TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስለ ትግራይ ህዝብ ከዶ/ር አብይ....

"ለኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ጥሪ ማቅረብ ምፈልገው ስለ ትግራይ ህዝብ ነው። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲ ይመጣል፤ ሰላም ይመጣል ብሎ ከማንም በላይ ልጆቹን ገብሯል። አሁን ዛሬ መልካም አስተዳደር ችግር ያለው ትግራይ ክልል ውስጥ ነው።

የትግራይ ክልል የተለየ ነገር ያገኘ የሚመስለን ዴሞክራሲ ያለው የሚመስለን፤ የተጠቀመ የሚመስለን በተለይ #ደቡብ#ኦሮሚያ#አማራ አካባቢ ያለን ሰዎች #እባካችሁን የትግራይ ህዝብ አሁንም ውሀ ለመጠጣት ይቸገራል። አሁንም ያገኘው አንዳች ትርፍ የለም።

በተሳሳተ መንግድ ጥቂት ሰዎች ተሳስተው ሲያሳስቱን ወለጋ ጫፍ ያለ የጋዝ ነጋዴ ጭምር በስመ ትግራይ መ ቅጣት ተገቢ አይደለም። ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። ያገኘው ነገር የለም። ይሄን የምለውን ነገር የማያምን ሰው በፈለገው መንገድ ትግራይ ገጠር ሄዶ ማየት ይችላል። ምናገረው እውነት ነው። #ጥቂቶች በስሙ ነግደው ይሆናል እንጂ የትግራይ ህዝብ የተለየ ጥቅም ያገኘው ነገር የለም።

ጥቅም አላገኘው እምብዛም ጥቅም አይፈልግም። የተለየ እንዲደረግለት አይፈልግም።

የአብዬን ወደ እምዬ የሚባል ነገር አይሰራም። Mr X አጠፋ ብለን የማያውቁ ሰዎችን ጭምር በዛ ወንጀል ሀሳብ በቂም፣ በጥላቻ ማየት ለኢትዮጵያ አይበጅም። መለየት ያስፈልጋል።

ይሄ ጥቃት እየባዛ ከመጣ ዘር መጨረስ ያመጣል። ይሄ ደግሞ ወርደት ለልጆቻችን ያሸጋግራል።"

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከተናገሩት የወሰድኩት።

ፍቅር ያሸንፋል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስለ ትግራይ ህዝብ ከዶ/ር አብይ....

"ለኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ጥሪ ማቅረብ ምፈልገው ስለ ትግራይ ህዝብ ነው። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲ ይመጣል፤ ሰላም ይመጣል ብሎ ከማንም በላይ ልጆቹን ገብሯል። አሁን ዛሬ መልካም አስተዳደር ችግር ያለው ትግራይ ክልል ውስጥ ነው።

የትግራይ ክልል የተለየ ነገር ያገኘ የሚመስለን ዴሞክራሲ ያለው የሚመስለን፤ የተጠቀመ የሚመስለን በተለይ #ደቡብ#ኦሮሚያ#አማራ አካባቢ ያለን ሰዎች #እባካችሁን የትግራይ ህዝብ አሁንም ውሀ ለመጠጣት ይቸገራል። አሁንም ያገኘው አንዳች ትርፍ የለም።

በተሳሳተ መንግድ ጥቂት ሰዎች ተሳስተው ሲያሳስቱን ወለጋ ጫፍ ያለ የጋዝ ነጋዴ ጭምር በስመ ትግራይ መ ቅጣት ተገቢ አይደለም። ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። ያገኘው ነገር የለም። ይሄን የምለውን ነገር የማያምን ሰው በፈለገው መንገድ ትግራይ ገጠር ሄዶ ማየት ይችላል። ምናገረው እውነት ነው። #ጥቂቶች በስሙ ነግደው ይሆናል እንጂ የትግራይ ህዝብ የተለየ ጥቅም ያገኘው ነገር የለም።

ጥቅም አላገኘው እምብዛም ጥቅም አይፈልግም። የተለየ እንዲደረግለት አይፈልግም።

የአብዬን ወደ እምዬ የሚባል ነገር አይሰራም። Mr X አጠፋ ብለን የማያውቁ ሰዎችን ጭምር በዛ ወንጀል ሀሳብ በቂም፣ በጥላቻ ማየት ለኢትዮጵያ አይበጅም። መለየት ያስፈልጋል።

ይሄ ጥቃት እየባዛ ከመጣ ዘር መጨረስ ያመጣል። ይሄ ደግሞ ወርደት ለልጆቻችን ያሸጋግራል።"

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከተናገሩት የወሰድኩት።

ፍቅር ያሸንፋል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
86,660 ብር ደርሰናል!

ምዕራፍ አንድ በ24 ሰዓት ውስጥ ሊጠናቀቅ ነው! 13,340 ብር ብቻ ይቅረናል(100,000 ብር)። የብሩን ማጠን ሳይሆን #አብሮነታችንን ማስመስከራችን ለቀጣይ ጉዟችን ትልቅ አቅም ይሆነናል። የዛሬው ህብረታችን ነገም ሌሎች ወገኖቻችን ለማገዝ ትልቅ አቅም ይፈጥርልናል።

#ኦሮሚያ #ሀረሪ #ደቡብ #ትግራይ #ሱማሌ #አፋር #ቤንሻንጉል #ጋምቤላ #አማራ #አዲስ_አበባ_ከተማ_አስተዳደር #ድሬዳዋ_ከተማ_አስተዳደር የምትገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ትልቅ ክብር አለን!

Account number(CBE): 1000277462439

@tsegabwolde @tikvaethiopia
#ደቡብ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሚታዩ የክልል እንሁን ጥያቄዎችን በጥናት ለመፍታት የክልሉ ገዥ ፓርቲ ደኢህዴን ሲያስጠና ቆየው ጥናት ውጤት ዛሬ ይፋ ሆነ።

የጥናት ቡድኑ ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዳሉት 20 አባላት ያሉት የጥናት ቡድን ተዋቅሮ ላለፉት ሰባት ወራት ሰፊ ጥናት ሲያካሂድ ቆየቷል። በዚህም መሰረት ሶስት አማራጮችን አስቀምጧል ብለዋል ምክትል ሰብሳቢዋ።

በጥናቱ የተለየው የመጀመሪያው አማራጭ አብዛኛው የክልሉ ህዝብ አሁን ያለው የክልሉ አደረጃጀት ቢቀጥል የህዝቦችን አብሮነትና ያጠናክራል፤ ጠነካራ የደቡብ ህዝቦች ክልልንና የኢትዮጵያን አንድነት ያጠናክራል የሚል ነው።

በጥናቱ የተለየው መጀመሪያ አማራጭ አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሮ ተቀባይነት የሚያጣ ከሆነ በጥናቱ በሁለተኝነት የተለየው አማራጭ ደግሞ ክልሉን በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በመክፈል ከዚህ በፊት ይነሱ የነበሩ የፍተሃዊነት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ ነው።

በጥናቱ በሶስተኝነት የተቀመጠው ሃሳብ ደግሞ ሁለቱ አማራጮች ተግባራዊ የማይሆኑ ከሆነና ሁኔታው ከክልል አልፎ በአገሪቱ ሰላምና አንድነት ላይ ጫና የሚፈጥር ከሆነ ጉዳዩ ለጊዜው ቢቆይና በእርጋታ ቢታይ የሚል ነው። እንደጥናት ቡድኑ ምክትል ሰብሳቢ ከ17 ሺህ በላይ ሰዎች በላይ ለጥናቱ በመረጃ ሰጪነት ተሳትፈዋል።

ምንጭ፦ ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ደቡብ

በ2011 ዓ.ም. በደቡብ ክልል በነበረ አለመረጋጋት በጉራጌ፣ ሲዳማ፣ ከፋ፣ ጎፋና በጌድዖ #ከ50 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ በመዘጋታቸው ከ40 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጣቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተሰማ ዲማ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። «አሁንም ሎካ ብላቴ ዙሪያ ወረዳና ምሥራቅ አርሲ ድንበር አካባቢ ላይ ግጭቶች አሉ፤ ወደ 7 የሚጠጉ የተቃጠሉ ትምህርት ቤቶች አሉ። እዛ አካባቢ አሁንም ተመልሰን ለማስተማር እና የማካካሻ ፕሮግራም ለመስጠት እንቸገራለን የሚሉ ወረዳዎች አሉ» ብለዋል።

Via #DW
@tsegawolde @tikvahethiopia
#ደቡብ

ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበባቸው የትምህርት አይነቶች ዛሬም የቤተሰባችን መነጋገሪያ እንደሆኑ ነው። ከላይ የምትመለከቱት #በደቡብ_ክልል ውስጥ በሚገኙ ሁለት የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተማሪዎች በBiology እና Civics የትምህርት አይነቶች ያስመዘገቡትን ተቀራራቢና ከፍተኛ ውጤት ነው።

🏷አስተያየታቸውን እያካፈሉን ያሉ ወላጆች እና ተማሪዎችም የፈተናዎች ኤጀንሲ የተፈጠረውን ስህተት ወይም ለምን እንዲህ ሊሆን እንደቻለ ጊዜ ወስዶ መመልከት አለበት፤ አንድና ሁለት ትምህርት ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ፈተናውን ሊፈትሸው ይገባል ብለዋል።

@tsrgabwolde @tikvahethiopia
#ደቡብ_ኮሪያ

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ ኮርያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተዘጋጀ የእራት ግብዣ ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ጋር ተገናኙ። ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የኮሚኒቲ አባላቱ በመደመር እሴቶች ላይ በማተኮር ባሉበት ሆነው ሀገራቸውን እንዲረዱ አበረታትተዋል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚ/ር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
5ኛው አመት የTIKVAH-ETH የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ ከነገ ነሃሴ 20 እስከ መስከረም 30 በመላው ሀገሪቱ ይካሄዳል!!

ላለፉት አመታት በአብዛኛውን በከተሞች አካባቢ የሰራነውን ስራ #በማጠናከር ዘንድሮ ደግሞ ከከተማ ውጭ ወደሚገኙ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትኩረታችንን እናደርጋለን።

ምን አይነት መፅሃፍት ነው ከቤተሰባችን አባላት የምናሰባስበው?

•ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ መደበኛ የመማሪያ መፅሃፍትን/Text Book/ እንዲሁም አጋዥ መፅሃፍት ብቻ

•በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ትውልዱን ይጠቅማል፤ እውቀት ያስጨብጣል የምንላቸው መፅሃፍት።

•ትንሹ መስጠት የሚቻለው መፅሃፍ 1

•መፅሃፍቱ የሚገቡት ገጠራማ አካባቢ ለሚገኙ እና በአካል ሄደን ለምንለያቸው ቤተ መፅሃፍት

#እርሶ ምን ማድረግ ይችላሉ??

√ቢያንስ አንድ የመማሪያ መፅሃፍ ለሚወዷት ለኢትዮጵያ መለገስ ይችላሉ። እንዲሁም ከፍተኛ የመፅሃፍት ችግር ያሉባቸው ቦታዎችን በመለየት የማስተባበር ስራ ሊሰሩ ይችላሉ።

•TIKVAH-ETH በሀገሪቱ በየትኛውም አካባቢ ለምትገኙ የበጎ አድራጎት ማህበራት ይህን ሀገራዊ ስራ እንድታግዙ ጥሪውን ያቀርብላችኃል።

•የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ ትልቁን ድርሻ በመውሰድ ከተማራቹባቸው እና ስትጠቀሟቸው ከነበሩት መፅሃፍ መካከል ቢያንስ አንዱን ለመጪው ትውልድ በስጦታ አበርክቱ።

•በStopHateSpeech ጉዞ ተሳታፊ የነበራችሁ የቤተሰባችን አባላት ይህን ለሀገርና ለትውልድ የሚሰራን ስራ በሙሉ አቅማችሁ እንድታግዙ ጥሪ እናቀርባለን።

•በውጭ ሀገር የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት ጠቃሚ ናቸው የምትሏቸው መፅሃፍት በመላክ አልያም እዚህ ሀገር ባላችሁ ወዳጅና ዘመድ መፅሃፍት እንዲገዛ በማድረግ ይህን

#ኦሮሚያ
#አማራ
#ትግራይ
#ደቡብ
#ሱማሌ
#አፋር
#ሀረሪ
#ጋምቤላ
#ቤኒሻንጉል
#አ/አ ከተማ አስተዳደር
#ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር

🏷በማኛውም አይነት ቋንቋ የተዘጋጀ የመማሪያ መፅሃፍ መለገስ ይቻላል!!
-------------------------------------------------------
በአሁን ሰዓት ልየታ ከተደረገባቸው አካባቢዎች መካከል፦

#ራያ_ቆቦ በራያ ቆቦና ዙሪያዋ የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት መፅሃፍት ለመለገስ እና ይህን ስራ ለማስተባበር ከቤተሰባችን አባል #ሉላይ ጋር ይገናኙ፦ +251949256094

#ድሬዳዋ በድሬዳዋ ከተማ እና አካባቢው የምትገኙ ደግሞ ከቤተሰባችን አባል መሃሪ 0915034762/መሃሪ/ ጋር መገናኘት መፅሃፍ መለገስ ትችላላችሁ።

ሌሎች አካባቢዎች ላይ እኛም ለሀገራችን መስራት እንፈልጋለን የምትሉ እውቅና ያላችሁ ማህበራት ካላችሁ መልዕክት አስቀምጡልን @tsegabwolde 0919743630

5ኛው አመት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት የመፅሃፍ ማሰባሰብ ዘመቻ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደቡብ_አፍሪካ

የዛምቢያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የፊታችን ቅዳሜ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ሊያደርገው የነበረውን የወዳጅነት ጨዋታ በአገሪቱ ባለው የዘረኝነት ጥቃት ምክንያት መሰረዙን አስታውቋል።

የጨዋታው መሰረዝ በዛምቢያ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች ላይ በደቡብ አፍሪካ እየደረሰ ባለው የዘረኝነት ጥቃት እና መንግስት ጥቃቱን ለማስቆም ባሳየው ቸልተኝነት ምክንያት መሆኑ ታውቋል።
የዛምቢያ መንግስት የጸጥታው ሁኔታ እስኪሻሻል ድረስ የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌሮች ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዳይጓዙም አስጠንቅቋል።

በተመሳሳይ ዜና...

ታዋቂው የናይጄሪያ ድምፃዊ ቡራን ቦይ በዘርኝነት ጥቃቱ ምክንያት በጭራሽ ወደ ደቡብ አፍሪካ መጓዝ እንደማይፈልግ ተናግሯል።
ናይጄሪያም በደቡብ አፍሪካ ያሉ ዜጎቿ ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም አስጠነቅቃለች።

አቡጃ ባወጣችው መግለጫ በተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ከተሞች የሚገኙ ዜጎቿን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ለመውሰድ መዘጋጀቷን ይፋ አድርጋለች።
የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ጥላቻን የሚያራምዱ ደቡብ አፍሪካዊያን በናይጀሪያዊያን ላይ ያደረሱት ጥቃት መንግስትን በእጅጉ አስቆጥቷልም ተብሏል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት በበኩላቸው በደቡብ አፍሪካ ባሉ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዜጎችን ኢላማ አድርጎ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት አውግዘዋል።

ሊቀ መንበሩ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ወደ ደቡብ አፍሪካ በማቅናት በንግድ ስራ ላይ በተሰማሩ ሰዎች ላይ ንብረት መዝረፍ እና ማውደምን ጨምሮ ሌሎች እየፈፀሙ ያሉ ድርጊቶችን ክፉኛ ኮንነዋል። የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት አጥፊዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመራቸውንም ሊቀ መንበሩ የሚበረታታ ተግባር ነው ብለዋል።

Via #EBC
@tikvahethiopia
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እስካሁን ከ80 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሏል። #ደቡብ_አፍሪካ #SouthAfrica
#ደቡብ_ሱዳን

የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ ም/ሚኒስትር ሀገራቸው የናይል ወንዝን በመጠቀም ሀይል ማመንጫ ግድብ ለመገንባት ዕቅድ ማዘጋጀቷን አሳወቁ።

ም/ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴንግ ዳው ዴንግ ማሌክ ለናሽናል ጋዜጣ በሰጡት ቃል፥ ከዕርስ በርስ ጦርንት የተላቀቀችው ደቡብ ሱዳን ወደ ኢንዱስትሪ መር የገበያ ስርዓት ለመሸጋገር የሚያስችል ሀይል ማመንጫ ግድብ ለመገንባት የሚስችል ገንዘብ አላት ብለዋል።

ፕሮጀክቱ መንግስት ከነዳጅ ሽያጭ በሚያገኘው ገቢ ለመገንባት ዕቅድ ከተያዙ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ መሆኑን ተገልጿል።

ደ/ሱዳን ርካሽ፣ ታዳሽና በሀገሪቱ በየጊዜው የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ መከላከል የሚያስችል የግዙፍ ግድብ ግንባታን በይፋ ለማስጀመር ዕቅድ መያዟን ተናግረዋል፡፡

ሀገሪቱ በየወቅቱ በሚፈጠር የጎርፍ አደጋ፣ በሀይል እጥረት፣ የውሃ እጥረትና በደካማ የመሰረተ-ልማት ችግር እንደምትሰቃይ ጠቅሰዋል።

ወደ ኢንዱስትሪ መሸጋገር የሚቻለው በቅድሚያ የሀይል አቅርቦት አስተማማኝ በሆነ መልኩ ማምረት ሲቻል እንደሆነና ግድቡ የሀይል ፍላጎትን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ግድቡ ምን ያህል ርዝመት፣ ምን ያህል ውሃ መያዝና ምን ያህል ሀይል የሚያመነጩ ተርባይኖች ሊኖሩት እንደሚገባ የሚሳይ መነሻ ዝርዝር ዕቅድ እና ጥናት በሀገሪቱ የመስኖ ሚኒስቴር በኩል መከናወኑ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ደቡብ ሱዳን ይህን ግድብ የመገንባት ሉዓላዊ መብት እንዳላት ምክትል ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እየገነባች ባለው ግድብ ሚነሱ አለመግባባቶች በትብብር መንፈስ በውይይት ሊፈታ ይገባል ብለዋል።

www.thenationalnews.com/world/africa/south-sudan-poised-to-realise-nile-dam-dream-says-minister-1.1248408

#ENA

@tikvahethiopia
በደቡብ፣ ሐረሪ፣ እና ጋምቤላ ክልሎች የ2013 የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል።

#ሐረሪ

በሐረሪ ክልል 56 በሚሆኑ የግል እንዲሁም የመንግስት ትምህርት ቤቶች ነው ተማሪዎች ፈተናው እየወሰዱ የሚገኙት ፤ በአጠቃላይ 5160 ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ተገልጿል።

ፈተናውን ለመስጠት 214 መምህራንና 24 የፈተና ጣቢያዎች መዘጋጀታቸው ተነግሯል።

#ጋምቤላ

በጋምቤላ ክልል ለ8ኛ ክፍል ፈተና 10 ሺህ 319 ወንድ እና 7 ሺህ 639 ሴት ተማሪዎች በድምሩ 17 ሺህ 958 የቀንና የማታ ተማሪዎች ተቀምጠዋል።

ፈተናው እየተሰጠ የሚገኘው በ186 የፈተና ጣቢያዎች ሲሆን 523 ፈታኞች ተሰማርተዋል።

#ደቡብ

በደቡብ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ዞኖች ከዛሬ ጥዋት አንስቶ እየተሰጠ ቢሆንም ምን ያህል ተማሪ ለፈተናው እንደተቀመጠና በስንት ጣቢያ ፈተናው እየተሰጠ እንደሆነ ይፋዊ መረጃ ማግኘት አልተቻለንም።

መረጃው የየክልሎቹ ትምህርት ቢሮ ነው።

@tikvahethiopia