TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዲሱ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ማን ይሆንከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ይታወቃል። #ጨፌ_ኦሮሚያ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጨፌ_ኦሮሚያ

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የህዝብን #ሰላምና #ደህንነት ለማረጋገጥ የህግ የበላይነት ለማስከበር ትኩረት እንዲሰጥ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ አሳሰቡ።

አፈ ጉባዔዋ ዛሬ በአዳማ ከተማ የከልሉን ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ጉባዔ ሲከፍቱ እንዳስገነዘቡት ለሕግ የበላይነት መከበር ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ ይገባል፤ የህዝብ የመልካም አስተዳደርና የእኩልነት ጥያቄ መመለስ አማራጭ እንደሌለው ያስገነዘቡት አፈ ጉባዔዋ ፣ በክልሉ ያለው ችግር የህግ የበላይነት ጥስትና የህዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ያለመመለስ ነው ብለዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ህዝቡ በትግሉ የተጎናፀፈውን ድልና ለውጥ ማደናቀፍ ሳይሆን ፣ የሰፈነውን የፖለቲካ ምህዳር በመጠቀም በምርጫ ተወዳድሮ ለማሸነፍ እንዲሰሩ አሳስበዋል። ጨፌው ችግሮቹን ለማስወገድና ለውጡን ለማስቀጠል ድጋፍ እንደሚያደርግም አፈ ጉባዔዋ አረጋግጠዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጨፌ ኦሮሚያ ለክልሉ የ2012 በጀት ዓመት ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አፅድቋል። #ጨፌ_ኦሮሚያ

@tsegabwolde @tikvahethiopia