TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀዋሳ🔝ከአምስት መቶ በላይ የሚሆኑ የማረቆ ብሔረሰብ አባላት ዛሬ በሀዋሳ ከተማ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ፊት ለፊት በመገኘት "ብሄር ተኮር ጥቃት ይቁም" በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡

©dw
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ከ986 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የሚያስገነባው የካንሰርና የልብ ህክምና ማእከልን በተያዘለት ግዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ያለውን ችግር መንግስት በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈልግለት የግቢው ተማሪዎች እየጠየቁ ናቸው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ🔝

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ #ሰላም ተመልሷል። ይህን አስመልክቶ የሰላም መድረክ በግቢው ተሰጋጅቶ ነበር። በዚህ ዝግጅት ላይ የተገኙ ተማሪዎች አንድነትን የሚያጠነክሩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update አሁን ያለውን የፌዴራል ስርዓት አወቃቀር ለመቀየር መሞከር #ያልተጠበቀ ውጤት ሊያስከትል ይችላል ተባለ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ፖሊስ‼️

በአዲስ አበባ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል የሚባለው ሰላማዊ ሰልፍ #ዕውቅና_የሌለው መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለfbc በላከው መግለጫ፥ አንዳንድ ግለሰቦች #ቅዳሜ እና #እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ገልጿል።

ይሁን እንጂ ሰልፉ በከተማ አስተዳድሩም ሆነ በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው መሆኑ ነው የተገለፀው።

በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ችግሮች ሊቀረፉ ይገባል እና የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ እንደግፋለን የሚሉ መነሻ ሃሳቦችን ምክንያት በማድረግ ሊካሄድ የታሰበው ሰልፍ ምንም ዓይነት እውቅና የሌለው መሆኑን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህገ መንግስታዊ መብት ቢሆንም በተጠቀሱት ቀናት ሰልፍ እናደርጋለን የሚሉ አካላት የሰልፉን መነሻ እና መድረሻ ፣ የሰልፉን አስተባባሪዎች ማንነትና አድራሻ እንዲሁም መሰል ተያያዥ ጉዳዮች ለሚመለከተው አካል ባለማሳወቃቸው ምክንያት አስፈላጊውን ጥበቃ ለማድረግ እንደሚቸገር አስታውቋል።

የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ሌሎች ተግባራትን ለማከናወን አስቀድሞ ፕሮግራም የተያዘ ስለሆነ ሰልፍ እናደርጋለን ለሚሉ ወገኖች ጥበቃ ለማድረግ የሰው ኃይል ችግር ሊያጋጥም እንደሚችል ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

ስለሆነም ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው በመሆኑ ሰልፉን የጠሩ ወገኖች ፣ የሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም ህብረተሰቡ እንዲገነዘቡለት ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

በመጨረሻም ይህንን መልዕክት ተላልፎ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ የሚደረግ ከሆነ በህግ አግባብ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቧል፡፡

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስቴር‼️

ትምህርት ሚኒስቴር ነገ #በፍኖተ_ካርታው ዝግጅት ዙሪያ ጋዜጣዊ #መግለጫ ይሰጣል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ለቀጣዮቹ 15 ዓመታት ተግባራዊ የሚሆን አጠቃላይ የትምህርት ፍኖተ ካርታ እያዘጋጀ እንደሆነ ከዚህ ቀደም ተገልጧል፡፡

የፍኖተ ካርታው ዝግጅት ለሚመለከታቸው አካላት በየደረጃው ለውይይት ቀርቦ ግብዓት እንደተሰጠበት ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የፍኖተ ካርታው ዝግጅት የደረሰበትን ደረጃ በሚመለከት ነገ በትምህርት ሚኒስትር የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ 3፡00 ስዓት ጀምሮ የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር #ጥላዬ_ጌቴ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፡- ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እርስ በእርስ ተጋጭተው የ3 ተማሪ ህይወት ጠፋ እየተባለ #በፌስቡክ የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው። ግቢውም ሆነ ከተማው ፍፁም ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።

#ሼር ወላጆቻች ጋር እንዲደርስ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በሰብዓዊ መብት #ጥሰቶች የተጠረጠሩ 5 የፌደራል ፖሊስ፣ 9 የማረሚያ ቤት፣ 2 የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሠራተኞችን ጨምሮ በጠቅላላው 33 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ሲቀርቡ የዛሬው ሦስተኛ ጊዜያቸው ነው፡፡

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልካም ዜና!

ትላንት በታየው ዱክመንተሪ ፊልም ላይ ልጄ #ጠፍቶብኛል ያሉት የአቶ #ዮሃንስ_ተረፈ ልጅ #አቤል_ዮሃንስ የተሳቢ ሺፌር ሲሆን ማታ አፋር ክልል አፍዴራ ላይ ደክመንተሪውን አይቶ ሲያለቅስ አድሮ ዛሬ ጧት በአከባቢው ያለው ህዝብ ወደ አድስ አበባ ሸኝተውታል አባቱ ጋር ዛሬ ይገናኛል።

via~Ali Buna Manche Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️የኢትዮጵያ መንግስት በሞያሌ አካባቢ ያለውን ጉዳይ በአንክሮ እንዲከታተለው የተፈጠረውንም ችግር በአስቸኳይ እንዲፈታው በከተማይቱ የሚፈኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት አሳስበዋል። በከተማው የለየለት "ስርዓት አልበኝነት ነፍሷል ሲሉም አክለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይ🔝በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙሪያ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያስተላለፉት መልዕክት።

"ግፍ ሰርቶ መደበቅ፣ ዘርፎ መንደላቀቅ አይቻልም!"
@tsegabwolde @tikvahethiopia