TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ👆የጅማ ዩኒቨርሲቲ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት¶#StopHateSpeech ሌላው በጅማ ቆይታችን #ሀገርን መውደድ #ታሪክን ከማውቅ ይጀምራልና የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ታሪካዊውን የአባ ጅፋር ቤተመንግስትን ጎብኝተናል።

ምስጋና፦

√ጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና አጠቃላይ አመራሮች
√የጅማ ከተማ ወጣቶች/ቄሮ/
√የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች(በተለይ የዋናው ግቢ እና የJiT ተማሪዎች)

Family of TIKVAH-ETH #Jimma

√Semira Jemal
√Ayanalem Kasa (wande)
√Mekedes Zawude
√Beruk
√Yadani
√Tihitina
√Jarso Haile
√Desta Muhhamed
√Daniel Tadesse
√Bereket
√Mohammed Degisiso (Mame)
√Mohammed Baker
√Sultan Ahamed
√Sinishawu kadir
√mulatu
√Surafel
√Kasahun
√Moges from kito

We want to thanks all who helped to achieve our program of #StopHateSpeech at jimma. And also we want to thanks all who helped us #indirectly.

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

ተማሪ NEIMA TIJANI ABABIYA በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ /የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ/ ፈተና 638 ያስመዘገበች ኢትዮጵያዊት ናት! TIKVAH-ETH በቀጣይ ቀናት አስተያየቷን ይዞ ለመቅረብ ጥረት ያደርጋል። #Jimma #GERA #638

@tsegabwolde @tikvahethiopia
VACANCY⬆️

JIMMA UNIVERSITY AGARO CAMPUS

Via #JIMMA_UNIVERSITY
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#JIMMA---በጅማ ከተማ ከቀን ጀምሮ በአንዳንድ አከባቢዎች አለመረጋጋት እና ውጥረት እንዳለ እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላትም ትኩረት እንዲሰጡ በርካታ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት እየጠቆሙ ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለት በጅማ ከተማ ምንተፈጥሮ ነበር?
የተጣራና ዝርዝር መረጃ ከከተማይቱ ነዋሪዎች እንዲሁም ከከተማው የፀጥታ ኃላፊዎች ጠይቀን የምናቀርብ ይሆል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#JIMMA ጅማ ከተማ ቤተክርስቲያን #ተቃጠለ፤ አገልጋዮችም እየታረዱና እየተገደሉ ነው፤ በሚል በፌስቡክ የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን አሳውቋል። ይህን ስራ እየሰሩ ያሉት ምንም ኃላፊነት የማይሰማቸው አካላት ናቸው ያለው የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን በከተማይቱ ውስጥ ንብረት አልወደመም ሰዎች ላይም ጉዳት አልደረሰም፤ እየተናፈሰ ያለውም በሬ ወለደ ፕሮፖጋንዳ በመልቀቅ ህዝቡን ማደናበር ነው ብሏል። በመሆኑም ሁሉም አካላት የጉዳዩን ጥንስስ አላማን በመረዳት ዋስትና ለሆነዉ ሰላምና አንድነት ተግቶ በመስራት ጅማን #ወደቀድሞ ሰላሟ ለመመለስ እየተደረገ ላለዉ ርብርብ የድርሻውን እንዲወጣ ዞኑ ጥሪ አስተላልፏል።

የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን⬆️
_______________________________________

ከጅማ ከተማ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ዝርዝር እና የተጣሩ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን፦

•ዛሬ በከተማይቱ አንዳንድ አካባቢዎች ለተፈጠረው ውጥረት ምክንያቱ ምንድነው?
•በእርግጥ በከተማው በአሁን ሰዓት በፌስቡክ ላይ እየተወራ እንዳለው የከፋ እና አስጊ ችግር አለ?

📑የከተማይቱን ነዋሪዎች፣ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች እንዲሁም የከተማው የፀጥታ ኃላፊዎች ስለተፈጠረው ሁኔታ ምን ይላሉ? የሚለውን እንዳዘጋጀንና እንደጨረስን ተጨማሪ መረጃ እናቀርባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅማ #JIMMA

•በጅማ ከተማ ምንም ቤተክርስቲያን አልተቃጠለም
•የሃይማኖት አባቶች አልታረዱም፤ አልተገደሉም
•ከፍተኛ እልቂት እየተፈፀመ ነው የሚባለውም ሀሰት ነው።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን👇

√በጅማ ከተማ በሃይማኖት ሽፋን ብጥብጥ ለመፍጠር ሲደረግ የነበረው እንቅስቃሴ በሕዝቡ እና በፀጥታ አካላት ተሳትፎ ከሽፏል።

√በከተማው በሃይማኖት ሽፋን ክልሉን እና ሀገሪቱን ለማመስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላት በሕዝቡ እና በፀጥታ ኃይሎች ድጋፍ ሴራቸው ሊከሽፍ ችሏል።

√"በጅማ ከተማ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተቃጠለ" በሚል የሐሰት ወሬ ሕዝቡን በመቀስቀስ ብጥብጥ ለመፍጠር እና ክስተቱም ወደሌሎች ከተሞች እንዲስፋፋ በተቀናጀ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበር።

የተለያዩ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ለTIKVAH-ETH የተገሩት፦

ስለውጥረቱ መነሻ ተመሳሳይነት ያለው መረጃ አላገኘንም! የሚመለከታቸውን አነጋግረን እናቀርባለን!

•ከትላንት 7:00 ጀምሮ ውጥረት ነበር።

•ቁጥራቸው ብዙ ባልባልም በመኪና ሆነው የሚንቀሳቀሱ አካላት ነበሩ።

•ወጣቶች ቤተክርስቲያን ሲጠብቁ ነው ያደሩት። አሁንም እዛው ናቸው።

•ፖሊስ በከተማው ውስጥ ለየት ያለ እንቅስቃሴ ሲታይ አስቸኳይ መፍትሄ አልሰጠም።

•የተቃጠለ ቤተክርስቲያን የለም፤ ግን ሙከራ ነበር ብለን እናምናለን።

•በፌስቡክ ላይ የሚነገረው ግን በተሳሳተ ምልኩ ነው።

•ፖሊስ ይህን ያህል ውጥረት ሳይፈጠር በከተማው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላትን መቆጣጠር ይችል ነበር።

•አመሻሹን ከቤተክርስቲያን የሚመለሱ አካላት በሚመለሱ ወቅት ግርግር ተፈጥሮ ነበር።

•አንዳንድ ወጣቶች በግርግሩ ውስጥ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

•የከተማይቱን ሁኔታ መንግስት ትኩረት ይስጠው።

•ዛሬም አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ እየሰማን ነው። ውጥረት አለ!

•የከተማው ፀጥታ ኃይል ነገሮች እንዲ ስሳይባባስ ማስቀረት ይችል ነበር፤ ትኩረት አልተሰጠውም።

•ሙስሊሙም ክርስቲያኑም ቤተክርስቲያን እየጠበቀ ነው።

•ያለውን ስጋት ለመቅረፍ መንግስት አስፈላጊውን ትኩረት ይስጥና ይስራ።

•ሚዲያዎችም ከአንድ ወገን ብቻ የሚያቀርቡትን መረጃ ማስተካከል አለባቸው።

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#JIMMA

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ በመግባት ብጥብጥና ሁከት ሊያስነሱ ነበር የተባሉ ወጣቶች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን፣ የከተማው አስተዳደር አስታውቋል፡፡ ወጣቶቹ የተያዙት በአይሱዙ ቅጥቅጥ አውቶብስ ተጭነው ወደ ከተማው ሊገቡ ሲሉ ማክሰኞ ጳጉሜን 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ኬላ ላይ በፀጥታ ኃይል መሆኑን ለሪፖርተር ጋዜጣ የገለጹት፣ የከተማው የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈራ ሽብሩ ናቸው፡፡

ሕዝብን ከሕዝብ ጋር ለማጋጨት ወጥነው ሲንቀሳቀሱ የከተማው መግቢያ ላይ የተያዙትን ወጣቶች በተመለከተ አስቀድሞ ለፀጥታ ኃይል የደረሰ መረጃ በመኖሩ፣ በቀላሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አቶ ተፈራ አስረድተዋል፡፡

‹‹ከተማዋን የጦርነት አውድማ›› ለማድረግ የሚፈልጉ ኃይሎች ለወጣቶቹ ገንዘብ ከፍለው እንዳሰማሯቸው ገልጸዋል፡፡ በቅጥቅጥ አውቶብስ ተጭነው ወደ ከተማዋ ሊገቡ ሲሉ የተያዙት እነዚህ ወጣቶች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ በእጃቸው የያዙት ዱላም ሆነ ሌላ መሣሪያ እንዳልነበረ፣ ከእነሱ አንደበት በተወሰደ መረጃ መሠረት ግን ከተማው ውስጥ ከገቡ በኋላ አስፈላጊውን መሣሪያ በተሰጣቸው ገንዘብ ለመግዛት ተስማምተው ጉዞ መጀመራቸውን አስረድተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-15-3
#JIMMA_UNIVERSITY

"...ለተማሪዎች ትምህርት ሲሰጥ የቆየው በህጋዊ መንገድ መሆኑን እያረጋገጥን ይህንኑ በህግ የተሰጠውን ሥልጣን በመጋፋት ኤጀንሲውና የሥራ ኃላፊዎቹ በማድረግ ላይ ያሉት አግባብ የሌለዉ እንቅስቃሴ ህዝብና መንግስት እንዳይረጋጋ የሚያደርግ በመሆኑ በፅኑ የምናወግዘው ነው"
___________________________________

ለጅማ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ አበባ ካምፓስ ተማሪዎች በሙሉ!

ጉዳዩ፡- ተገቢነት በሌላቸው ጽሁፎችና መግለጫዎች እንዳትደናገሩ ስለማሳሰብ

ዩኒቨርሲቲያችን መንግስት የከፍተኛ ትምህርትን ለማዳረስ የሚያደርገውን ጥረት በማሳካት ረገድ ግንባር ቀደም ሚና ያለው መሆኑ ከሁላችሁም የተሰወረ አይደለም፡፡ የመንግስትን የትምህርት ፖሊሲ ተግባራዊነት ከማረጋገጥ አኳያ ዩኒቨርሲቲያችን በተለያዩ ደረጃዎች የሚሰጠውን ትምህርት አድማስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሰፋ መምጣቱ የቁርጠኝነቱ አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ ይኸውም ዋና መቀመጫው ጅማ ከተማ ሆኖ በአገሪቱ የተለያዩ ስፍራዎችና ከአገር ውጪም በሐርጌሳ ጭምር ካምፓሶችንና የትምህርት ማዕከሎችን ከፍቶ ትምህርቱን በማስፋፋት ላይ የሚገኘውም በዚሁ አግባብ ነው፡፡

ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዩኒቨርሲቲያችን የሚያደርገውን ህጋዊ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍና ለማስቆም የሚሞክሩ አካላት ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ተገንዝበናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-18-2
#JIMMA በጅማ ከተማና አካባቢው የሚኖሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሰከረም 17 የመስቀል ክብረ በዓል የሚከበርበትን ስፍራ ዛሬ በማፅዳት ዝግጁ አደረጉ። በከተማው በዓሉ በሚከበርበት “ሚኒ ሁለገብ ስታዲየም” በተካሄደው የጽዳት ሥራ ላይ አባገዳዎች፣ ሀደ ስንቄዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የጸጥታ አካላትና የወጣት ተወካዮች ተሳትፈዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia