TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አርፈን ቀሎ🔝

የአንጋፋው የኦሮሞ አርቲስቶች ባንድ አርፈን ቀሎ አባላት ወደ ሀገራቸው #ተመለሱ። ዛሬ አዲስ አበባ የገቡት የባንዱ አባላት 17 ሲሆኑ፥ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በኦሮሚያ ክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና በአድናቂዎቻቸው አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የባንዱ አባላት ከአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን ጀምሮ ህዝቡ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መነቃቃት እንዲፈጥር የበኩላቸውን ሲያበረክቱ ቆይተዋል።

ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው ኢትዮጵያ የገቡት የባንዱ አባላት በአርቲስት አሊ ሸቦ፣ አርቲስት ቱሬ ሌንጮ፣ አርቲስት ሸንተም ሹቢሳ፣ አርቲስት ጃፋር አሊ፣ አርቲስት አደም ሀሩን እና ፕሮፌሰር #ጀማል_ሀሰን ተመርተዋል፡፡

ወደ ሀገር ቤት የተመለሱትን አርቲስቶች ጨምሮ አዳዲስና ነባር የኦሮሞ አርቲስቶችን የሚያሳትፍ የሙዚቃና የጥበብ ኮንሰርት ለጥር 18 ቀን 2011 በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እየተዘጋጀ ይገኛል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምዕራብ ወለጋ‼️

በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው #አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረት #ተመለሱ። በዞኑ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውም ተገልጿል።

የኮማንድ ፖስቱ ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ #ደጀኔ_ገብረማርያም እንደገለጹት በዞኑ በነበረው የፀጥታ ችግር የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ሌሎች ንብረት ተመልሰዋል። ከነዚህም 110 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች፣ 41ሽጉጦችና 20 የእጅ ቦምቦች ይገኙበታል። እንዲሁም 326 ኋላ ቀር ጠመንጃዎችና ከአራት ሺህ የሚበልጡ ጥይቶች መመለሳቸውን አስረድተዋል።

በተጨማሪም 50 በርሜል ነዳጅ፣ 14 የመንግሥትና የግል ተሽከርካሪዎችና 28 የሞተር ቢስክሌቶች መመለሳቸውን አቶ ደጀኔ ተናግረዋል።

የዞኑ ሕዝብ የተዘረፉትን የጦር መሣሪያዎችና ሌሎች ንብረት ለማስመለስ በተደረገው ጥረት ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው መንቀሳቀሱን ገልጸዋል።

በዞኑ በ20 የገጠር ወረዳዎችና ሦስት ከተሞች በተካሄዱት የሰላም ኮንፈረንሶች አንፃራዊ #ሠላም በመስፈኑ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውን አስተባባሪው አስረድተዋል፡፡ በካማሺና የምዕራብ ወለጋ ዞኖች መካከል የሕዝብ ለሕዝብ እንቅስቃሴ መጀመሩንም አመልክተዋል፡፡

የመነ ሲቡ ወረዳ የአስተዳደርና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ #ለታ_አባተ በሰጡት አስተያየት ሕዝቡና ኮማንድ ፖስቱ ባደረጉት ክትትልና ቁጥጥር የጦር መሣሪያዎቹ መመለሳቸው ለዞኑ ሰላምና ጸጥታ መከበር አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡ አሁንም ያልተመለሱትን የጦር መሣሪያዎች ለማስመለስ ተቀናጅቶ እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡

የመንዲ ከተማ የአስተዳርና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ #ዳኖ_ኢተፋ በበኩላቸው የተዘረፉት የጦር መሣሪያዎችና ሌሎች ንብረት መመለሳቸው ለሰላም ያላቸው ፋይዳው ጉልህ ነው ብለዋል። የምዕራብ ኢትዮጵያ ከዚህ ዓመት መግቢያ ጀምሮ በተከሰተው ግጭት ሰላምና ጸጥታው ታውኮ መቆየቱ ይታወሳል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞የካቲት 12/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን 82ኛ ዓመት የመታሰቢያ ስነ ስርዓት በዛሬው እለት ተካሂዷል። መታሰቢያ ስነ ስርዓቱ በተለይ 6 ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰማእታት አደባባይ ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ነው የተካሄደው።
.
.
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጣልያኑ ትጥቅ አምራች ኩባንያ ኤሬአ ጋር የነበረውን ስምምነት ቀይሮ ከእንግሊዙ አምብሮ ኩባንያ ጋር የአራት አመት የትጥቅ ልብስ ማቅረብ ስምምነት ተፈራርሟል።
.
.
በአማራ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም የክልሉ መንግስት ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ #ጥረት_ኮርፖሬሽን የ10 ሚሊዮን ብር የመጀመሪያ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።
.
.
ግሎባል አልያንስ ከምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር #ለተፈናቀሉ 46ሺ ለሚሆኑ ዜጎች 20ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይንም በኢትዮጵያ 6 መቶ ሺ ብር #መለገሱን አስታውቋል።
.
.
በፌደራል ስርዓቱ ላይ ከማንም ጋር #ለድርድር እንደማይቀመጥ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) አስታውቋል። ፓርቲው በትናነትናው እለት ባወጣው መግለጫው፥ ኦዲፒ በአጀንዳነት ይዞ ከሚታገልባቸው ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛው የፌደራል ስርዓቱ ነው ብሏል።
.
.
በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን #ያአበሎ_ወረዳ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
.
.
“ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር” የሽኝት መርሃ ግብር ከነገ በስቲያ በይፋ እንደሚካሄድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።
.
.
ከነገ በስቲያ/ሀሙስ የካቲት 14/2011 ዓ.ም. የሲዳማ ሪፈረንደም ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ በሀዋሳ ከተማ የጠራው #ሰላማዊ_ሰልፍ በመንግስት ፍቃድ አግኝቷል።
.
.
ጥቅምት 4/2011 ዓ/ም ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (#ቴዲ_አፍሮ) በሚሊኒየም አዳራሽ ያቀረበው የሙዚቃ ዝግጅት ደረጃውን በጠበቀ የድምፅ እና የምስል ጥራት #በዲቪዲ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 16 ለገበያ ይቀርባል ተብሏል።
.
.
#የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልኡክ አባላት #ከሀዋሳ_ከተማ ነዋሪዎች ጋር #ተወያይተዋል
.
.
ድሬዳዋ ውስጥ በዓመት 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ የሚያመርት ፋብሪካ #ሊገነባ መሆኑን የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ተገልጿል።
.
.
#ቂሊንጦ_ማረሚያ_ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል በሚል የተጠረጠሩ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመስርቷል።
.
.
በኢፌዲሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሁለተኛ ዙር የ100 ቀን ዕቅድ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተርሩ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ አስታውቀዋል።
.
.
የሱማሊያ ጫት ነጋዴዎች ከኬንያ ጫት ማስገባታቸውን ትተው #የኢትዮጵያን_ጫት ለመግዛት መወሰናቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኻን ዘግበዋል፡፡
.
.
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባደሳደር ዶ/ር #አላስቴይር_ዲቪድ ማክፌይል በዛሬው ዕለት የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው #አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረቶች #ተመለሱ። በዞኑ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውም ተገልጿል።
.
.
የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር በህገወጥ መንገድ ተገንብተዋል ያላቸውን መኖሪያቤቶች ማፍረስ ጀምሯል።
.
.
በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦነግ አባላት ህዝቡን #እየተቀላቀሉ ሲሆን፣ በዞኑ፣ መነ ሲቡ ወረዳ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።
.
.
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ብሄራዊ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት እና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጋራ የተዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ምንጭ፦ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ fbc፣ etv፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፣ wazemaradio፣ የጀርመን ራድዮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia