TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Sidama #Hawassa #Motor

በሀዋሳ ከተማ ከሞተር ሳይክል የታርጋ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ 221 ሞተሮች መያዛቸዉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር እና ስምሪት ክፍል ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በአንፃሩ የሞተር ባለቤቶች ፤ " መንግስት የሞተር ሳይክል ታርጋ የለም ይለናል፤ በሌላ በኩል ደሞ ትራፊክ ፓሊስ ታርጋ የላቹም ብሎ ያሳድደናል " ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል።

አንዳንዶች ደግሞ የቀድሞው የደቡብ ክልል  ታርጋ ወደ ሲዳማ ታርጋ መቀየር አለበት በሚል የመያዝና የማንገላታት ነገርም አለ ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር እና ስምሪት ምክትል ዳይሬክቶሬት ኃላፊ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ ፤ ህብረተሰቡ ህጋዊ  ታርጋ በማዉጣት ህጋዊ ይሆን ዘንድ 221 ሞተሮች መያዛቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ኢንስፔክተር ተስፋዬ አክለውም፤ " የደቡብ ታርጋ አየተያዘ ነዉ " የሚባለዉ #ስህተት መሆኑን በመግለጽ ማንም በነጻነት ማሽከርከር እንደሚችል ገልጸዋል።

" በዚህ ምክንያት የታሰሩ ሞተሮች ካሉ ስህተት ነው፤ ይለቀቃሉ። የደቡብ ክልል ታርጋ እስካልሸጠ እስካለወጠ ድረስ ችግር የለውም " ሲሉ አረጋግጠዋል።

ከአዲስ ታርጋ ጋር በተያያዘ በጹሑፍ ቅሬታቸውን ያቀረቡ የሀዋሳ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፤ " መንግስት የሞተር ሳይክል ታርጋ የለም ይለናል፤ በሌላ በኩል ደሞ ትራፊክ ፓሊስ አባላት ታርጋ የላቹም ብለው ያሳድዱናል። እኔ በግሌ 2% ግብር ከከፈልኩ ወራቶች ተቆጥረዋል ነገር ግን ታርጋ ማግኘት አልቻልኩም የሚመለከተው አካል መፍትኤ ይስጠን፤ ትራፊክ ፓሊስ አባላት እያንገላቱን ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ይህንን አስመልክቶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የሀዋሳ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደስታ ዳንቾ ችግሩ መኖሩን በማመን ችግሩ ከሀገራዊ የዶላር ችግር ጋር ተያይዞ የመጣ (ለታርጋ ማሳተሚያ) መሆኑን አንስተዋል።

" አሁን ላይ ህትመቱ በማለቁ በሚቀጥለዉ ሳምንት ይሰጣል " ብለዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም፥ ታርጋ ያልደረሳቸዉ አሸከርካሪዎች ሪሲት በማሳየት እንዲንቀሳቀሱ የተያዙትም እንዲለቀቁ ከከተማዉ ትራፊክ ፖሊስ አመራሮች ጋር መግባባት ላይ ደርሰናል " ሲሉ ምላሽ  ሰጥተዉናል።

መረጃው የተዘጋጀው በሀዋሳ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia