TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የስደተኞች ጉዳይ...‼️

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 9፣ 2011 ዓ. ም. ማለዳ ባደረገው አስራ ዘጠነኛ #መደበኛ ስብሰባ፤ #የስደተኞች_ጉዳይ ረቂቅ አዋጅን በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

አዋጁ በተለያየ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ስደተኞች ልዩ ልዩ መብቶችን በማጎናፀፍ፤ ኢትዮጵያ ለምታስተናግዳቸው ስደተኞች የምታደርገውን እንክባካቤ ያስቀጥላል ተብሏል። አዋጁ በሦስት ተቃውሞና በአንድ ተዓቅቦ ፀድቋል።

በአዋጁ መሠረት ዕውቅና ያገኙ ስደተኞች ከመንቀሳቀስ መብት በተጨማሪ ትምህርትና ሥራ የማግኘት መብት ይኖራቸዋል።

ኢትዮጵያ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች የሚገኙባት ስትሆን፤ ይህም በርካታ ስደተኞችን ከተቀበሉ የአፍሪካ አገራት ከቀዳሚዎቹ ተርታ ያስመደባታል።

"በኢትዮጵያዊያን ሥራ ፈላጊዎች ላይ ተጨማሪ ፈተና ይደቅናል። ስደተኞችን የሚያስተናዱ የክልል መንግሥታት አልተማከሩበትም" የሚሉ ነቀፌታዎችን አዋጁ ላይ የሰነዘሩ የሕዝብ እንደራሴዎች ነበሩ።

አዋጁን የተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጡ የነበሩት የሕግ፣ የፍትሕ እና ዲሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፎዚያ አሚን፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወኪል በመሆኑ፤ በጉዳዩ ላይ መወያየቱ የሕዝቦችን ድምፅ እንዳስተናገደ እንደሚቆጠር ተናግረዋል። በተጨማሪም በረቂቅ አዋጁ ላይ ሕዝባዊ ምክክሮች መደረጋቸውን አስረድተዋል።

በአዋጁ መሠረት፤ ስደተኞች ለውጭ አገር ዜጎች የተፈቀዱ የሥራ መስኮች ላይ የመሰማራት ዕድል የሚኖራቸው ሲሆን፤ ይህም የኢትዮጵያዊያንን ዕድል የሚነጥቅ ሳይሆን ክፍተትን የሚሞላ ይሆናል ተብሏል።

ከማርቀቅ እስከ ማስፀደቅ ከሁለት ዓመታት በላይ ጊዜ ወስዷል የተባለው አዋጅ፤ በዓለም አቀፍ ትብብር በሚቀረፁ ላይ ሰባ መቶ የሚሆነውን ድርሻ ኢትዮጵያዊያን እንዲይዙት ተደርጎ፤ የቀረውን ብቃት ባላቸው ስደተኞች እንዲያዝ የሚያስችል ይሆናል።

ለስደተኞች ክፍት ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁት እና ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ አጋሮቿ ጋር በጋራ ከምትከውናቸው ፕሮጀክቶች መካከል የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና የመስኖ ልማቶች ይገኙበታል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia