TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈 #የጤናባለሞያዎችድምጽ

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በዘጠኝ ጤና ጣቢያ ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች ከግንቦት 2016 ዓ/ም ጀምሮ ያልተከፈላቸው  የተጠራቀመ የትርፍ ሰዓት ስራ (ዲዩቲ) ክፍያቸው ሳይከፈላቸው እንደቆየ ተናግረዋል።

ክፍያቸው እንዲፈጸምላቸው ተደጋጋሚ የሆነ ጥያቄ ለወረዳው እና ለጤና ጽ/ቤቱ ሲጠይቁ የቆዩ ሲሆን የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ከ6 ወር ክፍያው ውስጥ የ2 ወሩን እንደከፈላቸው ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያቀረቡ የጤና ባለሞያዎች ተናግረዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎች የቀረውን የ4 ወር ክፍያ ለመፈጸም ግን ከወረዳው " በጀት የለንም " የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

ያነጋገርናቸው የጤና ባለሞያዎች " ወረዳው በክልሉ ካሉ የሰላም ወረዳ (ቀጠና) አንዱ ነው የመንግስት ስራ በሁሉም ሴክተር እየተሰራ ነው ያለው የግብር እና የታክስ መሰብሰብ ስራም በአግባቡ እየተሰራ ነው የበጀት እጥረት አጋጠመን የሚባለው በጭራሽ ከእውነት የራቀ ነው " ብለዋል።

" በዞኑ የሚገኙ አጎራባች ወረዳዎችን፣ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር፣ ባቲ ወረዳ፣ አርጎባ ልዩ ወረዳ እና ሌሎችም ወረዳዎች ለባለሙያዎቻቸው የሰሩበትን የትርፍ ሰዓት ክፍያ ከፍለዋል የእኛ በምን ተለይቶ ዘገየ " የሚል ጥያቄን አንስተዋል።

በወረዳው ከሚገኙ ጤና ጣቢያዎች አንዱ ከሆነው " ደጋን " ጤና ጣቢያ ሁለት የጤና ባለሞያዎች ማክሰኞ 03/03/17 ዓም በጸጥታ አካላት ተወስደዋል።

የጤና ባለሞያዎች ለእስር የተዳረጉት ካልተከፈላቸው ክፍያ ጋር በተገናኘ የሰሩበትን የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዲከፈላቸው የሚጠይቅ ጽሁፍ " በሶሻል ሚዲያ አጋርታቹሃል " በሚል ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሯል።

ባለሞያዎቹ ከ4 ቀናት እስር በኋላ ትላንት ምሽት ተፈተዋል።

የቃሉ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን አህመድ ለጤና ባለሞያዎቹ ክፍያው በእርግጥም አለመፈጸሙን አረጋግጠው ያልተከፈላቸው ግን በበጀት እጥረት ምክንያት አለመሆኑን ተናግረዋል።

" ክፍያው የዘገየው በየጤና ጣቢያዎቹ የሚሰጠው አገልግሎት እና የሥራ ጫና የሚለያይ በመሆኑ የሚያድረው የጤና ባለሞያ ቁጥርም ይለያያል በዛ ምክንያት ደረጃ ይውጣለትና በሚሰጡት አገልግሎት እና ባለባቸው የስራ ጫና ልክ ይከፈላቸው ተብሎ ይህንን የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ በወረዳው በሚገኙ በዘጠኙም ጤና ጣቢያዎች እያጣራ ነው ሪፖርቱን እንዳቀረበ ይከፈላቸዋል " ብለዋል።

በሌሎች ትይዩ ወረዳዎች ላይ ከክፍያ ጋር በተያያዘ ተመሳሳይ ችግር የለም ይህ በቃሉ ወረዳ ለምን ተፈጠረ ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ " የእኛ ወረዳ ከሌሎች የጎንዮሽ ወረዳዎች ጋር ለማነጻጸሪያ ቢቀርብ የተሻለ ከፋይ ነው " ብለዋል።

ታሰሩ ስለተባሉት ባለሞያዎች መረጃው እንደሌላቸው ተናግረው በሌላ ጉዳይ ተጠርጥረው ካልታሰሩ በቀር በክፍያው ጉዳይ አይታሰሩም ብለዋል።

" ከተያዙም ሌላ የጸጥታ ስራ ስላለ በዛ ምክንያት ተጠርጥረው ነው የሚሆነው በተባለው ምክንያት ከሆነ ግን አጣርቼ ልጆቹን ትሪት አደርጋለው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM