TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

በተለምዶ ሰይጣን ቤት ወይም ፒራሚድ አዲስ እና ባስ አዲስ ክለብ ታሸጉ ፤ 68 ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስነዋሪ ድርጊት እና ትውልድን በሚጎዳ ስራ ላይ የተሰማሩና ሲጠቀሙ የተገኙ 68 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማው አስተዳደር አሳውቋል።

ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በተደረገ #ድንገተኛ_ፍተሻ በተለምዶ #ሰይጣን_ቤት ወይም #ፒራሚድ_አዲስ እና #ባስ_አዲስ_ክለብ በማህበረሰቡ ተቀባይነት የሌላቸው አፀያፊ ድርጊቶች ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲፈፅሙ በመገኘታቸው ቤቶቹ መታቸጋቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እና የሠላምና ፀጥታ ቢሮ በጋራ በመሆን ትላንት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ነው ህገወጥ ተግባራት ሲፈጸምባቸው የተገኙት የምሽት ቤቶች እንዲታሸጉ የተደረገው።

በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ፦

- ከ100 በላይ የሺሻ ዕቃዎች ፣
- በርካታ መዋሰሎች፣
- ከ6 በላይ ሀሺሽ የያዙ እቃዎች እንዲሁም በወቅቱ በቦታው የነበሩ ከ68 በላይ የሚሆኑ ተጠቃሚዎችን እና ወጣቱን በዚህ እኩይ ድርጊት ላይ እንዲሳተፍ ሲያደርጉ የቆዩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማው አስተዳደር ገልጿል።

ነዋሪዎች በየአከባቢያቸው አዋኪና ከማህበረሰቡ ወግና ባሕል ያፈነገጡ አስነዋሪ ድርጊቶች ላይ ወጣቱ እንዲሳተፍ የሚያደርጉ ምሽት ቤቶችንና ግለሰቦችን በማጋለጥ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

#MayorOfficeofAddisAbaba

@tikvahethiopia