TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ በ2015 ዓ.ም ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዟል!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሃል ክፍል የአርማታ ሙሌት ስራ መጀመሩን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር #አብርሃም_በላይ ከፋና ብሮድካስቲንግ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት የግድቡ ግንባታ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው።

የሁለቱ ቅድመ ሃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የብረታ ብረት ገጠማ እና ኤሌክትሮ መካኒካል ስራም ግማሽ ተጠናቋል ነው ያሉት። የግድቡ አካል ከሆኑት አንዱ የሆነው ኮርቻ ግድብ (ሳድል ዳም) ግንባታው ከሁለት ወራት በኋላ እንደሚጠናቀቅም ተናግረዋል። አሁን ላይ ግድቡ ከ16 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ በላይ አለት የተሞላ ሲሆን፥ ኮንክሪት ለብሶ የማጠናቀቂያ እና የለቀማ ስራ ላይ መድረሱንም ገልጸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-24

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia