TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህግን ተከትለው የሚሰሩ የሪል ስቴት አልሚዎችን እንደሚደግፍ ነገር ግን ህገወጥ የሆኑት ላይ #ዕርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ትናንት ከሪል ስቴት አልሚዎች በመከሩበት መድረክ ላይ እንደተናገሩት፤ የሪልስቴት ዘርፉ የከተማውን የቤት ችግር ለመቅረፍ እንደ አጋዥ ፕሮጀክት የሚጠቅም መሆኑን ገልጸው፤ የከተማ አስተዳደሩ ህግን ተከትለው የሚሰሩ የሪል እስቴት አልሚዎችን እንደሚደግፍ ነገር ግን ህገወጥ የሆኑት ላይ ዕርምጃ እንደሚወስድም አሳስበዋል፡፡

Via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 23/2011 ዓ.ም.

ከትራንስፓርት ሚንስቴርና ከሌሎች ሚንስቴር መስሪያ ቤቶች የተወጣጣው የሉኡካን ቡድን የጅቡቲ ወደብን ጎብኝቷል።
.
.
ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በምዕራብ እንዲሁም ምሥራቅ ጉጂ በኢትዮጵያ መከላከያ ኃይልና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች መካከል በታካሄደ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን በርካቶች ከቤታቸው መፈናቀላቸው ተናግረዋል።
.
.
ከአመት በፊት ሳውዲ አረቢያ ጀምራው የነበረውን መጠነ ሰፊ የፀረ-ሙስና ዘመቻ እንዳጠናቀቀች አስታውቃለች፡፡ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት 100 ቢሊዮን ዶላር በጥሬ ገንዘብ እና በቁስ መልክ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሰዎች መሰብሰቡን አስታውቋል።
.
.
የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ የፀደቀውን #የስደተኞች_አዋጅ በመቃወም ነገ በጋምቤላ ከተማ ሊደረግ ለታሰበው የተቃውሞ ሰልፍ ፈቃድ #ከልክሏል
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ6 ሺህ ነጋዴዎች ግብር ሰርዣለሁ ብሏል፡፡ ግብር ስረዛው ከ2003 እስከ 2010 ዓ.ም ባለው ጊዜ ከፍተኛ የግብር ተመን ተጥሎባቸው አቤቱታ ሲያቀርቡ የቆዩትን ነጋዴዎች ያካትታል፡፡
.
.
4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ ከመጋቢት 29 ቀን ጀምሮ ይካሄዳል።
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህግን ተከትለው የሚሰሩ የሪል ስቴት አልሚዎችን እንደሚደግፍ ነገር ግን ህገወጥ የሆኑት ላይ #ዕርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
.
.
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ጃማ ወረዳ በጫነው አሸዋ ላይ 31 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የሰዎች ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።
.
.
በቴፒ ከተማ ከትንላንት ጀምሮ ዳግም #ያገረሸው #አለመረጋጋት ዛሬም ቀጥሏል። የንግድ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ተቋርጦ ውሏል። ከተማዋ በፀጥታ ሃይሎች በከፍተኛ ደረጃ እየተጠበቀች ነው።
.
.
ዛሬ በስራ ላይ የሚውለውን የነዳጅ ዋጋ መጨመር ተከትሎ ምንም አይነት #የትራንስፖርት_ታሪፍ  ጭማሪ #እንደማይኖር የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ገልጿል።
.
.
ጅቡቲ በተካሄደው 15ኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ የተካፈሉ የኢትዮጵያ ልዑካን ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያይተዋል።
.
.
በኦሮሚያ ክልል ለመንግስት ሰራተኞች #አዲስ የስራ ምደባ እየካሄደ መሆኑን የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።
.
.
#ኮማንድ_ፖስቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 3 ወረዳዎች ላይ በቁጥጥር ስር ካዋላቸዉ 528 ተጠርጣሪዎች 440 የሚሆኑትን በነፃ አሰናብቷል።
.
.
የአዋሽ ወልድያ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት የመጀመሪያው ምዕራፍ የሆነው ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ ያለው 270 ኪሎ ሜትር የባቡር መንገድ ግንባታ 97 በመቶ #መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ገልጿል።
.
.
በሱማሌ ክልል ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ ሰዓት ዕላፊ ገደብ ተጥሏል፡፡ የአደባባይ ስብሰባም ተከልክሏል፡፡
.
.
#ቴዎድሮስ_አዲሱ(ቴዲ ማንጁስ) በ80 ሺህ ብር ዋስ ቢፈቀድለትም #በሙስና_ወንጀል ተጠርጥሮ በእስር ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል።
.
.
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ለሚያልፉ ዐለም ዐቀፍ መንገደኞች #የነጻ ጉብኝት መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
.
.
የኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንስል፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ዘርፍ ማህበር እና #የሰላም_ሚኒስቴር በጋራ በመሆን የሰላም ሚዲያ ህብረት ትስሰር ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት ዛሬ ማምሻውን አካሂደዋል።
.
.
የሐረሪ ክልል የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ #መሻሻል ማሳየቱን የክልሉ ፍትህና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ  አስታውቋል።
.
.
#ብሄሬን መሰረት ተደርጎ ጥቃት ተፈፅሞብኛል በሚል በሀሰት የሽንት መሽኛ #ብልቱን በፋሻና ፕላስተር በመጠቅለል ግጭት ለመቀስቀስ የሞከረው ግለስብ ድሬ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ በዳቦ ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ አግባብነት የሌለውና ህብረተሰቡን ያላማከለ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
.
.
በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላውያን አንድ #ኢትዮጵያዊ በእስራኤል ፖሊስ መገደሉን በመቃወም ቴላቪቭ ውስጥ ትናንት የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል።
.
.
በአሜሪካ በተከሰተው ከፍተኛ ቅዝቃዜ እስካሁን ቢያንስ ስምንት ሰዎች #መሞታቸው ተገለጸ፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው በአሜሪካ ሜድ ዌስት የተከሰተው ቅዝቃዜ በአስር አመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ አደገኛ ነው፡፡
.
.
ምንጭ፦ etv፣ የጀርመን ራድዮ፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ ዋዜማ ራድዮ፣ fbc፣ ኢዜአ፣ bbc፣ VOA፣ የሰላም ሚኒስቴር፣ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia