TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#IMF

የዓለም ገንዘብ ድርጅት « IMF» ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እና የምጣኔ ኃብት ችግር ላጋጠማት ኢትዮጵያ ወደ ሦስት ቢሊዮን የሚጠጋ የአሜሪካን ዶላር ሊሰጥ ነዉ። ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ የሚታተመዉ ጋዜጣ «ፋይናንሻል ታይምስ» እንደዘገበዉ የገንዘብ ድርጅቱ የሚሰጠዉ ብድር የኢትዮጵያ የክፍያ ተባለጥን « መዛባትን» ለመደገፍ እና ሃገሪቱ ምጣኔ ኃብትዋን ነፃ ለማድረግ ለምታደርገዉ ጥረት ቴክኒካል ድጋፍ የሚዉል ነዉ ተብሎአል። ብድሩን የዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት ቦርድ ሲያፀድቀዉ ለኢትዮጵያ መሠጠት እንደሚጀምርም «ፋይናንሻል ታይምስ»ጋዜጣ የጠቀሳቸዉ የኢትዮጵያ የገንዘብ ምኒስቲር ዲየታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ቶሊና አስታዉቀዋል።

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#IMF

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ( አይ ኤም ኤፍ) ለኢትዮጵያ የ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ፡፡ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ያጸደቀው ይህ ድጋፍ የኢትዮጵያን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ለመደገፍ  የሚውል  መሆኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#IMF

ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ፥ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገትን ዝግ እንደሚያደርገው ትላንት ይፋ ባደረገው ሪፖርት አሳውቋል።

IMF ፤ የዓለም ምጣኔ ሀብት እ.አ.አ. ባለፈው 2021 በ6.1 ከመቶ ማደጉን አስታውሶ ዘንድሮ ግን ዕድገት የሚኖረው በ3.6 % ብቻ እንደሚሆን ተንብዩዋል።

" ጦርነቱ በምጣኔ ሀብት ላይ ያሳደረው አንድምታ ራቅ እያለም አድማሱንም እያሰፋ ነው " ሲል ገልጿል።

IMF የውጭ ንግድ የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎችን በማስተጓጎል እንዲሁም የነዳጅ እና የምግብ ዋጋ ንረት በማስከተል የዓለም ኢኮኖሚ ወደ አሉታዊ አቅጣጫ እንዲያመራ አድርጓል ሲል አመልክቷል።

ዋናው የIMF ኢኮኖሚስት ፒየር ኦልቪዬ ጉሪንቻስ በጻፉት የዓለም ኢኮኖሚ ትንበያ ሪፖርቱ መግቢያ ፦

" በዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ምክንያት ተንኮታኩቶ የነበረው የዓለም ኢኮኖሚ ጠንከር ብሎ ሊያንሰራራ ተቃርቦ ነበር።

ጦርነቱ መጣና በቅርብ ጊዚያት የተገኙ አብዛኞቹን ስኬቶች ጠራርጎ የሚያጠፋ ሁኔታ ፈጠረ።" ሲሉ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ፤ IMF ከዚህ ቀደም ለዓለም አገራት በሰራው ትንበያ የገደፈውን የኢትዮጵያን ምጣኔ ሐብት የተመለከቱ መረጃዎች በትላንት ሪፖርቱ አካቷል።

እኤአ 2022 የኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብት 3.8 በመቶ ያድጋል ሲል ተንብዩዋል። በ2023 የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ 5.7 በመቶ ያድጋልም ብሏል።

በሸማቾች የዋጋ ግሽበት መለኪያ (Consumer Prices) ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ 26.8 በመቶ የነበረው የሸቀጦች ዋጋ ንረት በተያዘው ዓመት ወደ 34.5 በመቶ እንደሚደርስ የIMF ትንበያ ያሳያል። ይኸ እኤአ 2023 በአንጻሩ 30.5 በመቶ ይሆናል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/IMF-04-20 (VOA, DW, IMF)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ብድር ለማግኘት ድርድር ላይ ናት። እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከ2020 ጀምሮ ምንም ፈንድ ያላገኘችው ኢትዮጵያ ብድር እንዲለቀቅላት ከIMF ተከታታይ ድርድሮች እያካሄደች ነው። ከIMF 3.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንደጠየቀች ተነግሯል። ድርጅቱ ብደሩን ለመስጠት ኢትዮጵያ ብር ከዶላር አንጻር ያለው የመግዛት አቅም #እንዲዳከም ማድረግ እንዳለባት…
#Ethiopia #IMF

ኢትዮጵያ ከIMF ብድር ለማግኘት የብርን የመግዛት አቅም ለማዳከም ትስማማለች ? ሌላ አማራጭ የለም ?

የምጣኔ ሃብቱ ባለሞያ አቶ ያሬድ ኃይለመስቀል ፦

" devaluation የሚቀር አይመስለኝም። በምን ያህል ደረጃ devalue ይደረጋል የሚለው ጥያቄ ነው እንጂ devalue ሳይደረግ IMF / World Bank ገንዘብ ይሰጣል ብዬ እንደ ራሴ አልገምትም።

አማራጭ ፖሊስ በራሱ መጥፎ አልነበረም። ቅደም ተከተሉን አለማስተካከል ነው ትልቁ ስህተት። ለምሳሌ ከሌሎች መጀመር ይቻል ነበር።

liberalization ሊቀድም ይችል ነበር ከdevaluation ፤ liberalization ሲደረግ አዲስ ካፒታል ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ ማድረግ ይቻላል።

በዚህ ሂደት ካፒታል / ዶላር ይገኝ ነበር። ይህ ደግሞ የዶላርም ይሁን የሌላ ውጪ አሳሳቢ አይሆንም ነበር። እዳንም መቀነስ ይቻላል። አሁን ግን እዳ ይጨምራል።

ለምሳሌ ፦ የዛሬ 7 ዓመት ለባቡር ወይም ለሌላ የተበደርነው ዶላር ቢኖር መንግሥት ይጠበቅበት የነበረው 22 ብር ቀረጥ ሰብስቦ ወደ 21 ዶላር ቀይሮ መስጠት ነበር አሁን 56 እና 57 ታክስ መሰብሰብ አለበት።

የኑሮው ውድነት ?

ካለንበት ችግር በመነሳት የብር የመግዛት አቅም እንዲዳከም ቢወሰን በዋጋ ንረት ላይ በኑሮው መወደደ ላይ የሚያደርሰው ተፅእኖ ከባድ ነው።

ብዙ ነገር imported inflation የሚባለው ነዳጅ 39 ብር ነበር አሁን ከ70 በላይ ሆኗል ፤ ማዳበሪያውም ፣ ስንዴውም ፣ መኪናውም በብዛት 21 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት እቃ ወደ ሀገር ይገባል 3 - 4 ቢሊዮን የሚገመት export ታደርጋለች ይሄ ልዩነት ላይ ያለው 17 ቢሊዮን ብር የሚመጣውን እቃ ዋጋ ሊጨምረው ይችላል። ይሄ በእያንዳንዱ ቦታ ተበታትኖ በየሰዉ ኑሮ ላይ ተፅእኖ ያደርጋል።

inflation አሁን ትንሽ ረገብ አለ ቢባልም ከፍተኛ ነው። እንደገና ከፍ ሊል ይችላል።

ካፒታል ያላቸው ሰዎች ምንም ችግር የለባቸውም። ለምሳሌ ነጋዴ እቃ ቢወደድም ቢረክስም ችግር የለበትም የገዛበት ላይ ጨምሮ ነው የሚሸጠው ምናልባት ብዙ ላይሸጥ ይችላል ያ ሊጎዳው ይችላል።

ቁርጥ ያለ ገቢ ያለው ሰው ሊጎዳ ይችላል። ለምሳሌ የዛሬ 7 ዓመት 22 ሺህ ብር ደመወዝ የሚከፈለው ሰው 1000 ዶላር አካባቢ ነው አሁን ግን 450 ነው የሚያገኘው ስለዚህ ደመወዙ 50% ቅናሽ አድርጓል። በሌላ በኩል የመኖሪያ፣ የምግብ ዋጋ ጨምሯል።

ብዙ አማራጭ ያለ አይመስለኝም ከ devalue አንጻር። ያለውን ብር መቀበል ነው። አልያም ብሩን አልፈልግም ብሎ ሌላ አማራጭ መፈለግ ነው። ወይም የሚባለውን አድርጎ የሚያስከትለውን ችግር መፍትሄ መፈለግ ነው። "

ይህ የምጣኔ ሃብት ባለሞያ አስተያየት የተወሰደው ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይገልጻል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ የኢትዮጵያ መንግሥት " በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት " ማስተዋወቁን ይፋ አድርገዋል። ገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓትን ጨምሮ ሌሎቹንም የኢኮኖሚ ሪፎርምን በተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮች በገንዘብ ሚኒስቴር እና በብሔራዊ ባንክ በኩል በየጊዜው ይገለጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። @tikvahethiopia
#IMF : የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ኢትዮጵያ በጠየቀችው ብድር ላይ ለመወያየት ነገ ሰኞ ሐምሌ 22 / 2016 ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ብሎምበርግ ድረገጽ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የመረጃ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ ጋር የምታደርገው ድርድር ከተሳካ በቀጣይ አመታት 10.5 ቢሊዮን ዶላር ልታገኝ እንደምትችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በፓርላማ ቀርበው በነበረበት ወቅት መናገራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አሳውቋል። (ሙሉ መግላጫው ከላይ ተያይዟል) @tikvahethiopia
" 10.7 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ተገኝቷል " - ብሔራዊ ባንክ

ብሔራዊ ባንክ ፥ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች መገኘቱን አሳውቋል።

ባንኩ " የሽግግር ወቅት ወጪዎችንና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ የሚያስከትላቸውን ጫናዎችን ለመቀነስ የሚረዳ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ትልቅ የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች ተገኝቷል " ብሏል።

የገንዘብ ድጋፉ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (#IMF) ፣ ከዓለም ባንክ (WB) እና ከአበዳሪዎች የሚገኘውን እንደሚጨምር አመልክቷል።

ነገር ግን፣ በሁለትዮሽ የማዕከላዊ ባንክ ተቀማጭ (central bank deposits) እና በከረንሲ ልውውጥ (currency swap) መልክ የሚመጣውን 2.8 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንዲሁም ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) እና ከሌሎች ባለብዙ ወገኖች (multilaterals) ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀውንና በሃደት ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት ይፋ የሚደረገውን ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ አያካትትም ብሏል።

ብሔራዊ ባንክ " በዓለም የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ የሚለገሰው ልዩ የገንዘብ እርዳታ የመንግሥትን የሪፎርም ሥራዎችን ጥንካሬ ያገናዘበና በአፍሪካ አህጉር ትልቁ ከሚባሉት የገንዘብ እርዳታዎች አንዱ ነው " ብሎታል።

#NBE #Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 በጀት አመት 971.2 ቢሊዮን ብር በጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ከጸደቀው ገንዘብ ውስጥ ፦ ➡️ 451,307,221,052 ለመደበኛ ወጪዎች ➡️ 283,199,335,412 ለካፒታል ወጪዎች ➡️ 222,694,109,445 ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ➡️ 14,000,000,000 ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ የተመደበ ነው፡፡ @tikvahethiopia
#Ethiopia

ለ2017 የበጀት አመት ተጨማሪ በጀት በቅርቡ ይጸድቃል።

የዘንድሮ በጀት 1.8 ትሪሊየን ብር እንደሚሆን ይጠበቃል።

ይህ መጠን ባለፈው ሰኔ ወር ለ2017 በጀት አመት ከጸደቀው 971 ቢሊየን ብር አንጻር በእጥፍ የሚጨምር ነው፡፡

ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ መጀመሩን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ድጋፍ ማግኘት የጀመረው መንግስት ለውጡን ተከትሎ ሊፈጠሩ የሚችሉትን ጫናዎችን ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡

ከነዚህም ውስጥ #ድጎማ እና #የደመወዝ_ጭማሪ የሚጠቀሱ ሲሆን በተጨማሪም ሌሎች ወጪዎች በአመቱ ሊኖሩ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡

IMF ሰንድ ትንበያ ምን ያሳያል ?

- የመንግስት ወጪ ቀደም ሲል ከጸደቀው 971 ቢሊየን ብር በእጥፍ ሊጨምር ይችላል።

- ይህንን ወጪ ለመሸፈን ከአገር ውስጥ ገቢ 1.3 ትሪሊየን ብር (1.15 ትሪሊየን ብር ከታክስ) 214 ቢሊየን ብር ከውጭ የበጀት ድጋፍ በጥቅሉ 1.52 ትሪሊየን ብር የሚገኝ ይሆናል።

- ከውጭ ከሚገኘው 214 ቢሊየን ብር ብድር እና እርዳታ አምና (2016) ከተገኘው 43 ቢሊየን ብር አንፃር በአምስት እጥፍ (500 በመቶ) ጭማሪ ይኖረዋል።

- ከውጭ ከሚገኘው የበጀት ድጋፍ በተጨማሪም ደግሞ በእርዳታ ተቋማት አማካኝነት የሚፈሰው ሃብት ሲካተትበት በጠቅላላ ወደ 304 ቢሊየን ብር ይደርሳል።

- ወጪ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው 1.8 ትሪሊየን ብር ሲሆን የበጀት ጉድለቱ 270 ቢሊየን ብር ይሆናል።

- ከጠቅላላው የመንግስት ወጪ 1.24 ትሪሊየን ብር የመደበኛ ወጪ ይሆናል። ቀሪው 557 ቢሊየን ብር የካፒታል ወጪ ይሆናል፡፡

ሰኔ መጨረሻ ለ2017 በጀት አመት ፀድቆ ከነበረው 971 ቢሊየን ብር በጀት ውስጥ 358.5 ቢሊየን ብር ወይም ከጠቅላላው በጀት 37 በመቶ የሚሆነው የበጀት ጉድለት ነበር፡፡

ሆኖም በIMF ትንበያ ወጪ ይደረጋል ከተባለው 1.8 ትሪሊየን ብር ውስጥ የበጀት ጉድለቱ ከወር በፊት ተቀምጦ ከነበረው መጠን የሚያንስ ነው፡፡

መረጃው የካፒታል ጋዜጣ ነው።

#Capitalnewspaper #Ethiopia #IMF

@tikvahethiopia
#IMF #Ethiopia

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ሠራተኞች ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የተራዘመ የብድር አቅርቦትን በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ።

አይኤምኤፍ ባወጣው መግለጫ፣ ድርጅቱ በአራት ዓመታት የሚያቀርበው የ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ የብድር አቅርቦትን (Extended Credit Facility) በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ተደርሷል።

ስምምነቱ በይፋ በዓለም አቀፉ ገንዘብ ተቋም ዋና የአመራር ቦርድ ከታየ በኋላ ኢትዮጵያ ወደ 345 ሚሊዮን ዶላር ገደማ እንደምታገኝ ተገልጿል።

" በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመንን ጨምሮ ኢትዮጵያ አገር በቀል የምጣኔ ሃብት ፖሊሲ ማሻሻያ ማድረጓ በጥሩ ሁኔታ ውጤት እያሳየ ነው " ብሏል ተቋሙ በመግለጫው።

በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመን መተግበሩ በትይዩና በይፋዊ ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት በስፋት እያጠበበ እንደሆነ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ያለፈው ዓመት ሐምሌ ላይ በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመንን ለመተግበር ውሳኔ አሳልፎ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ የመጣው በአልቬሮ ፒሪስ የተመራው የልዑካን ቡድን ሲሆን ከተደረሰው የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በኃላ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አልቬሮ ፒሪስ ምን አሉ ?

የአይኤምኤፍ ሠራተኞችና የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣኖች ስምምነት በተቋሙ ዋና የአመራር ቦርድ በቀጣይ ሳምንታት የሚታይ ይሆናል።

ቦርዱ ከተመለከተው በኋላ ኢትዮጵያ በመጀመሪያ 345 ሚሊዮን ዶላር ታገኛለች።

የኢትዮጵያ የምጣኔ ሃብት ማሻሻያ በተለይም በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመን መተግበሩ በትይዩና በይፋዊ ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት በስፋት እያጠበበ ነው።

ለውጡ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት መጠንን በመጨመር ለአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ነው።

ወደፊት የአገር በቀል ምጣኔ ሃብት ፖለሲ ለውጡ የማክሮኢኮኖሚ መረጋጋትና የምጣኔ ሃብት እድገት ያመጣል።

የፖሊሲ ማሻሻያው በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለውን የፋይናንስ ሥርዓት በመለወጥ የዋጋ ንረትን ያረጋጋል ምጣኔ ሃብታዊ እንዲሁም ማኅበራዊ ጠቀሜታ አለው።

ገቢ መጨመርና በመንግሥት ይዞታ ሥር ያሉ ተቋማትን ለማጠናከር የሚደረጉ የፋይናንስ ዘርፍ ለውጦች መንግሥት የሚያወጣውን ወጭ ቅደም ተከተል ለማስተካከልና ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ይረዳሉ።

የዓለም የገንዘብ ተቋምን የምጣኔ ሃብት ፕሮግራም በስኬታማነት በማስተግበር ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ሊመሰገኑ ይገባል።

በአልቬሮ ፒሪስ እና ቡድናቸው ንግግር ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምሕረቱ፣ ከገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ እና ከገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ጋር ነው።

መረጃውን IMFን ዋቢ በማረግ ያጋራው ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia