TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጭልጋ ወረዳ‼️

‹‹በጭልጋ አካባቢ አንድ ሰው ተገድሏል፤ 39 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 50 ቤቶችና 9 ወፍጮ ቤቶች ተዘርፈዋል››

‹‹ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ 153 ሰዎች በተጠርጣሪነት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡›› የማዕከላዊ ጎንደር ዋና አስተዳዳሪ
.
.
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ አካባቢ ‹‹በቅማንት ብሔር ስም በህቡዕ ተደራጅተው የሚነግዱ›› የተባሉ ቡድኖች ትናንት ጥቃት አድርሰዋል፡፡ በጥቃቱ ‹‹የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል፤39 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 50 ቤቶችና 9
ወፍጮ ቤቶች ተዘርፈዋል›› ብለዋል የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ #ብርሃኑ_ጣምያለው፡፡

አቶ ብርሃኑ እንዳሉት ሌሎች 8 ሰዎችም ቆስለዋል፡፡ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ 153 ሰዎች በተጠርጣሪነት መለየታቸውንና ወደ ሕግ ለማቅረብ እንደሚሠራም ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል፡፡

አካባቢው ወደ ከፋ ግጭት እንዳያመራ የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ከፌዴራል ፖሊስና ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት አካባቢውን የማረጋጋት ሥራ እያከናወኑ መሆናቸውንም አቶ ብርሃኑ አብራርተዋል፡፡

ግጭቱን ዘገባው በተጠናቀረበት ወቅት ማስቆም የተቻለ ሲሆን ሙሉ በሙሉ የአካባቢውን ሰላም ወደ ቀደመ ሁኔታ ለመመለስ መስተዳድሩ ከሀገር ሽግሌዎችና ከሃይማኖት አባቶች ጋር አብሮ እየሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ኅብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላምና ደኅንነት ለማደፍረስ የሚጥሩ ኃይሎችን አጥብቆ እንዲያወግዛቸውና ሕግ ፊትም ለማቅረብ በሚደረገው ጥረት ከመንግሥት ጋር በመሆን የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ዋና አስተዳዳሪው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡አሁን ላይ አካባቢው በመረጋጋት ላይ እንደሆነ ከዞኑ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia