TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ‼️

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሱ አካላትን #ለሕግ እንደሚያቀርብ ገለጸ።

ፓርቲው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ ባወጣው መግለጫ ከመረራና እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ የተገኘውን ለውጥ #ለመቀልበስ ስልጣንን ያለአግባብ ተጠቅመው ዘረፋ ሲያካሄዱ የነበሩና አሁን ጥቅሙ የቀረባቸው አካላት በተለያዩ ቦታዎች እሳትን በማቀጣጠልና የሰው ልጆች ላይ መፈፀም የሌለበት ወንጀል እንዲፈጸም፣ ዜጎች እንዲፈናቀሉና የክልላችን ሰላም እንዲናጋ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

የእነዚህ አካላት ሴራ እነሱን በመቅበር የሚጠናቀቅ ይሆናል እንጂ ኦሮሚያን የግጭት ሜዳ ማድረግ አይሳካላቸውም ብሏል ፓርቲው በመግለጫው፡፡

እነዚህ አካላት የተጀመረው የህግ የባላይነትን የማስከበር ስራ እንዲስተጓጎል ሌተ ቀን እየተፍጨረጨሩ ይገኛሉ፡፡

የኦሮሞን የህዝብ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን እርስ በእርስ በማጋጨት የጥፋት እጃቸውን እንደዘረጉ መግለጫው ያትታል፡፡

እንደ ፓርቲው መግለጫ፣ እነዚህ አካላት በቅርቡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልና የሱማሌ ወሰን አካባቢ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ #የግድያ_እርምጃ ወስደዋል፣ ሰላማዊ ዜጎችንም አፈናቅለዋል፣ የተቀናጀ ጦርነት በመክፈትም በኦሮሚያ ፖሊስ ላይ ጉዳት አድርሰዋል ይላል መግለጫው፡፡

በዚህ በሰላማዊ ዜጎችና በኦሮሚያ ፖሊስ ላይ ለደረሰው አሰቃቂ ወንጀል ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ በመግለጫው ገልጿል፡፡

ድርጊቱ በሌቦች፣ ዘራፊዎችና በሰው ልጆች ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላት ላይ መውሰድ ከጀመርነው ሕጋዊ እርምጃ ወደ ኋላ እንደማይመልስ ተገልጿል፡፡

በህዝባችን ላይ ይህንን ጉዳት ያደረሱ አካላት የገቡበት ጉድጓድ ገብተን ለሕግ እናቀርባቸዋለን፤ እንዲሁም እነዚህ አካላት ያላቸውን ኃይል በድጋሚ በማይጠገን መልኩ ሰብረን እንቀብረዋለን ብሏል የፓርቲ መዕከላዊ ኮሚቴ በመግለጫው፡፡
ማንኛውም የሰበአዊ ጥሰት የፈፀሙ አካላት በሕግ የሚጠየቁ መሆኑን የማዕከላዊ ኮሚቴው መግለጫ ያስረዳል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia