TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
* ብሔራዊ ፈተና የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው። በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች በአካዳሚክ ካላንደራቸው ላይ ማስተካከያ እያደረጉ ይገኛሉ። ይህ እየተደረገ ያለው ተማሪዎች ፈተናቸውን በሚወስዱበት ወቅት በቅጥር ግቢዎቹ ውስጥ ማንኛውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ መገኘት ስለሌለበት ነው። በሌላ በኩል ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት #ለሪፖርተር_ጋዜጣ…
#ብሔራዊ_ፈተና

ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ከ50 ኪሎ ሜትር በላይ ለሆኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የትራንስፖርት ወጪን ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች እንደሚሸፍኑ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በሁለት ዙር ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አገልግሎቱ ገልጿል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ለ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኤፍ ቢ ሲ) የሰጡት ቃል ፦

- ፈተና ማተም ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች ከወዲሁ ተጠናቀዋል።

- ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በ50 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ያሉ ተፈታኝ ተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪን በራሳቸው ይሸፍናሉ፤ ከ50 ኪሎ ሜትር ርቀት #በላይ የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች ወጪያቸውን ይሸፍናሉ።

- ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ #የሚፈቀዱላቸው

• መጽሐፍት፣
• ሲያጠኗቸው የነበሩ ማስታወሻወች፣
• የንጽህና መጠበቂያዎች
• የሌሊት ልብስ ከተፈቀዱት ቁሳቁስ መካከል ናቸው።

ተማሪዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ የቀበሌ መታወቂያ ፣ የመፈተኛ ካርድ ወይም አድሚሽን ካርድ መያዝ ይኖርባቸዋል።

- ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ #የሚከለከሏቸው ቁሳቁስ፦

• ማንኛውንም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
• ከጋብቻ ቀለበት ውጪ የተለየ ፈርጥ ያላቸው ቀለበቶች፣
• ሀብሎች ፣
• የጸጉር ጌጦች
• ድምጽ የሚያወጡ ጃኬቶች መያዝ አይቻልም።

- የመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የመኝታና የምግብ አገልግሎት ያመቻቻሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል " - የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ፈተናው ከሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል። ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ…
#ብሔራዊ_ፈተና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ኮማንድ ፖስት በፈተናው ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ፦
• የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣
• የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣
• የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣
• የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፣
• የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
• የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
• የፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ሀላፊዎች እና የክ/ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተናውን ፦

- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤
- ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤
- ኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣
- አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- ፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ በውይይቱ ላይ ተገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የተፈታኞችን መብትና ግዴታዎች አቅርበዋል።

#የተፈታኞች_መብቶች_የሆኑት፡- 

➭ ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት አላቸው።

➭ በየኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽና ትራስ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መጽሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች፣ የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አላቸው።

➭ የኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበር፣ መጻፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት አላቸው።

ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት አላቸው።

#የተፈታኞች_ግዴታ_የሆኑት፡-

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልም ይሁን መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት #ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ቁሳቁሶችን/ዕቃዎችን መያዝ የለበትም።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል ውስጥና በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ  ሲመጣ  አንሶላ፣  ብርድልብስና  የትራስ  ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት።

#ዩኒፎርም ለብሶ መገኘት አለበት።

#ለተፈታኞች_የተፈቀዱ_ነገሮች

➣ አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማር እና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ  ደብተር ፣ የትምህርት መጽሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መጽሐፍት፣ ባዶ ወረቀት

➣ ደረቅ ምግቦች ወይም ሰንዱች ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)

➣ ገንዘብ (ብር)

➣ የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ

➣ የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ የገላ ማድረቂያ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)

#ለተፈታኞች_የተከለከሉ_ነገሮች

⮕ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡

⮕ ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው።

⮕ ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ /ቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና  ሌሎች  ማንኛቸውም  ፎቶ፣  ምስል  እና  ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ  ዙሪያ  ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

⮕ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት  ወይም  መጠቀም  የተከለከለ ነው፡፡

⮕ ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣  ሲጋራ፣  በሓኪም  ማዘዣ  የሌለው  መድኃኒት  (በሽሮፕም ይሁን በታብሌት፣ ህክምና መስጫ መርፌ)) መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

⮕ ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

⮕ ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀረ)

ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ  45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡

⮕ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡

⮕ በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

⮕ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ የተመዘገቡ ሲሆን ፈተናው ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው ይፈተናሉ ፤ ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ ያገኛሉ።

(የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ)

@tikvahethiopia
#ብሔራዊ_ፈተና

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከቀናት በኃላ መሰጠት ይጀምራል።

ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ይታወቃል። ተማሪዎች መብታቸው ፣ ግዴታቸው፣ ወደ ዩኒቨርሲቲ ይዘው መሄድ የሚችሉት እና የተከለከሏቸው ነገሮችን ከላይ በምስሉ በዝርዝር ተቀምጧል።

በተጨማሪም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ቀርቧል።

➤ የመጀመሪያ ዙር (የሶሻል ሳይንስ) ፦

🗓 ከመስከረም 26 - 28 (ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ)

🗓 መስከረም 29 (ኦረንቴሽን ይሰጣል)

🗓 ከመስከረም 30 - ጥቅምት 2 (ፈተና ይሰጣል)

🗓 ከጥቅምት 3 - ጥቅምት 4 (ተፈታኞች ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ)

➤ ሁለተኛ ዙር (የተፈጥሮ ሳይንስ) ፦

🗓 ከጥቅምት 5 - ጥቅምት 6 (ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ)

🗓 ጥቅምት 7 (ኦረንቴሽን ይሰጣል)

🗓 ከጥቅምት 8 - ጥቅምት 11 (ፈተና ይሰጣል)

🗓 ከጥቅምት 12 - ጥቅምት 13 (ተፈታኞች ወደየአከባቢያቸው ይመለሳሉ)

(ትምህርት ሚኒስቴር / የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው። ፈተናው ከዛሬ ታህሳስ 18 ጀምሮ እስከ ታህሳስ 21/2015 ዓ/ም በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል። ተቀባይነት ባገኙ ምክንያቶች በመጀመሪያው ዙር ፈተናውን መውሰድ ያልቻሉ በሁሉም ክልል የሚገኙ ተማሪዎች በሁለተኛው ዙር ለፈተና ይቀመጣሉ። በሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና የማህበራዊ ሳይንስ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች…
#Update #ብሔራዊ_ፈተና

" የፈተናውን ውጤት በአጭር ጊዜ እናሳውቃለን " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አሳውቋል።

አገልግሎቱ ፤ ይህ የፈተና ሥራ በውጤታማነት እንዲጠናቀቅ አወንታዊ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ምስጋና ያቀረበ ሲሆን ለተፈታኞች ደግሞ መልካም ውጤት ተመኝቷል።

" በአጭር ጊዜ ውስጥ የፈተናውን ውጤት የምናሳውቅ ይሆናል " ያለው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ተፈታኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#ብሔራዊ_ፈተና

" እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2015 ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች የፈተና ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ዓ/ም ድረስ ብቻ እንደሚካሄድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

አገልግሎቱ ፥ ማንኛውም የስም፣ የፆታ፣ የተፈጥሮ/የማህበራዊ ዘርፍ እና የፎቶ ማስተካከያ ከፈተና በፊት ስለማይደረግ እያንዳንዱ ተፈታኝና እና መዝጋቢ ትክክለኛነቱን የማጣራትና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት ብሏል።

ይህ መሆን ያለበትም ምዝገባው በበየነ መረብ በመሆኑ በትምህርት ቤት ደረጃ የተካሄደው የምዝገባ መረጃ በቀጥታ በማንም ሳይነካ ወደ ተቋሙ የመረጃ ቋት የሚገባ በመሆኑ ነው ሲል አስረድቷል።

ከሚያዚያ 20/2015 ዓ/ም በኋላ በግለሰብ ወይም በተቋም በኩል የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን #አላስተናግድም ሲል በጥብቅ ያሳሰበው አገልግሎቱ ፥ ፈተናው የሚሰጠው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥና የመፈተኛ ጊዜን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚገለፅ አሳውቋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፥ እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም ያለ ሲሆን ተፈታኞች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#ብሔራዊ_ፈተና

ባለፉት ሁለት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት ግን እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው።

ምን የተቀረ ነገር ኖሮ ነው ? የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከሰሞኑን በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ማብራሪያ ሰጥታዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" የፈተናው ክብደ እና ቅለት ከሆነ ምንም የተቀየረ ነገር የለም።

የፈተና አሰጣጥ እና ዝግጅት ሂደት አለ፤ እራሱን የቻለ ሳይንስ አለው በጣም እንዳይከብድም በጣም እንዳይቀልም።

እስከ ዛሬ ሲሰራ ከነበረው ምንም የተለየ ነገር የለም። የተለየው ፈተና አሰጣጡ ነው።

ፈተና አሰጣጡ ያመጣው ለውጥ ምንድነው ከተባለ ፤ ከዚህ በፊት ፈተናዎች በየትምህርት ቤት ነው የሚሰጡት ፈተና መታተም ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ፣ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ ፈተናዎቹ ይሰረቃሉ።

ፈተና ሲሰረቅ የነበረው በተደራጀ መልክ ነው በክልሎች ፈታኞች በየክልሉ ሲሄዱ ትልቅ ግብዣ ተደርጎ ጉቦ ተሰጥቷቸው ተማሪዎቹ እንዲኮራረጁ ይደረጋል። ውጤቱ ትርጉም ያለው አልነበረም።

እኔ ትምህርት ሚኒስቴር የመጣሁ ጊዜ በሁለተኛው ሳምንት ፈተና ሰጥተን ነበር በድሮው አሰጣት ፎርማት ያኔ ነው የማለፊያ ውጤት 50 በመቶ ነው ብለን ፖሊሲ ያደረግነው ፣በወቅቱ ፈተና አሰጣጡን አልቀየርንም ነበር ያኔ ያለፈው 48% ነው። አንዳንድ ክልሎች 70-80 በመቶ አሳልፈዋል።

በምንም አይነት የተማሪዎቹ ችሎታና ብቃት አይደለም። ... መሰረቅ መኮረጁን ለማወቅ ዳታውን ከተታትሎ ማግኘት ይቻላል፤ ግልፅ ነው።

ፈተናው እራሱ የተማሪዎች ችሎታና ብቃት መለኪያ አልነበረም። ያንን ነው የቀየርነው። ከምንም በፊት የሰራነው በተማሪዎች ጭንቅላት ውስጥ በስርቆት፣ በማጭበርበር  ፣ ሌላ ሰው በማስፈተን ፣ በመኮረጅ የሚገኝ ትምህርት የለም የሚል ነው። ይሄን አውቀው እንደ ችሎታቸው እንዲያጠኑ ነው ያደረግነው።

የዛ ውጤት፣ እንደ ሀገር ያለንበትን ልክ ነው ያሳወቀን። በዚህም ይሄ ነው የትምህርት ስርዓቱ ካልን በኃላ ሪፎርሞችን በተግባር አውለን አንድ ትውልድ ቢበላሽብን ቀጣዩን እንዴት እናድናለን ብለን ነው እየሰራን ያለነው። "

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ በ2014 እና በ2015 በድምሩ 1,741,619 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውስደዋል። ከነዚህ ውስጥ ያለፉት በድምሩ 57,301 ተፈታኞች ናቸው።

በዚህ ልክ ተፈታኝ ተማሪዎች መውደቃቸው ዜጎችን ያስደነገጠ ቢሆንም ከነዚህ ተማሪዎች በፊትም ፈተናው አሰጣጡ በዚህ መንገድ ቢሆን ውጤቱ ከዚህ እንደማይለይና የትምህርት ስርዓቱ ውድቀት ከታች ጀምሮ የመጣ እንደሆነ የሚገልጹ በርካቶች ናቸው።

ለዚህ ውድቀት ደግሞ ሁሉም ባለድርሻ ኃላፊነት እንዳለበትና ተማሪዎቹን ከሚያስተምሯቸው መምህራን ብቃት አንስቶ ፣ የትምህርት ቤቶች የጥራት ጉዳይ፣ የግብዓት አቅርቦት ሁሉ ሊፈተሽ የሚገባው እንደሆነ የሚያመላክት መሆኑ ይነሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ብሔራዊ_ፈተና

" በበይነ መረብ የሳይበር ጥቃት በመፈጸም ፈተናውን ለመስረቅ ጥረት አያደርጉም ብለን እንጠብቅም ፤ ያንን ለመከላከል ዝግጅት ተደርጓል  " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

በበይነ መረብ / #በኦንላይን የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሳይበር ጥቃት እንዳይሰረቅ ዝግጅት መደረጉን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር እሸቱ ከበደ ለኢቢሲ በሰጡት ቃል ፤ " በዚህ ዓለም ምንም አይነት ችግር የሌለበት ነገር የለም። ሁሉም ነገር የራሱ የሆነ ችግር / ጉድለት ይኖረዋል ያለን ምርጫች ግን ችግሩን የመከላከል አቅም ጎን ለጎን መገንባት ነው " ብለዋል።

" በበይነ መረብ የሳይበር ጥቃት በመፈጸም ፈተናውን ለመስረቅ ጥረት አያደርጉም ብለን እንጠብቅም " ያሉት ዋና ዳይሬክቲ ፥ " የሳይበር ደህንነት (ሴክዩሪቲ) ስራዎች ፦
° ሞያው ባላቸው ፣
° መሳሪያዎች ባሏቸው
° አቅም ባላቸው ተቋማት በኩል ተገቢ የሆነ ዝግጅት አድርገን እየሰራን ነው " ሲሉ አሳውቀዋል።

" በማህበራዊ ሚዲያ ስለ ፈተናው ብዥታ ለመፍጠር የሚፈልጉ ፣ ፈተናው ላይ ጥቃት ለመፍጠር የሚያስቡ አካላት ማወቅ ያለባቸው ይሄ #የፖለቲካ#የሃይማኖት ጉዳይ አይደለም ማንም ወላጅ ልጁን አስተምሮ የሚያደርስበት ስለሆነ ሁለት ሶስቴ ማሰብ አለባቸው ፤ ተማሪዎቹ ነገ ለሀገር እዳ እንዳይሆኑ ማሰብ ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።

ከኦንላይን ፈተናው ጋር በተያያዘ ማንም አካል ወላጆችን " ኮምፒዩተር አቅርቡ " አላለም ፤ ሊጠየቁም አይገባም ከተጠየቅም ስህተት ነው ተብሏል።

ፈተና የሚሰጠው መንግሥት በሚያቀርበው አቅርቦት / ኮምፒየተር እንደሆነ ተመላክቷል።

ይህ ማለት የኮምፒዩተር አቅም ኖሯቸው ት/ቤታቸውን ማገዝ የሚፈልጉ ዜጎችን አይችሉም ማለት አይደለም ተብሏል።

የወረቅት ፈተናን በተመለከተ አሁን ላይ ህትመት ወደ መጠናቀቁ ሲሆን ፈተናው ልክ እንዳለፉት ፈተናዎች ደህንነቱ እንዲጠበቅ በቂ ዝግጅት መደረጉ፣ በክፍል ውስጥም ኩረጃ እንዳይኖርና ተማሪዎች በራሳቸውን ሰርተው እንዲያልፉ ካለፈው #በጠነከረ ሁኔታ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ ተገልጿል።

#Ethiopia
#NationalExam
#Grade12

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam " የኦንላይን ፈተናው አልቀረም። የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጿል። ሚኒስቴሩ ይህ በፍጹም ከእውነት የራቀ ሃሰተኛ…
#ተጨማሪ #ብሔራዊ_ፈተና

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በኦንላይን ከሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ጋር በተያያዘ አንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አናግሯል።

አመራሩ ፥ " የኦንላይን ፈተናው አልቀረም " ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል።

በየማህበራዊ ሚዲያው " የኦንላይን ፈተና ቀርቷል ፤ ሁሉም ተፈታኝ ፈተናውን በወረቀት ይወስዳል " እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ፍጹም ሀሰተኛ መረጃ እንደሆነም አረጋግጠዋል።

ተማሪዎች በሀሰተኛ መረጃ ሳይረበሹ ለፈተናው ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት  ፥ የ2016 ዓ.ም የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኦንላንይ እና በወረቀት እንደሚሰጥ አረጋግጧል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ እየቀረበ ያለው መረጃ  ሃሰተኛ ነው ብሏል።

ፈተናው በሁለቱም በወረቀት እንዲሁም በኦንላይን እንደሚሰጥ አሳውቋል።

@tikvahuniversity @tikvahethiopia