ጅማ ዩኒቨርሲቲ🔝
የጅማ ዩኒቨርስቲ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደረገባቸውን ተቋማት የፊታችን ቅዳሜ ሊያስመርቅ ነው።
ተቋማቱ ለአካባቢው ማህበረሰብም አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸውንና ሙሉ ወጪያቸውን በመንግስት በጀት የተሸፈነ መሆኑን የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር #ፍቅሬ_ለሜሳ ተናግረዋል፡፡
በእለቱ ከሚመረቁት ውስጥ 30 ሺ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው የጅማ የህክምና ማዕከል አንዱ ነው፡፡
የህክምና ማዕከሉ ለጎረቤት አገራት ጭምር አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተገነባ ሲሆን ከ20 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚችል ሰምተናል፡፡
75 ሺ 400 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈውና 40 ሺህ የእግር ኳስ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ያለው ስቴዲየምና የስፖርት አካዳሚ በእለቱ ይመረቃል ተብሏል፡፡
አካዳሚው የኢትዮጵያ ስፖርት ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችሉ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንደሚረዳም ተነግሮለታል፡፡
ዘመናዊ የኮንፍረንስና የሲቪክ ማዕከሎች እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች የሰለጠኑ ተማሪዎችም እንደሚመረቁ ታውቋል፡፡
ተቋማቱ ትምህርት እንዲስፋፋ በማስቻል ምርምር እንዲካሄድና የማህበረሰብ አገልግሎት በማበርከት ዩኒቨርስቲው አገራዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣ የሚያግዙ ናቸው ተብሏል፡፡
ምንጭ፦ ሸገር 102.1 ፎቶ፦ ጅማ ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የፕሮፌሰር ፍቅሬ ለሜሳ መልቀቂያ‼️
"የጅማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር #ፍቅሬ_ለሜሳ ያቀረቡት የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን በነበራቸው ቆይታ ስላበረከቱት አስተዋፆ እያመሰገንኩ በቀጣይም በከፍተኛ የትምህርተ ተቋማት የአመራር አመራረጥ መመርያና አሰራር መሰረት አዲስ ፕሬዝዳንት የሚሰየም ይሆናል።"
ዶ/ር #አሚር_አማን