TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ታላቁ ቤተ መንግስት⬆️

በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤትና #መኖሪያ የሚገኝበትን በአራት ኪሎ አካባቢ የሚገኘው የአፄ ምኒልክ ቤተ መንግሥት በዘመናዊ መንገድ በማደስና በማልማት ወደ #ሙዚየምነት ለመቀየር፣ የፈረንሣይ መንግሥት #ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱ ታወቀ።

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት ታላቁን የምኒልክ ቤተ መንግሥት በማደስና ተጨማሪ ልማቶችን በማከናወን፣ ለሕዝብና ለጎብኝዎች ክፍት የሚሆን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ዕቅድ ተይዟል፡፡ ይህንንም በፍጥነት በተግባር ለመቀየር የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርትሚኒስቴር ኃላፊነት ተሰጥቶታል።

ይሁን እንጂ ፕሮጀክቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸው በበላይነት እየተከታተሉት እንደሚገኝ ታውቋል። በዚህም መሠረት የተለያዩ አገሮች ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኝነታቸውን እንዳሳዩ፣ በዋናነት ግን የፈረንሣይ መንግሥት አስፈላጊውን የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱን ምንጮች ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ሳምንት የሚያደርጉትን የአውሮፓ ጉብኝት በፈረንሣይ የሚጀምሩ ሲሆን፣ በፈረንሣይ በሚኖራቸው የአንድ ቀን ቆይታ ቤተ መንግሥቱን ወደ ቱሪዝም መዳረሻ ለመቀየር ለተቀረፀው ፕሮጀክት የሚፈለገውን የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ የተመለከተ ስምምነት ተፈራርመው ይመለሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግንቦት ወር 2010 ዓ.ም. በውጤታማ ሥራ አፈጻጸም ላይ በወቅቱ ለነበሩ የካቢኔ ሚኒስትሮች ባደረጉት ገለጻ፣ የአፄ ምኒልክ ቤተ መንግሥትን የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ እንደሚገባ መግለጻቸው ይታወሳል።

 ቤተ መንግሥቱ ኢትዮጵያ ምን እንደምትመስልና ጥንታዊ ገናናነቷ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ መሆን በወቅቱ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ያለፋት የኢትዮጵያ መንግሥታት እያንዳንዳቸው በቅጥር ግቢው ትተው ያለፋትን አሻራ ለማሳየት፣ ለዓመታት የተዘጉ ቤቶችን በማስከፈት የካቢኔ አባሎቻቸውን እያዞሩ ማስጎብኘታቸው አይዘነጋም።

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia