TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ከ7 ዐመት በኋላ የእነ ጋዜጠኛ #እስክንድር_ነጋ "ኢትዮጲስ" መፅሄት ወደ ህዝብ መድረስ ሊጀምር ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Ethiopia_ጀዋር_እና_እስክንድር_በDW_የአዲስ.mp3
14.9 MB
ጀዋር መሀመድ እና እክንድር ነጋ በDW የአዲስ አበባ የባለቤትነት ዉዝግብ፦

«እኛ የምንለዉ ሕጉ የሚለዉን ነዉ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሕግ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ነች ይላል። የፌደራሉ ሕገ መንግሥትም ኦሮሚያ (ከአዲስ አበባ) ልዩ ጥቅም እንዳለዉ ያስቀምጣል------»የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅና የመብት አቀንቃኝ #ጀዋር_መሐመድ

«የአዲስ አበባ ጉዳይ የዜግነት ጥያቄ ነዉ-----ሕገ መንግስቱ ከየት መጣ? ማን አወጣዉ? ምንስ አላማ ነበረዉ?------» ጋዜጠኛና የመብት አቀንቃኝ #እስክንድር_ነጋ

«እንዴ!! ምነዉ እባክሕ? እስክንድር ነጋ እኮ የመብት ታጋይ ነዉ----ልንቃወመዉ፣ ልንተቸዉ እንችላለን፣ ከዚያ ባለፈ ግን ዛሬ እስክንድርን ያስፈራሩ ነገ ጀዋርን #ያስፈራራሉ-----እስክንድር ብቻዉን ሳይሆን ሁላችንም አብረነዉ ተሰልፈን እንታገላለን----»ጀዋር መሐመድ

ጀዋር ያለዉን «የምጠራጠርበት ምንም ምንም ምክንያት የለኝም። #አመሰግነዋለሁ።-------»እስክንድር ነጋ

«በግሌ ከጠይቀከኝ ከእስክንዳር ጋር አይደለም ከማንም ጋር በማንኛዉም ሰዓት በዚሕ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌላም ጉዳይ ላይ ለመወያየት ዝግጁ ነን----»ጀዋር መሐመድ

«ለመወያየት መቶ በመቶ ዝግጁ ነኝ። እምንፈታዉም በድርድርና ዉይይት ነዉ።----ብስለቱም አለን» እስክንድር ነጋ

Via የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እስክንድር ነጋ

በጋዜጠኛ #እስክንድር_ነጋ የሚመራው የባልደራስ ምክር ቤት የፀጥታ ስጋት መኖሩን ፓሊስ መከልከሉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕረስ ሴክሬታሪያት አቶ #ንጉሱ_ጥላሁን አስታወቁ፡፡ የፕረስ ሴክሬታሪያቱ አዲስ አበባን በተመለከተ የተለያዩ ሀሳቦች እንዲሁም እንቅስቃሴዎች አሉ ብለዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ተጨባጭ የፀጥታ ስጋት በመኖሩ እና ውጤቱም ወደ ግጭት ሊያመራ የሚችል በመሆኑ ከእስክንድር ነጋና ከአመራሮቹ ጋር ፓሊስ ውይይት እንዳደረገ ነው የተናገሩት፡፡

በዛሬው ዕለትም ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ ምልክቶች የታዩ በመሆኑና እነዚህን ነገሮች በሰላማዊ መንገድ ስርዓት ማስያዝ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ጋዜጣዊ መግለጫው እንዲቋረጥ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የባልደራስ ምክር ቤት የፖለቲካ ስልጣን ጥያቄ የለውም!!

ከጋዜጠኛ #እስክንድር_ነጋ መግለጫ በፊት የባላደራ ምክር ቤቱ የአቋም መግለጫ በጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ተነቧል።

በጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ መግለጫ እንድትሰጡ መንግስት ፈቅዶላችሁ ነበር። ለምን አልተጠቀማችሁበትም? ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የቀረበለት ጥያቄ ነበር።

መልስ፦

እኛ ቤተመንግስት አንገባም። የህዝብ ድምፅ ነን። ለወደፊቱም ህዝብ መሃል እንጂ ቤተመንግስትም ሆነ ሌላ የመንግስት ተቋም ውስጥ ሆነን መግለጫ አንሰጥም። በሚቀጥለው ምርጫ የመወዳደር ፍላጎት ፈፅሞ የለኝም እንደ አጠቃላይ እራሱ የባልደራስ ምክር ቤት የፖለቲካ ስልጣን ጥያቄ የለውም። ባቋራጭ ስልጣን ለመንጠቅ የሚባለው ነገር ከንቱ ውንጀላና የተነሳውን የመብት ጥያቄ ለማዳፈን የቀረበ ምክንያት ነው።

Via Nafkot Eskinder
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ምስጋናው ጌታቸው
/በኤልያስ መሰረት/

"ጋዜጠኛችን በሁለት ዙር ድብደባ ተፈጽሞበታል። እንደሰማሁት ደብዳቢ ፖሊሶቹ 'እስክንድር ይመጣል ብለን ነበር' እያሉ እኔን ሲጠባበቁ ነበር"--- #እስክንድር_ነጋ

"በተባለው ግለሰብ ላይ ምንም ድብደባ አልተፈፀመም። የጋዜጠኛ መታወቂያ እና ደብዳቤ ሳይዝ በድብቅ ካሜራ ሲቀርፅ ተይዞ መጣራት እያረግን ነው"--- የአራዳ ፖሊስ ባልደረባ ኮማንደር የኔወርቅ

እስክንድር እንደሚለው "ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦች ኢትዮጲስ ጋዜጣን 'ጉዳያችንን ዘግቡልን' ባሉት መሰረት ጋዜጠኛ ምስጋናው ጌታቸው በድብቅ የሚቀርፅ ሪኮርደር ይዞ ዛሬ ወደ ስፍራው አመራ። መነፅር ላይ ያለው ይህ ድብቅ ካሜራን ለመጠቀም የፈለግነው ፖሊሶች ተደራጅተው እንደሚጠብቁን ስላወቅን ነው። ጋዜጠኛው ስፍራው ላይ እንደደረሰ ካሜራውን ተቀብለው ደበደቡት። እንደገና በሁለተኛ ዙር ከ45 ደቂቃ በሁዋላ ድብደባ አደረሱበት። ከዛም 4 ኪሎ ብርሀን እና ሰላም አካባቢ ወዳለ ፖሊስ ጣብያ ወስደውታል። ፖሊስ አሁን እያለ ያለው ጋዜጠኛው ቃሉን ከሰጠ በሁዋላ አቃቤ ህግ ይወስናል ነው። ድብደባ ሲፈፀምበት ምስክር አለ ብንላቸውም ክስ መመስረት አትችሉም ተብለናል።"

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት ኮማንደር የኔወርቅ ደሞ "ጋዜጠኛ ለመሆኑ መታወቂያ ይዟል እንዴ?" ብለው እኔኑ ጠይቀውኝ ከዛ እንዲህ ብለዋል። "የተደበደበ የለም። ፍቃድም መታወቂያም አልነበረውም። እኛ ገና ጋዜጠኛ መሆኑን እያጣራን ነው። ተደብቆ ሲቀርፅ የእኛ ፖሊሶች ይዘውታል። ፈቃድ የሌለው ሰው በድብቅ ሰው መቅረፅ አይችልም። ግን ጫፉን የነካው ሰው የለም።"

እስክንድር አክሎም "የጋዜጠኝነት ስራ ለመስራት ልዩ ፈቃድ አያስፈልገውም። አስፈላጊነት መስዋትነት እንከፍላለን እንጂ ሁሌ ደብዳቤ እያፃፍን ስራ አንሰራም" ብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia