TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቤንሻንጉል ጉምዝ‼️

በአሶሳ ወረዳ ከ190 በላይ የሚሆኑ የሚሊሺያ አባላት ከክልሉ መንግስት እውቅና ውጭ #ወታደራዊ ስልጠና መውሰዳቸው ተገለፀ። ይህን ባደረጉ አመራሮች ላይም ህጋዊ #እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

በክልሉ የሰላም ግንባታና የፀጥታ ቢሮ የሚሊሺያ ዘርፍ ሃላፊ አቶ #ደርጉ_ዚያድ ለኢቢሲ እንደተናገሩት በክልሉ ደረጃ የሚሊሺያ ሰራዊትን በአዲስ መልክ ለማደራጀት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከሰሞኑ የሚሊሺያ ሰራዊት አባላት ግምገማ የተካሄደ ሲሆን ለውጡን ማስቀጠል የሚችል የሚሊሺያ ሰራዊት መዋቅር ለመዘርጋት በሚያስችል መልኩ ግምገማ ተካሂዷል። በዚህም ከአሶሳ ወረዳ ብቻ 140 የሚሊሺያ አባላት በክብር ተሰናብተዋል። እንዲሁም ሰኔ 17 በአሶሳ ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት የተጠረጠሩ 9 የሚሊሺያ አባላት በህግ #ቁጥጥር ስር ውለዋል።

በአሶሳ ወረዳ 190 የሚሆኑ የሚሊሺያ ሰራዊት ከክልሉ መንግስት እውቅና ውጭ ወታደራዊ ስልጠና ወስደዋል ያሉት አቶ ደርጉ ይህን ባደረጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው ብለዋል። የክልሉን የሚሊሺያ ሰራዊት በአዲስ መልክ ለማደራጀት እየተሰራ መሆኑን አቶ ደርጉ ለኢቢሲ ተናግረዋል።

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ #የእሳት_ቃጠሎ እንዲደርስበት አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በፖሊስ #ቁጥጥር_ስር መዋላቸውን EBC ዘግቧል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ🔝

በባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ #በድጋሜ የእሳት ቃጠሎ ተከሰተ። ባለፋት ሳምንታት ለተከታታይ ስድስት ቀናት እንዲሁ በጥበቃ ቦታው ላይ የዚህ አይነት የእሳት ቃጠሎ በመነሳት ስፋት ያለው በአስታ ደን የተሸፈነ የፓርኩ አካል መውደሙ የሚታወቅ ነው።

በሌሎቹ የጥበቃ ቦታዎቻችንም ቢሆን እንዲሁ የዚህ አይነት ቃጠሎ በሰው ሰራሽ ችግር ምክኒያት በተደጋጋሚ የሚከሰት ሲሆን በመከላከያ ሠራዊት፣ በፌደራል ፓሊስ፣ በፈቃደኛ ወጣቶችና በአካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብ እርብርብ እየተደረገ የተነሳውን እሳት መቆጣጠሩ የተለመደ ነው።

የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በአገራችን ከሚገኙት ከፍተኛ ተራሮች መካከል የቱሉ ዲምቱ እና የሰናቴ ፕላቶዎች የሚገኙበት በመሆኑ አብዛኛው የመሬቱ አካል በአስታ ዛፎች የተሸፈነ ነው። በተጨማሪም የዚህ እጽዋት ዝርያዎች በቀላሉና በፍጥነት በእሳት የሚቀጣጠል ከመሆኑም በተጨማሪ ወደ ስሩ አካባቢ ያለው ግንድ እሳቱን ይዞ ስለሚቆይ የጠፋ ይመስልና ንፋስ ሲያገኝ እንደገና ይቀጣጠላል። ይህ ባህሪው አካባቢውን ከእሳት ለመታደግ አስቸጋሪ ያደርገዋል።

አሁን ላይ በባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ ቀናትን ያስቆጠረ ሲሆን እንደተለመደው እሳቱን ለመቆጣጠር የፀጥታ ሃይሉና ህብረተሰቡ ወደ ቦታው በመሄድ እሳቱን እያጠፋ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪም የቃጠሎውን መንስሄ ለማወቅ በሚደረገው ጥረት የአካባቢው ፓሊስ #የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በህግ #ቁጥጥር_ስር አውሎ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን የፓርኩ ሃላፊ አቶ አስቻለው ገልፀውልናል።

Via ኢ.ዱ.ል.ጥ.ባ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች
ፎቶ፦ TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia