሰበት #ድብደባ በአካሉ ላይ ጉዳት የደረሰበት ወጣት #ዮናስ_ጋሻው ከተለያዩ አካላት ዛቻና መስፈራሪያ እየደረሰበት መሆኑን ተናገረ።
ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ላይ ወጣቱ እንደገለጸው፤ «የደረሰብኝን ግፍ በመገናኛ ብዙኃን ይፋ ማድረጌን ተከትሎ የተለያዩ ዛቻና ማስፈራሪያዎች እየደረሱብኝ ነው” ብሏል።
“ከሁሉ በላይ ግን ልቤን የሰበረው በበደል ፈፃሚዎች ባለሥልጣናት የሚደርስባቸውን ጫና በመፍራት አንዳንድ አከራዮች ለህይወታ ቸው
አስጊ በመሆኔ ቤታቸውን እንድለቅ ማድረጋቸው ነው» ሲልም ነው ወጣት ዮናስ የተናገረው።
የአንድ ልጅ አባት መሆኑን የሚናገረው ወጣት ዮናስ ከደረሰበት የሥነ ልቦና ጫና እና የአካል ጉዳት ባሻገር በአሁኑ ወቅት ቤት ንብረቱን ማጣቱንም ገልጿል።
እርሱም ሆነ ሌሎች የታሰሩ ወገኖች ዋጋ የከፈሉት በፍትህ እጦት እንደመሆኑ ህዝቡም ሆነ መንግሥት የሚገባውን ከለላ ሊያደርግላቸው እንዲሁም ካሳ ሊከፈላቸው እንደሚገባ አስታውቋል።
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia