TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ባህር ዳር⬆️

‹ለአንቺ ነው ኢትዮጵያ › በሚል ርዕስ አቀባበል እንደሚደረግ የአቀባበል ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ዳዊት ሞላ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የንቅናቄው ከፍተኛ አመራሮች ፕሮፌሰር #ብርሃኑ_ነጋ እና #አንዳርጋቸው_ፅጌን ጨምሮ ሌሎች የግንቦት ሰባት አባሎች አርብ ማታ ባሕር ዳር ይገባሉ፡፡

አርበኞቹ ለነፃነት ሲባል ላበረከቱት አስተዋፅኦ የክብር አቀባበል እንደሚደረግ ሰብሳቢው ተናግረው በአቀባበሉ ሥነ-ስርዓቱም "ለአርበኛ ታጋዮች ቅድሚያ ይሰጣል" ብለዋል፡፡

ቅዳሜ መስከረም 5/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የአቀባበል ሥነ-ስርአቱ ይካሄዳል፡፡ ከሰዓት በኋላ ደግሞ የውይይት መድረክ መዘጋጀቱን አቶ ዳዊት ገልጸዋል፡፡

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia