TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢሳት‼️

የእንግሊዙ የዜና ማሰራጫ ቢቢሲ ኢሳትን በተመለከተ የሰራጨውን #የተሳሳተ ዘገባ ማረሙን ለኢሳት በጻፈው ደብዳቤ ገለጸ።

የቢቢሲ አለም አቀፍ አገልግሎት ዳይሬክተር ጄሚ አንገስ ኢሳት ለጻፈው የቅሬታ ደብዳቤ ትናንት በላኩት ምላሽ ቢቢሲ ባለፈው ወር ባሰራጨው ዘጋባ ኢሳት ሆን ብሎ #የዘር_ግጭት የሚጭር ቪድዮ #አዘጋጅቶ አሰራጭቷል በሚል በቢቢሲ ያቀረበው ዘገባ ያስተላለፈው መልዕክት ትክክል አለመሆኑን በመገንዘብ ማስተካከያ መደረጉን በደብዳቤያቸው ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በእንግሊዝኛ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ እና ኦሮምኛ ቢቢሲ ያቀረበውን ዘገባ ማስተካከሉን አስታውቀዋል።

በማስተካከያውም የተባለው ቪድዮ የተዘጋጀው በሌላ አካላት እንደነበርና ኢሳት ወዲያውኑ ቪድዮውን ማውረዱንና #ይቅርታ መጠየቁን በቢሲ በማስተካከያው ላይ ጨምሯል።

ዳይሬክተሩ ቢቢሲ ማስተካከያ ለማድረግ በመዘግየቱ ይቅርታ ጠይቀው በዚሁ እንግሊዝኛ ተናጋሪ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ተሰራ ያሉትን የተሳሳተ ዘገባ ኢሳትን ለመጉዳት ያለመ ነው የሚል እምነት እንደሌላቸው እምነታቸውን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በትላንት በስቲያ #በሽረ ከተማ ወደ #ሀዋሳ በማምራት ላይ የነበረ የመከላከያ ሰራዊት ኮንቮይ ላይ መንገድ የዘጉ ወጣቶች፣ ከመከላከያ ሀላፊዎች ጋር ተወያዩ። ከውይይቱ በኅላ የመከላከያ ኮንቮዩ ከጫነው ከባድ መሳሪያ ጋር እንዲንቀሳቀስ ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን፣ ወጣቶቹ #ይቅርታ ጠይቀዋል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እየጨፈርን #የናድነውን ቤት እያለቀስን አንሠራውም!"
.
.
"ሁላችንም ዘር አለን፡፡ ዘሩ ግን እኛ #አይደለንም! እኛ #ሰዎች ነን፡፡ ሰውነት #ከመፈጠር እንጂ #ከመወለድ አይጀምርምና ፈጣሪ ዘራችንን ኢትዮጲያ በምትባል ምድር ላይ ዘራው፡፡ ሲዘራው ኢትዮጲያ ማለት ሰዎች መሆኗን አወቅን፡፡ መነጣጠል እስከማንችል ተዋሃድን፡፡ ትናንት የሆነ የሰው ዲስኩር አንዳችንን ካንዳችን ካልለየሁ እያለ ሥያሜ አበጀልን፡፡ ፈጣሪን ለማረም ይመስል እኛም ሆሆሆ ብለን ተቀበልን፡፡ በሕንድ 2032 ብሔረሰብ በሠላም እየኖረ በቻይና 499 ብሔረሰብ በሠላም እየኖረ ምነው እኛ (ሰማኒያዋን) መሸከም አቃተን?ተራ በተራ መግዛታችንን ለበላይነት ተጠቀምንበት? ማንም ከማንም ጋር የሰውነት ጥል ሊኖረው አይችልም የዕውቀት ጥል እንጂ፡፡ ገና ስንወለድ ዘር ምን ይሁን ቋንቋ ምን ይሁን የምናውቀው ነገር አልነበረም፡፡ #የዕውቀት ጥል ደግሞ በጠረጴዛ ዙሪያ እንጂ በጦር ሜዳ አይፈታም፡፡ ምክንያቱም #ይቅርታ እንጂ #በቀል ታሪክን አያርምምና፡፡ ቋንቋ የሚባልን ነገር ከመካከላችን አውጥተን ማሰብ ብንጀምር ዘረኝነት ሃሳብ ላይ እንጂ ደም ላይ እንደሌለ እንረዳለን፡፡ #እየጨፈርን የናድነውን ቤት #እያለቀስን አንሠራውም፡፡ ሁልጊዜ ጥፋት ካደረስን በኀላ እንዳጠፋን ምንረዳ ከሆነ ዞሮ መልሶ አለማወቅ ይሆንብናል፡፡ በመቻቻል ሳይሆን በፍቅር እንኑር መቻቻል አንድ ቀን ያሰለቸናል፡፡ ታገስኩህ ቻልኩህን ያመጣል፡፡ ፍቅር ግን እስከዖሜጋ ይሸከማል፡፡ ከሰውነት በላይ ምን ማንነት ኖሮ፤ የሁሉም መገኛ ያው አዳም ነው ዞሮ፤ የማይሻር ሽረን አይሆኑሽ ሆነናል፤ የማይድን ስናክም የማይሞት ገለናል፡፡አትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለሁላችንም በቂ ናት! እንወዳድ በፍቅር እንኑር፡፡"

©ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ
#ሼር #Share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አ.ሳ.ቴ.ዩ‼️

የመማር ማስተማሩ ሂደት ተቋርጦ የነበረው የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተማሪዎች ተመልሰው ትምህርት እንዲጀምሩ በሴኔት መወሰኑን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር #ለሚ_ጉታ ለfbc እንደተናገሩት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እና መምህራን ትናንት ከተማሪ ወላጆች ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ሴኔቱ ተማሪዎች ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ወስኗል ብለዋል።

ከተማሪ ወላጆች ጋር በተደረገ ውይይትም ወላጆች ተማሪዎች ጥያቄ ቢኖራቸውም ትምህርት #ማቋረጣቸው ተቀባይነት የሌለው መሆኑንና የተፈጠረው ችግርም #እንዳሳዘናቸው መናገራቸውን አንስተዋል።

ወላጆች ለተማሪዎቹ ድርጊት #ይቅርታ እንዲደረግ መጠየቃቸውን ተከትሎም ሴኔቱ ያስተላለፈውን የአንድ ሴሚስተር ቅጣት ማንሳቱን ገልጿል።

በዚህ መሰረትም ከፊታችን ሰኞ የካቲት አራት ጀምሮ ተማሪዎች ወደ ተቋሙ የሚገቡ መሆኑ ነው የተገለፀው።

የተቋሙን የመማር ማስተማር ሂደት ሆነ ብለው ሲያውኩ የነበሩ ተማሪዎች ግን የስነ ምግባር ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርት ማቆማቸውን ተከትሎ  ከጥር 12 ቀን  እስከ 14 ቀን 2011 ዓ.ም  ጊቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጋቸው ይታወሳል ።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እየጨፈርን #የናድነውን ቤት እያለቀስን አንሠራውም!"
.
.
"ሁላችንም ዘር አለን፡፡ ዘሩ ግን እኛ #አይደለንም! እኛ #ሰዎች ነን፡፡ ሰውነት #ከመፈጠር እንጂ #ከመወለድ አይጀምርምና ፈጣሪ ዘራችንን ኢትዮጲያ በምትባል ምድር ላይ ዘራው፡፡ ሲዘራው ኢትዮጲያ ማለት ሰዎች መሆኗን አወቅን፡፡ መነጣጠል እስከማንችል ተዋሃድን፡፡ ትናንት የሆነ የሰው ዲስኩር አንዳችንን ካንዳችን ካልለየሁ እያለ ሥያሜ አበጀልን፡፡ ፈጣሪን ለማረም ይመስል እኛም ሆሆሆ ብለን ተቀበልን፡፡ በሕንድ 2032 ብሔረሰብ በሠላም እየኖረ በቻይና 499 ብሔረሰብ በሠላም እየኖረ ምነው እኛ (ሰማኒያዋን) መሸከም አቃተን?ተራ በተራ መግዛታችንን ለበላይነት ተጠቀምንበት? ማንም ከማንም ጋር የሰውነት ጥል ሊኖረው አይችልም የዕውቀት ጥል እንጂ፡፡ ገና ስንወለድ ዘር ምን ይሁን ቋንቋ ምን ይሁን የምናውቀው ነገር አልነበረም፡፡ #የዕውቀት ጥል ደግሞ በጠረጴዛ ዙሪያ እንጂ በጦር ሜዳ አይፈታም፡፡ ምክንያቱም #ይቅርታ እንጂ #በቀል ታሪክን አያርምምና፡፡ ቋንቋ የሚባልን ነገር ከመካከላችን አውጥተን ማሰብ ብንጀምር ዘረኝነት ሃሳብ ላይ እንጂ ደም ላይ እንደሌለ እንረዳለን፡፡ #እየጨፈርን የናድነውን ቤት #እያለቀስን አንሠራውም፡፡ ሁልጊዜ ጥፋት ካደረስን በኀላ እንዳጠፋን ምንረዳ ከሆነ ዞሮ መልሶ አለማወቅ ይሆንብናል፡፡ በመቻቻል ሳይሆን በፍቅር እንኑር መቻቻል አንድ ቀን ያሰለቸናል፡፡ ታገስኩህ ቻልኩህን ያመጣል፡፡ ፍቅር ግን እስከዖሜጋ ይሸከማል፡፡ ከሰውነት በላይ ምን ማንነት ኖሮ፤ የሁሉም መገኛ ያው አዳም ነው ዞሮ፤ የማይሻር ሽረን አይሆኑሽ ሆነናል፤ የማይድን ስናክም የማይሞት ገለናል፡፡አትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለሁላችንም በቂ ናት! እንወዳድ በፍቅር እንኑር፡፡" ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ

#ሼር #Share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮ-ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከተማ በኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያት በሚሰጣቸው የቴሌኮም አገልግሎቶች ላይ የጥራት ችግር እንዳጋጠመው አስታውቋል፡፡ ቴሌኮሙ የአገልግሎቶች መቆራረጥ ችግር ላጋጠማቸው ደንበኞቹ #ይቅርታ ጠይቋል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ አማራጭ የሀይል ምንጮችን በመጠቀም እየሰራ መሆኑንም የቴሌኮሙ የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት ጨረር አክሊሉ አስታውቀዋል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

ቦይንግ ካምፓኒ ሃላፊነቱን ወሰደ። ቦይንግ ካምፓኒ 346 ሰወች ለሞቱበት በቦይንግ 737 ማክስ 8 ሁለት አውሮፕላኖች ላይ ለደረሱት አደጋዎች ሃላፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቆ በአደጋው ለሞቱ ሰወች ቤተሰቦችም #ይቅርታ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ዛሬ ያወጣውን የመጀመሪያ ደረጃ መግለጫ ተከትሎ ቦይንግ ማምሻውን በሃላፊው በዴኒስ ሙሊንበርግ በኩል በሰጠው መግለጫ የኢንዶኔዥያውም ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የደረሰው አደጋ ከሶፍትዌር ጋር የተያያዘ መሆኑን አምኖ በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ሰወችም ይቅርታ መጠየቁን ዋሽንግተን ፖስት ከደቂቃዎች በፊት ዘግቧል።

Via waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ክልል ለ7 ሺህ 29 የህግ ታራሚዎች #ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ አስታወቁ፡፡ በክልሉ መንግስት ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች በቆይታቸው መልካም ባህሪ ያሳዩ መሆናቸው ጉዳዩን የሚመለከተው ቦርድ እንዳረጋገጠ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

ይቅርታው በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በዘር ጭፍጨፋ፣ በደን ጭፍጨፋ እና በሴቶችና ህፃናት ላይ ጥቃት የፈፀሙ አካላትን እንደማይመለከት ነው የተነገረው። ማህበረሰቡም ይቅርታ የተደረገላቸው ሰዎች ከማረሚያ ቤት ውጭ ያለውን ህይወት እስከሚላመዱ ድረስ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የህግ ታራሚዎችም ወደ ማህበረሰቡ ከተቀላቀሉ በኋላ በስራ ለመካስ መስራት እንደሚገባቸው ነው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የተናገሩት። ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎችም ከዛሬ ጀምሮም ህብረተሰቡን መቀላቀል ይጀምራሉ።

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካርታው ነገር...

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቅዳሜ እለት በድረ ገፁ ላይ የወጣውን ካርታ ማን እንዳተመው ለማወቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገለፀ።

የሚኒስትሩ ቃል አቀባይ፣ አቶ ነቢያት ጌታቸው፣ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት እንዴትና በማን ካርታው ድረ ገፃቸው ላይ እንደወጣ ይጣራል ብለዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም ማን እንዳተመው ከተለየ በኋላ አስፈላጊውን እርምጃ እንወስዳለን በማለት ተናግረዋል።

“ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራትም ሆነ ከሌሎች ጋር ላላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ልዩ ትኩረት ትሰጣለች፤ ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተልነው ነው’ ብለዋል።

ሶማሊያን የኢትዮጵያ አካል እንደሆነች የሚያሳይና ለሶማሌ ላንድን እውቅና የሚሰጠው ካርታ ባለፈው ቅዳሜ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ድረ ገፅ ላይ ከታተመ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በርካቶች ሲቀባበሉት ነበር።

ሚኒስትር መሥሪያ ቤቱም ወዲያውኑ ካርታውን ከድረገፁ ላይ በማንሳት #ይቅርታ ጠይቋል።

Via #bbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
2:30 ይጀመራል ተብሎ 5:30 የተጀመረው ስብሰባ...
-----------------------------------------------------------
መሪዎች የሰዓት #ቀጠሮን በማክበር #ለወጣቶች አርአያ ሊሆኑ እንደሚገባ ተቀዳሚ ሙፍቲ ዑመር እድሪስ ጠየቁ። ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ይህን ያሉት ሁለት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ይጀመራል ተብሎ ከረፋዱ አምስት ሰዓት በተጀመረው የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ሰባተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ነው። ለጋዜጠኞች የተሰጠው የመግቢያ ካርድ ላይ “ሰዓት ይከበር” የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት ሰፍሯል። ለዚህም ይመስላል ጋዜጠኞችና ተሳታፊዎች በሰዓቱ ታድመዋል፤ ይሁንና የክብር እንግዶቹ በወቅቱ ሊገኙ ባለመቻላቸው ጉባኤው በሰዓቱ ሊጀመር አልቻለም። የዘገየበትን ምክንያት የገለጸ፣ #ይቅርታ የጠየቀም ሆነ ኃላፊነት የወሰደ አካልም የለም። በጉባኤው የከተማዋ ምክትል ከንቲባና የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትርን ጨምሮ ከፌዴራልና ከከተማ አስተዳደሩ የተወጣጡ እንግዶችና የማህበሩ አባላት ታድመዋል። ተቀዳሚ ሙፍቲ ዑመር በዚሁ ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች የሚካሄዱ ስብሰባዎች በተባሉበት ጊዜ #እንደማይጀመሩ ነው የገለጹት። በተባለበት ሰዓት በመገኘት ቀጠሮ በማክበር መሪዎች ለወጣቶች አርአያ ሊሆኑ እንደሚገባ በመግለጽ አገር፣ ሰላምና አንድነት የጋራ በመሆኑ ወጣቶች አንድነትን በተግባር በማሳየት ሰላምን ሊጠብቁ እንደሚገባም ገልጸዋል።

Via #ENA
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia