TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዩኒቨርሲቲዎች ቀጣይ ሀገራዊ ግዴታ!

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም ትላንት ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዚዳንቶች ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ባደረጉት ውይይት ዩኒቨርስቲዎችን ለኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎች ለይቶ ማቆያና በቫይረሱ ለተያዙት ማገገሚያ እንዲሆኑ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ገምግመዋል፡፡

ፕሮፌሰር ሂሩት በዩኒቨርስቲዎቹ ጥሩ ዝግጁነት መኖሩን ጠቁመው አሁን ያለውን የዶርሚተሪ አቀማመጥ መቀየር ፤ መፀዳጃ እና መታጠቢያ ቤቶችን በበቂ ሁኔታ ማዘጋጀት እንደሚገባና እንዲሁም የምግብ አቅርቦት በዩኒቨርስቲዎች እንደሚሸፈን ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርስቲዎች ካሉባቸው ወረዳዎች ፣ ዞኖች፣ ከተማዎች እና ክልሎች ጤና ቢሮዎች እንዲሁም ከጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ መስራታቸውን እንዲቀጥሉም አሳስበዋል፡፡

#MoSHE
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoSHE

በሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የድህረ ምረቃና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ካሉበት ሆነው በኦንላይን እንዲከታተሉ ዩኒቨርስቲዎቹ እንዲያመቻቹ እና መምህራንም በኦንላይን የሚሰጡ ትምህርቶችን በማመቻቸትና በተለያዩ መንገዶች ተደራሽ በማድረግ እንዲያስቀጥሉ መወሰኑን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አስታውቋል።

የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችም ምርምሮቻቸውን ለማድረግ መረጃ ማሰባሰብ አዳጋች ካልሆኑባቸው በስተቀር የጨረሱት ተለይተው በምርምሮቻቸው ላይ ከአማካሪዎቻቸው ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ የሚወያዩባቸው ፕላትፎርሞች ተዘጋጅተው ተፈፃሚ እንዲሆኑ አቅጣጫ ተቀምጧል።

MORE : @TIKVAHETHMAGAZINE

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoSHE

የኮቪድ 19 የወረርሽኝ ስርጭትን በአጭር ጊዜ ውስጥ መቆጣጠር ካልተቻለ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ፕሮግራማቸውን ወደሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ሊራዘም እንደሚችል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ደቻሳ ጉርሙ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፣ እስከ አሁን ባለው ሁኔታ የዩኒቨርስቲዎች የትምህርት ሂደት እንዴት መሆን እንዳለበት እና ወደ መደበኛው የትምህርት አካሄድ ሂደት መመለስ ይቻል አይቻል የሚለው አልተወሰነም።

ምክንያቱም የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ በጤና ሚኒስቴር ይፋ የሆነው መጋቢት2/2012 ሲሆን ከዛ በኋላ ለአስራ አምስት ቀናት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጊቢያቸው ውስጥ ነበሩ።

ነገር ግን ተማሪዎቹ ወደመጡበት እንዲመለሱ ከተደረጉ አስራ አምስት ቀን እንደመሆኑ ውሳኔ ላይ አልደረስንም ብለዋል።

እንደታሰበው የወረርሽኙ ስርጭት በአጭር ጊዜ መቆጣጠር ካልተቻለ እና ስርጭት መጠኑ በከፍተኛ ሁኔት ከጨመረ በሽታውን ስርጭትን የተማሪዎች ወደ ዩኚቨርስቲው መመለሳቸው ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ማስከተሉ ስለማይቀር የትምህርት ጊዜው ወደሚቀጥለው ዓመት (2013) ሊዘዋወር እንደሚችል ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ግን የወረርሽኙ ስርጭት በአጭር ጊዜ የሚገታ ሆኖ ከተገኘ የእረፍት ጊዜን በመጠቀም ማለትም ወደ ክርምት በመግፋት እና ትምህርት አሰጣጡን በማሸጋሸግ ወደሚቀጥለው ዓመት ማለትም 2013 ሳይገባ በወጣለት መርሃ ግብር ለማገባደድ እንደታሰበ ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

MORE : @TIKVAHETHMAGAZINE

ምንጭ፦ https://addismaleda.com/archives/11140
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoSHE

ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸዉን የሚጀምሩት በተለያየ መደብ ተከፍለዉ እንደሚሆን የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁን ኤፍ ቢሲ አስነብቧል።

ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማሪያም በሰጡት መግለጫ የ2012 የትምህርት ዘመን ማካካሻና ማሟያ ትምህርትን ለመስጠት ተቋማት እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የትምህርት አሰጣጡን በተመለከተ ሳምንቱን በሙሉ እስከ ምሽት የሚከናወን ሲሆን ከ4ተኛ አመት በላይ ያሉና ተመራቂ ተማሪዎች በቅድሚያ እንዲገቡና ትምህርታቸዉን በኦንላይንና በገፅ ለገፅ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ቀድመዉ የገቡት መርሀ ግብራቸውን እንዳጠናቀቁ ከ3ተኛ አመትና ከዚያ በታች ያሉት ተማሪዎች በተመሳሳይ መንግድ ትምህርታቸዉን እንዲከታተሉ ይደረጋል ሲሉ ገልፀዋል።

የከፍተኛ ትምህርትም ይሁን አጠቃላይ ትምህርቱ የገፅ ለገፅ ተግባራዊ የሚደረገዉ የኮሮና ቫይረስ በጤና ሚኒስቴር እንዲሁም በሚመለከታቸዉ አካላት ስጋትነቱ መቀነሱ ሲረጋገጥ መሆኑን ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoSHE

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ ዳይክተሮች እና የስራ ክፍሎች ተወካዮች በተገኙበት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ2012 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2013 ዓ.ም እቅድ ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoSHE

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተከታዩን ብለዋል ፦

- በዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች በየደረጃው ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ የሚያስችል ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው።

- በቅርቡ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በየተራ ተማሪዎቻቸውን ይቀበላሉ።

- በሀገሪቱ ሁሉም ክልል የሚገኙ ተማሪዎች ወደዩኒቨርሲቲ ለማምራት #ዝግጅት ማድረግ አለባቸው።

- በ44 ዩኒቨርሲቲዎች በተደረገ ግምገማ አብዛኛዎቹ ኮሮና ቫይረስን በመከላከል የመማር ማስተማሩን ሂደት ማከናወን በሚችሉበት ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

- የቀሩ ጥቂት ዩኒቨርሲቲዎች በቀጣይ ሳምንት ዝግጅታቸውን እንዲያጠናቅቁ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

- የጤና ፕሮቶኮል እና የሰላም ሁኔታውን የሚያስጠብቅ መመሪያ ተዘጋጅቷል።

- በተጨማሪም በአመቱ ከክህሎት እና እውቀት በተጨማሪ የስብእና ግንባታ ላይ ያተኮሩ ትምህርቶችን በስርአተ ትምህርቱ ይካተታል። (ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoSHE

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በ2013 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና በሠላማዊ መንገድ ለማስቀጠል እንደሚሠራ ገልፀዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ትላንት ባቀረቡት በዩኒቨርሲቲዎች የነበሩ የሠላም ተግዳሮቶች ዳሰሳ ሪፖርት በ2013 በተቋማቱ ሠላም ለማስፈን በልዩ ሁኔታ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ባለፉት የትምህርት ዘመናት በተለይም ደግሞ በ2012 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ሲገጥሙ የነበሩትን ውጫዊና ውስጣዊ የሠላም ፈተናዎችን ለመቅረፍ ዝግጅት መደረጉን ዶ/ር ሳሙኤል ተናግረዋል፡፡

ጽንፍ የረገጡ የፖለቲካ አቋሞች ፣ ሚዛናዊ ያልሆኑ ውስን ሚዲያዎች ፣ አክትቪስቶች ፣ አሁን ባለዉ የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ምክንያት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ፣ የተቋማቱ አቅም ውስንነትና መሰል ጉዳዮች ሠላማዊ መማር ማስተማርን እንዳያዉኩ ብዙ ስራዎች እየተሠሩ እንደሆነ በገለጻው ቀርቧል፡፡

በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በቀጣይነት የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ በየደረጃው ካሉት ባለድርሻ አካት ጋር እንደሚሠራና ለተቋማቱም የተደራጀ ችግር ፈቺ ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ ተጠቅሷል፡፡ (MoSHE)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ተማሪዎች ለደህንነታችሁ"

ወደ ዩኒቨርሲቲ እየሄዳችሁ ያላችሁ ተማሪዎች ካላችሁ ወደ ወላጆቻችሁ አካባቢ ወይም ወደ ተቋማችሁ (ከሁለት አንዱ) ወደ ቀረበው ቦታ ደርሳችሁ እንድትቆዩ መልዕክት ተላልፏል።

ለሁሉም ተቋማት በቂ የሆነ ጥበቃ እንዲደረግላቸው #MoSHE ከሚመለከታቸው ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

እስካሁን ከወላጆቻችሁ አካባቢ ያልተነሳችሁ እና ጉዞ ያልጀመራችሁ ባላችሁበት ቆዩ።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማንኛውም መረጃ ከMoSHE ወይም ከዩኒቨርሲቲያችሁ ፕሬዜዳንት ብቻ ተከታትሉ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ለነበሩ ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ ተገለጸ !

በ2012 ዓ.ም ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ከነገ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

#MoSHE ከአንድ (1) ሳምንት በኋላ ሌሎች ቀሪ ተማሪዎች እንዲገቡ እና በዚህ የትምህርት ዘመን የሚጠበቅባቸውን 3 የትምህርት ሴሜስተር እንዲያጠናቅቁ በቂ ድጋፍ እና ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል ሲል ለኢቲቪ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#MoSHE

በፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ከአቻ (ባቻቸው) ጋር ጥሪ እንዲደረግላቸው ተባለ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በ2012 ዓ.ም በፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ከአቻ (ባቾቻቸው) ጋር ጥሪ ይደረግላቸው ዘንድ ሁሉንም ዩኒቨርሲቲዎች አሳስቧል። ~ EHEISU

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT