TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን አካዳሚ ለሦስት ዓመታት ያሰለጠናቸውን 559 ተማሪዎችን #በማስመረቅ ላይ ይገኛል። በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ #ተወልደ_ገብረማርያም ተገኝተዋል። ከተመራቂዎቹ መካከል 40ዎቹ ፓይለቶች፣ 58 ቴክኒሻን እና 123ቱ ደግሞ ሆስተስ ናቸው። እንዲሁም 286 የሚሆኑት ደግሞ የማርኬቲንግ ባለሙያዎች ሲሆኑ 52 የሚሆኑት ደግሞ የምግብ ዝግጅት ባለሙያ ናቸው ተብሏል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቁር ሳጥኑ ወደ ውጭ ሊላክ ነው‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፈው ዕሁድ የተከሰከሰውን ቦይንግ 737 ማክ 8 አውሮፕላን ጥቁር ሳጥን ለምርመራ ወደ ውጭ ሊለክ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ #ተወልደ_ገብረማርያም ገልጸዋል።

አቶ ተወልደ ከአሜሪካው የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲኤንኤን የቢዝነስ ተንታኝ ሪቻርድ ኩዌስት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የአውሮፕላኑ የመረጃ ሳጥን መመርመሪያ መሳሪያ ስለሌላት ለምርመራ ወደ ውጭ ይላካል።

ጥቁር ሳጥኑ ወደ አሜሪካ ሊላክ ይችላል ወይ የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ተወልደ “መረጃው የለኝም፤ ሆኖም ከቅርበትና ከፍጥነት አኳያ ምናልባት ወደ አውሮፓ ሀገራት ሊላክም ይችላል።” ነው ያሉት።

ባሳለፍነው ዕሁድ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ በረራ በጀመረ በስድስት ደቂቃ ውስጥ በተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ 149 ተሳፋሪዎችና 8 የበረራ ሰራተኞች ሁሉም ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

አቶ ተወልደ ለሪቻርድ ኩዌስት እንዳሉት በአየር ትራፊክ ቁጥጥር የድምፅ መቅጃ መረጃ መሰረት አብራሪው የበረራ ሚዛን ማስጠበቅ ችግር አጋጥሞት ነበር።

በተቀዱ የድምፅ ልውውጦች መሰረት አብራሪው የአውሮፕላኑን የበረራ ሚዛን ለማስጠበቅ ችግር ስላጋጠመው፤ ተመልሶ ለማረፍ ጠይቆ መስመር ቢሰጠውም 2 ሰዓት ከ44 ላይ አውሮፕላኑ ከራዳር ዕይታ ውጭ ሆኗል ነው ያሉት።

ሌላው ለአቶ ተወልደ የቀረበላቸው ጥያቄ አብራሪው ስለ ተከሰከሰው አውሮፕላን የበረራ ቁጥጥር መመሪያ በደንብ ያውቃል ወይ? ስልጠናው ወስዷልን? የሚል ነበር።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ “አዎ በቦይንግ የተዘጋጀ መመሪያ አለ፤ይህ የበረራ መመሪያ ለአብራሪዎቹ እንዲደርሳቸውና ግልፅ እንዲሆንላቸው ተደርጓል፤ የተከሰከሰው አውሮፕላን አብራሪም በበቂ ሁኔታ ስለአዲሱ ቦይንግ ማክስ አውሮፕላኑ የበረራ ደህንነት መመሪያው ግንዛቤ አለው። ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ከሌሎች የተለየ ስለሆነ ሁሉም አብራሪዎች ስልጠና ወስደዋል” ብለዋል።

ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ኢትዮጵያ ውስጥ መከስከሱን ተከትሎ በርካታ ሀገራትና አየር መንገዶች ተመሳሳይ አውሮፕላኖችን ከበረራ አገልግሎት አግደዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia