TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጋዜጣዊ_መግለጫ : " በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር (Enforced Disappearance) ድርጊት በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል " - የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን @tikvahethiopia
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ( #ኢሰመኮ ) በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች እየጨመረ የመጣውን የአስገድዶ መሰወር (Enforced Disappearance) እና ተይዘው የሚገኙበት ሁኔታ ሳይታወቅ በእስር ላይ የሚገኙ (incommunicada Detention) ሰዎችን ጉዳይ ሲከታተል ከቆየ በኃላ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

ኢሰመኮ ምን አለ ?

- በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በርካታ የአስገድዶ መሰወርን ድርጊት የሚያቋቁሙ ድርጊቶች መከሰታቸውን ተረጋግጧል።

- አብዛኛውን ጊዜ የዚህ ድርጊት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው፣ ከሥራ ቦታ ወይም ከመንገድ ላይ የሲቪልና የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታና ደኅንነት ሠራተኞች ያለ ፍርድ ቤት የመያዣ ትእዛዝ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ወዳልታወቀ ስፍራ እየተወሰዱ እንዲሰወሩ የተደረጉ ሲሆን፣ ከፊሎቹ ከተወሰኑ ቀናት፣ ሳምንታት ወይም ወራት መሰወር በኃላ የተገኙ መሆናቸው የተገለጸ ቢሆንም፣ ሌሎች ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ በግዳጅ እንደተሰወሩ የቀጠሉ ናቸው፡፡

- ከተጎጂዎች መካከል የተወሰኑት ሲያዙ በወንጀል ተጠርጥረው የሚፈለጉ መሆኑ ተነግሯቸው ወደ መደበኛ ፖሊስ ጣቢያ ከተወሰዱ በኋላ የተሰወሩ ሲሆን ከፊሎቹ ደግሞ ምንም ሳይነገራቸው በጸጥታ ኃይሎች ተወስደው የተሰወሩ ናቸው፡፡

ምሳሌ ፦

#1

በአዲስ አበባ ከተማ ከሚያዝያ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ በማስገደድ ተሰውረው ከነበሩ ሰዎች ውስጥ ከተለያየ የጊዜ መጠን መሰወር በኃላ ወደ ፌዴራል ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው የተገኙ ሲኖሩ፣ አስገድደው በተሰወሩበት ወቅት በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ውስጥ " ገላን " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ የቀድሞው ልዩ ኃይል ካምፕ ውስጥ ተይዘው እንደቆዩ ለማወቅ ተችሏል። በአስገድዶ መሰወሩ ወቅት ተፈጽሟል ስለተባለ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ ወይም #የማሰቃየት ተግባር ኮሚሽኑ ምርመራውን ቀጥሏል።

#2

በአማራ ክልል በባሕር ዳር እና በደብረ ብርሃን ከተማ የአስገድዶ መሰወር ሰለባዎች የሆኑ ሰዎችን ጉዳይ ኮሚሽኑ ሲከታተል ቆይቶ ነበር። ከነዚህም ውስጥ አንድ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል " ከሠራዊቱ ከድቷል " በሚል በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ወረብ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወላጅ #አባቱን " ልጅህን አምጣ " በሚል ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በግዳጅ ተወስደው ተሰውረው ከቆዩ በኋላ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ተለቀዋል፡፡

#3

አንድ የቀድሞ የ " ሶማሊ  ክልል  ልዩ  ኃይል " አባል ታኅሣሥ 6 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ከቢሮ ተደውሎለት ለሥራ ጉዳይ ቢሮ እንዲመጣ ተጠርቶ ከሄደ በኋላ በዕለቱ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጅምሮ ስልኩ የተዘጋ ሲሆን ከዚያ ቀን ጀምሮ የት እና ምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ለማወቅ አልተቻለም፡፡

#4

ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ቢያንስ #ሰባት ሰዎች የአስገድዶ መሰወር ድርጊት ሰለባ መሆናቸው ለኢሰመኮ አቤቱታ ቀርቦ ክትትል እየተደረገባቸው ነው።

ከእነዚህ መካከል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጎቡ ሰዮ ወረዳ ነዋሪ የሆነ አንድ ሰው ይገኝበታል፡፡

ይህ ግለሰብ ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. በወረዳው ፖሊስ ከሌሎች ሦስት ጓደኞቹ ጋር ተይዞ ፖሊስ ጣቢያ ከገባ በኋላ ሰኔ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ከሌሎቹ ታሳሪዎች ተለይቶ ነቀምት ከተማ የሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ መዘዋወሩ ለቤተሰብ የተነገረ ቢሆንም ከዚያ ቀን ጀምሮ ያለበትን ቦታ እና ሁኔታ ማወቅ አልተቻለም፡፡

በተመሳሳይ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የምሥራቅ ወለጋ ዞን የኦፌኮ አስተባባሪ የሆነ ሌላ ሰው ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት አካባቢ ላይ ከሚሠራበት መሥሪያ ቤት በመንግሥት #የደኅንነት_ኃይሎች ተይዞ ነቀምት ከተማ በሚገኘው የጸጥታ ቢሮ ውስጥ ታስሮ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት እንደነበረና እጁ በሰንሰለት በመታሰሩ ምክንያት ከቤተሰብ የሚሄድለትን ምግብ ተቀብሎ መመገብ ሲያቅተው ሰዎች የተመለከቱት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ግለሰቡ ከጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ሊገኝ አልቻለም።

ቡራዩ በተለምዶ " አሸዋ ሜዳ " ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊሶች ተይዞ በቡራዩ ወረዳ 3 ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር ውሎ የቆየ አንድ ሰው ከሁለት ወራት የፖሊስ ጣቢያ ቆይታ በኋላ አንድ ቀን ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ (ቀነ በትክክል አልታወቀም) ከሌሎች እስረኞች ተለይቶ መወሰዱ የታወቀ ቢሆንም ፣ ከዚያን ቀን ጀምሮ ያለበትን ቦታ እና ሁኔታ ማወቅ አልተቻለም፡፡

ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ላይ ቁጥራቸው ከሃያ ያላነሱ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በሰሜን ሸዋ ዞን ፣ ሱሉልታ ወረዳ ፣ ለገጦ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ፣ ልዩ ስሙ " ረቡዕ ገበያ " ፣ 04 ቀበሌ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ በመምጣት አንድ ሰው ይዘው የሄዱ ሲሆን፤ በማግስቱ ቤተሰቦቹ ታሳሪውን ለመፈለግ ወታደሮቹ ይኖሩበት ወደነበረው ደርባ ቶኒ፣ አበባ ልማት ካምፕ ቢሄዱም ወታደሮቹ የተያዘው ግለሰብ ያበትን ሁኔታ ሊያሳውቁ ፍቃደኛ አለመሆናቸውን፤ ይልቁንም ለመጠየቅ የሄዱ ሰዎች እስር እና ማስፈራርያ የደረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል። የተያዘው ግለሰብም እስከ አሁን ድረስ ያለበት ሁኔታ እና ቦታ ማወቅ አልተቻለም፡፡

(ሙሉ መግለጫው በዚይ 👉 https://t.iss.one/tikvahethiopia/78928?single ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ፤ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ሰብአዊ መብቶች ሊከበሩና ለግጭቶች ዘላቂ መፍትሔ ለሰላማዊ ውይይት ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል ብሏል።

ኮሚሽኑ ፤ ከሚያዝያ ወር 2015 ዓ/ም ጀምሮ እየተባባሰ የመጣውን የአማራ ክልል የትጥቅ ግጭትና የጸጥታ ችግር እንዲሁም በሰብአዊ መብቶች ላይ ያስከተለውን ተጽዕኖ ሲከታተል መቆየቱንና ይህንኑም አስመልክቶ በነዋሪዎች እና በአካባቢው ላይ ያደረሰውንና የሚያደርሰውን ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ለሰላም አማራጮች ቅድሚያ እንዲሰጥ፣ ሲቪል ሰዎች ለተጨማሪ ጉዳት እንዳይዳረጉ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰቡ አስታውሷል።

ሆኖም ግን የጸጥታ ሁኔታው ከመሻሻል ይልቅ ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. አጋማሽ ጀምሮ እየተባባሰ በመምጣቱ ብዙ የክልሉ አካባቢዎች በግጭት ውስጥ መሆናቸውን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ሲቪል ሰዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን እና ሲቪል ሰዎችና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶች መቋረጣቸውን፣ በቅርቡም የኢንተርኔት አገልግሎት በብዙ የክልሉ አካባቢዎች መቋረጡን፣ ነዋሪዎች በነጻነት ለመንቀሳቀስና ሥራቸውን ለመከወን መቸገራቸውን እንዲሁም የእንቅስቃሴ ገደቦች በአንዳንድ አካባቢዎች መጣላቸውን ለመገንዘብ መቻሉን ኮሚሽኑ አመልክቷል።

ግጭቱ ከሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች በግጭትና በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ፣ እንዲሁም ከጎረቤት ሀገራት ግጭት በመሸሽ የተሰደዱ በክልሉ የሚገኙ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችንም (ስደተኞች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች እንዲሁም ፍልሰተኞች) ለከፍተኛ ችግር የሚዳርግ ነው ብሏል።

ኢሰመኮ ፤ ሁሉም ወገኖች ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ለሰላም አማራጮች ቅድሚያ እንዲሰጡ፣ ግጭቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ፣ የክልሉን ሰላም እና ደኅንነት ለማረጋገጥ በመንግሥት የሚወሰዱ እርምጃዎች በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን ነዋሪዎችን ለበለጠ ጉዳት እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዳይዳርጉ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል።

በተጨማሪም የሚኒስትሮች ም/ ቤት በሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ያወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 በሕገ መንግሥቱና ኢትዮጵያ ተቀብላ ባጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ዕውቅና ያገኙ ሰብአዊ መብቶችን እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርሖችን በተለይም የጥብቅ አስፈላጊነት፣ በማናቸውም ሁኔታ የማይገደቡ መብቶችን የመጠበቅ፣ የተመጣጣኝነት እና ከመድልዎ ነጻ መሆን መርሖችን ባከበረ መልኩ እንዲተገበር አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ፤ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ሰብአዊ መብቶች ሊከበሩና ለግጭቶች ዘላቂ መፍትሔ ለሰላማዊ ውይይት ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል ብሏል። ኮሚሽኑ ፤ ከሚያዝያ ወር 2015 ዓ/ም ጀምሮ እየተባባሰ የመጣውን የአማራ ክልል የትጥቅ ግጭትና የጸጥታ ችግር እንዲሁም በሰብአዊ መብቶች ላይ ያስከተለውን ተጽዕኖ ሲከታተል መቆየቱንና ይህንኑም አስመልክቶ በነዋሪዎች እና…
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰኮ) ፤ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 ላይ ያዘጋጀውን ባለ 26 ገጽ የሰብአዊ መብቶች ትንታኔ እና ዝርዝር ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መላኩን አስታውቋል።

በመጪው ሰኞ ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዋጁ ላይ ለመምከርና ለመወሰን አስቸኳይ ስብሰባ የጠራው የሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት የኮሚሽኑን ምክረ ሐሳቦች በጥንቃቄ አጢኖ ተግባራዊ እንዲያደርጋቸው ኮሚሽኑ ጠይቋል፡፡

ኮሚሽኑ ለምክር ቤቱ በላከው የትንታኔ ሰነድ ላይ እንደተመለከተው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተለይም ፦
- በአዋጁ የተመለከቱ ክልከላዎችና ግዴታዎች፣
- ለመንግሥት የተሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን፣
- የአዋጁ ከባቢያዊና የጊዜ ተፈጻሚነት ወሰን፣
- የሕዝብ ተወካዮች እና ዳኞችን ያለምክር ቤቱ ውሳኔ አለመያዝና መከሰስ ልዩ መብት (mmunity) ሌሎችም ሊገደቡ ስለማይችሉ መብቶች ጥበቃ፤
- በአጠቃላይ የአዋጁ እያንዳንዱ አንቀጾች ከጥብቅ አስፈላጊነት (Necessity) ተመጣጣኝነት (Proportionality) እና ሕጋዊነት (legality) አንጻር አንዲመረመሩ ይጠይቃል፡፡

በተጨማሪም አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በነበሩት ተከታታይ ቀኖች በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ተከስቶ የነበረው የሰላምና ደህንነት ልዩ አደጋ በአሁኑ ወቅት ተወግዶና መደበኛ እንቅስቃሴዎች ወደ ነበሩበት ሁኔታ መመለስ መጀመራቸው በመንግሥት በይፋ የተገለጸ በመሆኑ ምክር ቤቱ ፦ በአሁኑ ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን አስፈላጊነት፣ ከባቢያዊና የጊዜ ተፈጻሚነት ወሰንን በተለይ በጥንቃቄ በማጤን ምክር ቤቱ አዋጁን የሚያጸድቀው ቢሆን ፦

👉 የጊዜ ተፈጻሚነቱ ከአንድ ወር ወይም የተወሰኑ ሳምንታት የበለጠ እንዳይሆን፤

👉 የከባቢያዊ ተፈጻሚነቱም ልዩ አደጋው ተከስቷል በተባለበት ቦታ ብቻ የተገደበ እንጂ በጠቅላላ ሀገሪቱ እንዳይደረግ ኮሚሽኑ ምክረ ሐሳብ አቅርቧል፡፡

(ይህ የተመለከተ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
አስቸኳይ_ጊዜ_አዋጅ_ቁጥር_6_2015_በተመለከተ_ከኢትዮጵያ_ሰብአዊ_መብቶች_ኮሚሽን_ኢሰመኮ_የተሰጠ_ምክረ.pdf
916.4 KB
#EHRC

" የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 " በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የላከው ምክረ ሃሳብ በዚህ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የታሰሩት የምክር ቤት አባላት የት ናቸው ? በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተያዙ የም/ቤት አባላት ታስረውበት ከነበረው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የማቆያ ቦታ እንደሌሉ እና ያሉበትን ቦታ ማወቅ እንዳልቻሉ ከጠበቆቻቸው አንዱ ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ተናግረዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እንዲሁም በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ…
#EHRC

አዋሽ አርባ ላይ ታስረው የሚገኙ አብዛኞቹ እስረኞች ለእስር የተዳረጉት #በብሔር ማንነታቸው ብቻ መሆኑን እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ 5 የኮሚሽኑ ባለሙያዎች የሚገኙበት ቡድን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በቁጥጥር ሥር ውለው አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙትን ታሳሪዎች ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ጎብኝቷል።

እነዚህ ታሳሪዎች ፦
- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ፣
- የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣
- የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ካሳ ተሻገር፤
- ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ፣ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ፤
- የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባል አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ አቶ በለጠ ጌትነት፤
- በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በኃላፊነት ይሠሩ የነበሩት አቶ ከፋለ እሱባለውን ጨምሮ በአጠቃላይ 53 ወንድ እስረኞች ሲሆኑ ከአዲስ አበባ ከተማና ከአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በተለያየ ጊዜ ተይዘው ከነሐሴ 15 ቀን እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የሚገኝ ጊዜያዊ / መደበኛ ያልሆነ ማቆያ ጣቢያ የተወሰዱ ናቸው፡፡

ኮሚሽኑ በተለመደው አሠራሩ መሠረት ታሳሪዎቹን ለብቻቸው አነጋግሯል፣ ቦታውን ጎብኝቷል እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የፖሊስ ኃላፊዎች አነጋግሯል፡፡

የፖሊስ ኃላፊዎች ለኮሚሽኑ እንደገለጹት ፤ ታሳሪዎችን ወደዚህ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ማምጣት ያስፈለገው አዲስ አበባ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ማቆያ ጣቢያ ላይ ከፍተኛ መጣበብ በመፈጠሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ታሳሪዎች ምን አሉ ?

እጅግ አብዛኛዎቹ ታሳሪዎች ብሔራቸው #አማራ፣ እምነታቸው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን መሆኑንና ለእስር የተዳረጉት ደግሞ #በብሔር ማንነታቸው ብቻ መሆኑን እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

ከፊሎቹ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተያዙበትና ቤታቸው በተበረበረበት ወቅት በራሳቸውና በቤተሰብ አባል ላይ ድብደባ፣ ብሔር ተኮር ስድብ፣ ማጉላላት፣ ዛቻና ማስፈራራት እንደደረሰባቸው ሆኖም በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ከሆነ በኋላ የተፈጸመ ድብደባ ወይም አካላዊ ጥቃት አለመኖሩን አመልክተዋል።

ከፊሎቹ በተለይም ከአማራ ክልል ተይዘው የመጡ ሰዎች ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ እንኳን እንደማያውቁ አስረድተዋል።

ታሳሪዎቹ የአዋሽ አርባ አካባቢ እጅግ ከፍተኛ ሙቀት ያለው በመሆኑና ከአካባቢው የአየር ጠባይ እንዲሁም ቦታው የወታደራዊ ካምፕ እንጂ መደበኛ የተጠርጣሪዎች ማቆያ ስፍራ ስላልሆነ ለጤንነታቸው፣ ለደኀንነታቸውና ለሕይወታቸው ሥጋት እንዳላቸው፣ አልባሳትን ጨምሮ ከቤተስብ የሚፈልጉትን አቅርቦት ለማግኘት እንዳልቻሉ፣ ከፊሎቹ በሥራቸውም ሆነ በግል ሕይወታቸው ፈጽሞ በፖለቲካ ነክ ጉዳይ ተሳትፎ እንደሌሉና እንዴት ለእስር እንደበቁ መገረማቸውንና መደንገጣቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ ከፖሊስ ኃፊዎች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን በእስር ወቅት ተፈጽመዋል ስለተባሉ የሥነ ምግባር ጥሰቶች ተገቢው ማጣራት እንዲደረግ፣ ታሳሪዎቹ ከቤተሰብ ለሚፈልጉት አቅርቦት አዲስ አበባ በሚገኘው የፖሊስ ቢሮ አማካኝነት እንዲመቻች፣ ከቤተስብ መገናኛ ስልክና ጉብኝት ለሚፈልጉም በአፋጣኝ እንደሚመቻች መግባባት ላይ ተደርሷል።

(ከኢሰመኮ የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EHRC

" ቀድሞውኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለዓመታት በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ አስቸጋሪ ሕይወት ይመሩ የነበሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች #ለሞት እና #ለአካል_ጉዳት መዳረጋቸው አሳሳቢ ነው " - ራኬብ መሰለ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሶማሊ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ፣ በሁለቱ ክልሎች የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ምክንያት በአካባቢው የተጠለሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና የአካባቢው ነዋሪዎች መጎዳታቸው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።

ኮሚሽኑ ፤ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በባቢሌ አቅራቢያ በኦሮሚያ እና በሶማሊ ክልል የጸጥታ ኃይሎች መካከል የተፈጠረውን የተኩስ ልውውጥ በተመለከተ ተጎጂዎችን፣ የኦሮሚያ እና የሶማሊ ክልል የጸጥታ አካላትን፣ የቆሎጂ መጠለያ ሠራተኞችን እና የሆስፒታል ባለሞያዎችን አነጋግሯል።

በአሁኑ ወቅት ግጭቱ የቆመ ቢሆንም፤ በተኩስ ልውውጡ ወቅት " ቆሎጂ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ " የሚኖሩ ቢያንስ 6 ተፈናቃዮች ተገድለዋል፣ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል እንዲሁም በሌሎች የአካባቢው ሲቪል ሰዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሷል ብሏል።

ስለዚህም ሁለቱ ክልሎች በቅንጅት በመሥራት በአካባቢው ለተከሰተው ግጭት ምክንያት ለሆኑ ጉዳዮች ሰላማዊ መፍትሔ በመስጠት የነዋሪዎችን እና የተፈናቃዮችን ደኅንነት በዘላቂነት የማረጋገጥ ሥራ እንዲሠሩ፣ ለደረሰው ጉዳት ተጎጂዎች እንዲካሱ እና ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ ባለማድረግ በሲቪል ሰዎች ላይ ጉዳት እንዲደርስ ባደረጉ የጸጥታ ኃይሎች አባላት ላይ አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ያስፈልጋል ሲል አሳስቧል።

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተፈጠረው ግጭት ወቅት በሲቪል ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ የነበረባቸው መሆኑን ጠቅሰው “በተለይም ቀድሞውኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለዓመታት በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ አስቸጋሪ ሕይወት ይመሩ የነበሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ለሞት እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸው አሳሳቢ ነው " በማለት ገልጸዋል።

ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ አክለውም " በአፍሪካ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና እገዛን አስመልክቶ የተደረገው የአፍሪካ ሕብረት ስምምነት (ካምፓላ ስምምነት) መሠረት የመንግሥት የጸጥታ አካላት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸውን የመጠለያ ጣቢያዎች ደኅንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ከሚችሉ ተግባራት ሊቆጠቡ ይገባል " ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ ለተፈናቃዮች መቅረብ የጀመረው የምግብ ድጋፍ ተፈናቃዮች የሚገኙበትን አሳሳቢ ሁኔታ በሚመጥን ደረጃ ሊጠናከር ይገባል ብሏል ዛሬ በላከልን መግለጫ።
 
ኮሚሽኑ የምግብ ድጋፍ አቅርቦት ወቅቱን የጠበቀ፣ በቂ፣ ተደራሽ እና የሕፃናትን ፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና አረጋውያንን ልዩ ፍላጎት ያገናዘበ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝቧል።

(ከኢሰመኮ የተላከልን ዝርዝር መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለይም አዲሱ የክልል አደረጃጀት ተከትሎ የተለያዩ አስተዳደሮች እና መዋቅሮች መልሶ መቋቋም ወይም ተያያዥ ውሳኔዎች ሂደት ጋር የሚነሱ የደመወዝ መዘግየት እና ያለመከፈል የተመለከቱ አቤቱታዎችን፣ እንዲሁም ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።

ይህ በተመለከት ከላይ የተያያዘውን መግለጫ ልኮልናል።

@tikvahethiopia
#EHRC

" በወልቂጤ ከተማ ጥቅምት 02 ቀን 2016 ዓ.ም. ለተከሰተው ሁከት እና የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ተጠያቂነት ማረጋገጥ፣ እንዲሁም ለተፈናቃዮች እና ተጎጂዎች አስፈላጊው ድጋፍ እና ካሳ ሊሰጣቸው ይገባል " - የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)

ከኢሰመኮ የተላከ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
Report_of_the_Ethiopian_Human_Rights_Commission_EHRC_and_the_Office.PDF
1.6 MB
#EHRC #UN #ሪፖርት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት ከሐምሌ ወር 2014 ዓ/ም - መጋቢት ወር 2015 ዓ/ም ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች በሽግግር ፍትሕ ጉዳይ ላይ ከተጎጂዎችና ጉዳት ከደረሰባቸው ማኅበረሰቦች ጋር ባደረጉት ምክክር የተገኙ ግኝቶችን በተመለከተ ይፋ ያደረጉት ባለ 90 ገጽ ሪፖርት ከላይ ባለፈው ፋይል ተያይዟል።

@tikvahethiopia