TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ⬇️

‹‹የድርጅቱ #ስያሜ እና #ዓርማ የአማራን ህዝብ አይወክልም በመባሉ ይመከርበታል፡፡››

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ብአዴን ወደፊት የሚመራባቸውን የፖለቲካ መስመሮች ለመወሰን እየመከረ ነው፡፡

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ይመራበት የነበረውን አብዮታዊ ዲሞክራሲ እናሻሽል ወይም አናሻሸል በሚሉ እና ሌሎች መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው፡፡

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በክልሉ ካሉ አመራሮች የሰበሰባቸውን መሰረታዊ የማሻሻያ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር እና ድርጅቱ በቀጣይ ስለሚከተላቸው የፖለቲካ መስመሮች ላይ ለመወሰን እየመከረ ነው፡፡

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና በብአዴን ጽ/ቤት የገጠር ፖለቲካ ና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምግባሩ ከበደ ማዕከላዊ ኮሚቴው በ12ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን በተመለከተ ከፍተኛ ጊዜ ሰጥቶ ይወያል ብለዋል፡፡

ብአዴን ከ11ኛ መደበኛ ጉባኤ በኋላ ባሉት ሶስት ዓመታት የታዩ ለውጦችን ይገመግማል፡፡

ማዕከላዊ ኮሚቴው በ12ኛው መደበኛ ጉባኤ ላይ ድርጅቱ ሊያሻሽላቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ለይቶ ለማቅረብ እንዲቻል ትኩረት ሰጥቶ ይወያያል፡፡

ድርጅቱ ባለፉት ጊዜያት ይመራባቸው የነበሩ ህጎች አንዳንዶቹ ወቅቱን ያላገናዘቡ በመሆኑ እና የድርጅቱ አመራሮችም ቢሻሻሉ ብለው ያቀረቧቸው በመሆኑ ማዕከላዊ ኮሚቴው በጥልቀት ተወያይቶ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል የሚላቸውን ጉዳዮች ውሳኔ በማሳለፍ በጉባየው ላይ ያቀርባል ብለዋል፡፡

ማዕከላዊ ኮሚቴው ሌላው የድርጅቱን የ2011ዓ.ም ዕቅድ እና በጀትን ጨምሮ የጉባኤው ሪፖርት እና የቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በምክክሩ ላይ የድርጅቱ ስያሜ እና አርማ ምን ይሁን በሚሉ ጉዳዮች ላይ ተመክሮ እንደሚወሰን አቶ አቶ ምግባሩ ገልጸዋል፡፡

ድርጅቱ ባለፈው የአመራር ስብሰባው ላይ አመራሮች የድርጅቱ ስያሜ እና አርማ የአማራን ህዝብ አይወክልም የሚሉ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን ማዕከላዊ ኮሚቴውም ይህን ጉዳይ አንድ እልባት ይሰጠዋል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ብአዴን ከሌሎች እህት ድርጅቶች ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ምን መሆን አለበት እና የአማራን ህዝብ ጥቅም ድርጅቱ እንዴት ማስጠበቅ አለበት በሚሉ ጉዳች ላይ የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

©አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀዋሳ⬇️

የደኢህዴን 10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ #በነገው ዕለት እንደሚጀምር የደኢህዴን ማ/ኮሚቴ ፅ/ቤት ኃላፊው አቶ ሞገስ ባልቻ ገለፁ፡፡ አቶ ሞገስ ባልቻ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫቸው፦

የ10ኛው መደበኛ ጉባኤ ዝግጅት መጠናቀቁን፣ #ሀዋሳና ነዋሪዎቿ በተለመደው እንግዳ ተቀባይነት ባህላቸው እንግዶቻቸውን እየተቀበሉ መሆኑን፣ በጉባኤው በክብር #የሚሰናበቱ አመራሮች እንደሚኖሩ፣ የህገ ደንብ፣ #አርማና #ስያሜ ለውጥን የሚመለከት ውይይት እንደሚካሄድና በጉባኤተኛው እንደሚወሰን እንዲሁም አዳዲስ አመራሮች ወደ ድርጅቱ የመሪነት እርከን እንደሚቀላቀሉ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ የደህዴን ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለአራት ቀናት የሚቆየው የደኢህዴን 10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት #በሀዋሳ ከተማ ጀምሯል፡፡ጉባዔው ከሌሎች ጊዜ በተለየ ሁኔታ በክብር የሚሰናበቱ አመራሮች እንደሚኖሩ ተገልጿል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የህገ ደንብ፣ #አርማና #ስያሜ ለውጥን የሚመለከቱ ውይይቶች ይካሄዳሉ ተብሏል፡፡ በ10ኛው የደኢህዴን ጉባዔ አዳዲስ አመራሮች ወደ ድርጅቱ የመሪነት እርከን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia