TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬆️

በአሜሪካ ኮንግረስ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮንግረስማን #ክሪስ_ስሚዝ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው #ለውጥ አድናቆት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የአሜሪካ ኮንግረንስ አባላት ልኡካን ቡድን ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ _ገበየሁ በአዲስ አበባ ተወያይቷል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ በ73ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ
ለመሳተፍ ኒውዮርክ ገብተዋል። ሚኒስትሩ ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን ከተ.መ.ድ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይወያያሉ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ⬇️

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ በ73ኛ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ለአካባቢው ሰላም እና ዘላቂ ልማት ተግታ የምትሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ እንደ ተመድ መስራች አባል ሀገር ለባለብዙ ወገን መድረክ ትኩረት በመስጠት የተ.መ.ድ መርህ እንዲከበር እንዲሁም ተግዳሮቶች እና ስጋቶች እንዲወገዱ በጋራ ትሰራለች ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የተካሄደው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ለሀገሪቱ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ክስተት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ እንዲሁም ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ተሰፋው እንዲፈነጥቅ ያደረገ መሆኑንም ዶ/ር ወርቅነህ አውስተዋል፡፡

የህግ የበላይነት እንዲከበር፣ ፍትህ እንዲሰፍን፣ የአገር ኢኮኖሚ በአግባቡ ለማስተዳደር እንዲቻል፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ የብዙሃኑ ተሳትፎ እንዲረጋገጥ እንዲሁም ዴሞክራሲ እንዲያብብ ለማድረግ መንግስት በስፋት እና በጥልቀት እየሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ
ተናግረዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመራው መንግስት በሁሉም አቅጣጫ የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት እና እንደ ሙስና፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ መልካም አስተዳደር ያሉትን የእድግት ማነቆዎች ለመቅረፍ በርካታ ተግባራት እየከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በቀጠናው የሰላም አየር እንዲነፍስ ያበረከተቸውን አስተዋጽኦም አብራርተዋል።

ለ20 አመታት ያክል በግጭት ላይ የነበሩት ኢትዮጵያና ኤርትራ አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ መክፈታቸው፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ እንዲሁም #ጅቡቲ እና #ኤርትራ ችግሮቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ የተደረገው ጥረት ከቀጠናው አልፎ ለአፍሪካ ሰላም ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ
መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር #ወርቅነህ_ገበየሁ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ካለው የተመድ ስብሰባ ጎን ለጎን የአሜሪካውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ አግኝተው አናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጨማሪ ፎቶዎች⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድና የኤርትራ ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ በጅማ ዞን ሰቃ ጮቆርሳ ወረዳ የሚገኘውን የሰቃ ፏፏቴን ዛሬ ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ላይ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ኃይለማሪያም_ደሳለኝና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ:- የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሞቃድሾ⬆️

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር #ወርቅነህ_ገበየሁ እና የኤርትራ አቻቸው #ኦስማን_ሳላህ ዛሬ ለጉብኝት ሞቃድሾ ገብተዋል። ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቆይታቸው ከሶማሊያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኦብነግ⬆️

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ወደ አገር ቤት ተመልሶ #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከመንግስት ጋር መስማማቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ ገለፁ፡፡

ዶ/ር ወርቅነህ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ “በዛሬው እለት በኤርትራ አስመራ በነበረን አገራዊ ተልኮ ለረጅም አመታት የትጥቅ ትግልን አማራጭ አድርጎ ሲንቀሳቀስ ከነበረው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ጋር ባደረግነው ድርድር ወደ አገር ቤት ተመልሰው በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ ከስምምነት ደርሰናል” ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም በሶማሊያ መዲና ሞቆዲሾ የተፈፀመውን የአሸባሪዎች ጥቃት አወገዙ፡፡ ዶ/ር ወርቅነህ ለሶማሊያ አቻቸው አህመድ ኢሴ አዋድ በላኩት መልዕክት በተሰነዘረው አሰቃቂ የሽብር ጥቃት 53 ንፁኃን ሶማሊያውያን ህይወታቸውን ማጣታቸውን እንዲሁም ከ 100 በላይ የመቁሰል አደጋ በመድረሱ የተሰማቸውን ጥለቅ #ሀዘን ገልጸዋል፡፡ ይህ አሰቃቂና ጭካኔ የተሞላበት የሽብር ጥቃት የፈጸሙ አካላት በጥብቅ አውግዘው ጥቀቱ አሸባሪነት ከሶማሊያም አልፎም የአካባቢው ስጋት መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም ለሶማሊያ ፌዴራል መንግስትና ህዝብ #መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ ዋልታ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር #ወርቅነህ_ገበየሁ በምዕራብ አርሲ ዞን በሻሸመኔ ወረዳ የሚገኘውን የኩየራ ሆስፒታል በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጣሊያን ባለሀብቶች በኢትየጵያ በስፋት ኢንቨስት እንደሚያደርጉ ተገለጸ። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር #ወርቅነህ_ገበየሁ ከጣሊያን ባለሀብቶች ጋር በዛሬው እለት ጥር 13 ቀን 2011ዓም ሮም በተወያየዩበት ወቅት የተገኙት ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በስፋት እንቨስት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የጣሊያኑ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ጨምሮ አስር ባለሀብቶች በተገኙበት ባደረጉት ገለፃ የጣለያን ባለሃብቶቹ በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨሰትመንት አማራጮች በስፋት መዋለንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢ.ፌ.ደ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ በአፍሪካ ህብርት ዋና ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ለመታሰቢያነት የሚቆመውን የንጉስ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ሀውልት ከመመረቁ በፊት ያለውን የሀውልቱን የተከላ ሂደት በቦታው ላይ ተገኝተው ጎብኝተዋል። ሀውልቱ በመጭው እሁድ የካቲት 3 ቀን 2011 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ እና ተሳታፊ የአፍሪካ አገራት መሪወችና የዓለም አቀፍ ድርጅትች ተወካዮች በተገኙበት በይፋ ይመረቃል።

via etv
#TIKVAHETHIOPIA #ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባደሳደር ዶ/ር #አላስቴይር_ዲቪድ ማክፌይል በዛሬው ዕለት የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞የካቲት 12/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን 82ኛ ዓመት የመታሰቢያ ስነ ስርዓት በዛሬው እለት ተካሂዷል። መታሰቢያ ስነ ስርዓቱ በተለይ 6 ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰማእታት አደባባይ ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ነው የተካሄደው።
.
.
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጣልያኑ ትጥቅ አምራች ኩባንያ ኤሬአ ጋር የነበረውን ስምምነት ቀይሮ ከእንግሊዙ አምብሮ ኩባንያ ጋር የአራት አመት የትጥቅ ልብስ ማቅረብ ስምምነት ተፈራርሟል።
.
.
በአማራ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም የክልሉ መንግስት ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ #ጥረት_ኮርፖሬሽን የ10 ሚሊዮን ብር የመጀመሪያ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።
.
.
ግሎባል አልያንስ ከምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር #ለተፈናቀሉ 46ሺ ለሚሆኑ ዜጎች 20ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይንም በኢትዮጵያ 6 መቶ ሺ ብር #መለገሱን አስታውቋል።
.
.
በፌደራል ስርዓቱ ላይ ከማንም ጋር #ለድርድር እንደማይቀመጥ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) አስታውቋል። ፓርቲው በትናነትናው እለት ባወጣው መግለጫው፥ ኦዲፒ በአጀንዳነት ይዞ ከሚታገልባቸው ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛው የፌደራል ስርዓቱ ነው ብሏል።
.
.
በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን #ያአበሎ_ወረዳ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
.
.
“ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር” የሽኝት መርሃ ግብር ከነገ በስቲያ በይፋ እንደሚካሄድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።
.
.
ከነገ በስቲያ/ሀሙስ የካቲት 14/2011 ዓ.ም. የሲዳማ ሪፈረንደም ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ በሀዋሳ ከተማ የጠራው #ሰላማዊ_ሰልፍ በመንግስት ፍቃድ አግኝቷል።
.
.
ጥቅምት 4/2011 ዓ/ም ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (#ቴዲ_አፍሮ) በሚሊኒየም አዳራሽ ያቀረበው የሙዚቃ ዝግጅት ደረጃውን በጠበቀ የድምፅ እና የምስል ጥራት #በዲቪዲ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 16 ለገበያ ይቀርባል ተብሏል።
.
.
#የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልኡክ አባላት #ከሀዋሳ_ከተማ ነዋሪዎች ጋር #ተወያይተዋል
.
.
ድሬዳዋ ውስጥ በዓመት 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ የሚያመርት ፋብሪካ #ሊገነባ መሆኑን የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ተገልጿል።
.
.
#ቂሊንጦ_ማረሚያ_ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል በሚል የተጠረጠሩ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመስርቷል።
.
.
በኢፌዲሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሁለተኛ ዙር የ100 ቀን ዕቅድ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተርሩ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ አስታውቀዋል።
.
.
የሱማሊያ ጫት ነጋዴዎች ከኬንያ ጫት ማስገባታቸውን ትተው #የኢትዮጵያን_ጫት ለመግዛት መወሰናቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኻን ዘግበዋል፡፡
.
.
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባደሳደር ዶ/ር #አላስቴይር_ዲቪድ ማክፌይል በዛሬው ዕለት የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው #አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረቶች #ተመለሱ። በዞኑ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውም ተገልጿል።
.
.
የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር በህገወጥ መንገድ ተገንብተዋል ያላቸውን መኖሪያቤቶች ማፍረስ ጀምሯል።
.
.
በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦነግ አባላት ህዝቡን #እየተቀላቀሉ ሲሆን፣ በዞኑ፣ መነ ሲቡ ወረዳ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።
.
.
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ብሄራዊ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት እና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጋራ የተዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ምንጭ፦ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ fbc፣ etv፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፣ wazemaradio፣ የጀርመን ራድዮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ ሰብሳቢነት ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ.ም በጅቡቲ የተካሄደው 46ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የሚኒስትሮች ካውንስል ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ረዳት ዋና ጸሀፊ ሆነው ተሾሙ። የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ #አንቶኒ_ጉቶሬስ ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን የድርጅቱ ረዳት ዋና ጸሀፊ አድርገው መሾማቸውን በዛሬው እለት የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ.ም ይፋ አድርገዋል። ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ለዚህ ከፍተኛ ሃላፊነት የተሾሙት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እንዲሁም ለደርጅቱ ዘላቂ የልማት ግቦች መሳካት ላደረገችው አስተዋጽኦ ከፍተኛ የመሪነት ሚና በመጫወታቸው ነው።

ምንጭ:- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia