TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቱርክ

ቱርክ ካለፈው ማክሰኞ ሃምሌ 20 ቀን 2013 አንስቶ የተነሳውን ከፍተኛ የሆነ የደን ቃጠሎ ለመቆጣጠር እና ለመግታት ጥረት እያደረገች ነው።

እሳቱ ወደ በሃያ አንድ ከተሞች የተስፋፋ ሲሆን በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ጣታቸውን ወደ PKK ጠቁመዋል። እሳቱን ቀደም ብሎ በሽብርተኛው ድርጅት የታቀደ ሊሆን እንደሚችል እያነሱ ነው።

የPKK ተባባሪ ቡድን "Children of The Fire Initiative" ሰኔ 27 እና ሀምሌ 2 ባወጣቸው ደብዳቤዎች በዚህ ዓመት ብቻ ለተቀሰቀሱት 13 የእሳት አደጋዎች ኃላፊነት እንደሚወስድ ገልጾ ነበር።

PKK ቱርክ ውስጥ ከሚነሱ የደን ቃጠሎች ጋር በርካታ ሪከርዶች ያሉበት ሲሆን ቡድኑ ይህንን የሚያደርገው የቱርክን ግዛት "ለመበቀል" እንደሆነ ይነገራል።

የእሳት ቃጠሎ ሲቪሎችን የገደለ ሲሆን በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

በ2020 PKK በሀታይ ግዛት ውስጥ ለተቀሰቀሰውና 350,000 sq m ላቃጠለው እሳት ኃላፊነቱን ወስዶ ነበር። ከቃጠሎው በላይ 500 የሚደርሱ ሰዎች አካባቢያቸውን ለቀው ለመውጣትም ተገደዋል።

የቱርክ ባለስልጣናት ባለፉት ቀናት በደቡባዊ ክፍል የተቀሰቀሰውን እና በከፍተኛ ደረጃ የተስፋፋውን እሳት መነሻ ምክንያት ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

Video Credit : Solcu Gazete

@tikvahethiopia
#Sudan #Turkey

ጎረቤት ሀገር ሱዳን የኢትዮ- ሱዳን የድንበር ላይ ውዝግብን ለመፍታት #ቱርክ ያቀረበችውን የማደራደር ጥያቄ መቀበሏ ታውቋል።

የቱርክን የማደራደር ጥያቄ ሱዳን መቀበሏን ያሳወቁት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማሪያም አል-ሳዲቅ አል-መሃዲ ናቸው።

ይህንንም ጉዳይ የቱርክ የዜና ወኪል የሆነው አናዱሉ እና የሱዳን መንግሥት የዜና ወኪል ሱና ዘግበውታል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ፥ "የሱዳን የሉዓላዊ ም/ ቤት ሊቀ-መንበር አብዱል ፋታህ አል-ቡርሐን ባለፈው ወር ወደ ቱርክ በተጓዙ ወቅት ፤ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈጠረውን የድንበር አለመግባባት ለመፍታት ከቱርክ ባለሥልጣናት የቀረበውን የማደራደር ጥያቄ ተቀብለዋል" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በኩል በጉዳዩ ላይ እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤቱ ሊቀ-መንበር አብዱል ፋታህ አል-ቡርሐን አብዱል ራህማን ሰኔ ወር ላይ ወደ ቱርክ መጓዛቸው ይታወሳል። አል-ቡርሐን በአንካራ ቆይታቸው ከፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ጋር ተገናኝተው በርካታ ምጣኔ ሀብታዊ ስምምነቶችን ተፈራርመው ነበር።

በተመሳሳይ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር የኢትዮጵያው ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ቱርክ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር የተወያዩ ሲሆን፤ የተለያዩ የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነቶችን ላይ ስምምነት ተፈራርመው እንደነበር ይታወሳል።

Credit : BBC/SUNA/ANADOLU

@tikvahethiopia
#Turkey

" ...በኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋት የሚያመጣ ማንኛውንም መንገድ እየደገፍን ነው " - ያፕራክ አልፕ

ቱርክ በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት የሚያመጣ ማንኛውንም መንገድ እየደገፈች መሆኑን በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ ገልፀዋል።

አምባሳደሯ ይህን የገለፁት በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ግጭት በቀጠለበት በዚህ ወቅት ነው።

ቱርክ በቅርቡ የተጀመረውን ብሔራዊ የውይይት ሂደት በደስታ እንደምትቀበል አምባሳደር ያፕራክ አልፕ ተናግረዋል።

ሁለቱ ሀገራት [#ቱርክ እና #ኢትዮጵያ] በአስቸጋሪ ጊዜያት እርስበርስ መደጋገፋቸውን ያነሱት አምባሳደር ያፕራክ አልፕ ፥ " በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የሚደረጉትን ሁሉንም እርምጃዎች በደስታ እንቀበላለን። አሁን ይህ እየሆነ በመምጣቱ ደስተኛ ነን ፤ ለሁሉም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ግጭቱ በቅርቡ እንደሚቆም ተስፋ እናደርጋለን " ብለዋል።

ቱርክ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግ እና ወደ ንግግር እንዲገባ ለሁሉም ወገኖች ጥሪ ስታቀርብ እንደነበር የቱርክ መንግሥት ደጋፊ እንደሆነ የሚነገረው ዴይሊ ሳባህ ፅፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Turkey #Ethiopia የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ አካሂዶት በነበረው 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ከቱርክ ሪፐብሊክ ጋር የተደረጉ ወታደራዊ የትብብር ስምምነቶችን ላይ ውይይት አድርጓል። ምክር ቤቱ ፤ ቱርክና ኢትዮጵያ ዘመናትን የተሻገረ ጥብቅ ወዳጅነት ያላቸው መሆኑን በማስታወስ ቱርክ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን አጋር መሆኗን በተደጋጋሚ ያረጋገጠች አገር ናት ብሏል። በዚህ መነሻነት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ…
#Ethiopia #Turkey

የኢትዮጵያ ፓርላማ በ #ኢትዮጵያ እና #ቱርክ መካከል የተደረጉ ወታደራዊ ስምምነቶችን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

ፓርላማው ስምምነቱን ያፀደቀው ባካሄደው ሰባተኛ መደበኛ ስብሰባው ነው።

ኢትዮጵያ እና ቱርክ ወታደራዊ ትብብሮችን ለማድረግ የሚያስችላቸውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም በቱርክ አንካራ መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

ከስምምነቱ መካከል በጥቂቱ ፦

(የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት)

➡️ ዓላማ፦ በ2ቱ አገሮች መካከል በመከላከያ ዘርፍ የሚደረገው ግንኙነት የሚመራበትን ግልጽ ማዕቀፍ ለመፍጠር ነው።

➡️ የስምምነቱ ይዘት ፦ በሁለቱ ሀገራት በትምህርት እና ስልጠና በተናጠልና በጋራ በሚዘጋጁ ወታደራዊ ልምምዶች ስለመካፈል፣ በመከላከያ ኢንዱስትሪ፣ የመረጃ ልውውጥ፣ የሎጅስቲክ፣ የጤና አገልግሎት፣ የመረጃ ስርአት እና የሳይበር ጥቃትን መከላከልና በሌሎች ተያያዥ መስኮች ፣ ከመደበኛ ጦርነት ውጭ ባሉ የሰላም ማስከበር ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ድንጋጌዎችን ያካተተ ነው።

➡️ በኢትዮጵያ ላይ የሚጥለው ግዴታ ፦ ሚስጥራዊ መረጃዎች፣ ሰነዶች እና ማቴሪያሎች ፣ አእምሮአዊ ንብረቶችን አስፈላጊውን ጥበቃ የማድረግ ኢትዮጵያ ለትምህርት እና ስልጠና ወደ ቱርክ ለምትልካቸው የመከላከያ አባላት እና ተማሪዎች በተቀባይ ሀገር የማይሸፈኑትን የህክምና ወጪዎችን ፣ ሌሎችንም የትምህርት እና ስልጠና ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ ይጥላል።

➡️ ከዚህ ስምምነት ኢትዮጵያ የምታገኘው ጥቅም ፦ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ፣ የሎጅስቲክ አቅርቦቶችን እና ድጋፎችን ለማግኘት የሰራዊት ትጥቆችን እንዲሁም በሰው ኃይል እና አስተዳደር ዙሪያ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ፣ የትምህርትና ስልጠና እድሎችን ለማግኘት ያስችላል።

(የወታደራዊ ፋይናንስ ትብብር ስምምነት)

➡️ ዓላማው ፦ በሁለቱ ሀገራት መካከል በመከላከያ ዘርፍ የሚደረገው ግንኙነት የሚመራበት ግልፅ የህግ ማዕቀፍ በመፍጠር የቱርክ መንግስት 100 ሚሊዮን የቱርክ ሊሬ ተመጣጣኝ የሆነ የአሜሪካ ዶላር ለኢትዮጵያ መንግስት ፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ለመከላከያ ዓላማ የሚውል 100% በቱርክ ሀገር የተመረቱ የመከላከያ ቁሳቁሶችን እና አገልግሎቶችን መግዛት የሚችልበትን መርዕ ለመወሰን ነው።

➡️ የስምምነቱ ይዘት ፦ የቱርክ መንግስት 100 ሊሬ ተመጣጣኝ የአሜሪካ ዶላር ለኢትዮጵያ መንግስት ስለሚሰጥበት ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት በዋናነት በቱርክ ከሚገኙ ኩባንያዎች 100% በቱርክ የተመረቱ የመከላከያ ቁሳቁሶችንና አገልግሎቶችን መግዛት የሚችልበትን መርህ ይደነግጋል።

➡️ በኢትዮጵያ ላይ የሚጥለው ግዴታ ፦ በሁለቱ ሀገራት የመረጃ ልውውጥ የተገኙ እና ሚስጥራዊ ተብለው የተለዩ መረጃዎችን ከሌላኛው ወገን የፅሁፍ ፍቃድ ሳይገኝ ለሌላ ሶስተኛ ወገን ያለ መግለፅ እና ሚስጥራዊ መረጃዎችን መጠበቅ እንዲሁም ከቱርክ መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት የተላለፈ ሀብት ፣ እቃ ወይም አገልግሎት ያለ ቱርክ መንግስት የፅሁፍ ፍቃድ ለሌላ ሀገር ወይም ሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፍ ወይም ጥቅም ላይ እንዳይውል የማድረግ ግዴታን ይጥላል።

➡️ ከስምምነቱ ኢትዮጵያ የምታገኘው ጥቅም ፦ ኢትዮጵያ ከቱርክ መንግስት የምታገኘው 100 ሚሊዮን የቱርክ ሊሬ ተመጣጣኝ የአሜሪካ ዶላር ወታደራዊ ቁሳቁስ እና አገልግሎት ከቱርክ ድርጅቶች በመግዛት ለአስፈላጊ አገልግሎት ማዋል እንድትችል ያደርጋታል።

#Ethiopia_Turkey
#ኢትዮጵያ_ቱርክ #ወታደራዊ_ስምምነቶች

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ ፦

➡️ #አሜሪካ - በኒውዮርክ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። ሰልፉ በመሳሪያ የገዙ ጥቃቶችን ለማውገዝ የተካሄደ ነው። ሰልፉ የተካሄደው አንድ ወጣት በቴክሳስ ሮብ በሚሰኝ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 19 ህፃናት ተማሪዎችን እና 2 መምህራንን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለ ከቀናት በኃላ ነው።

➡️ #ስፔን - በሰሜናዊ ስፔን ላ ሪዮጃ ክልል በባዮዲዝል ማምረቻ ፋብሪካ ላይ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ 2 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

➡️ #የመን - በየመን አደን ከተማ ሰዎች በሚበዙበት በተጨናነቀ ገበያ ላይ በደረሰ ፍንዳታ በትንሹ 4 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸው ታውቋል፤ እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዳለሁ ብሎ ብቅ ያለ የለም።

➡️ #ሱዳን - ከወራት በፊት በሱዳን የተካሄደውም ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ አሁንም ያልበረደ ሲሆን ትላንትና በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በካርቱም ጎዳናዎች ላይ ተቃውሞ አሰምተዋል። የጥቅምቱ መፈንቅለ መንግስት ሀገሪቱን ወደ ፖለቲካዊ ቀውስ አስገብቷል።

➡️ #ጣልያን - የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ የሩሲያው ፕሬዜዳንህ ፑቲን አሁን ላይ በዓለም የሚየው የምግብ ችግር "በሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ነው " ብለው እንደነገራቸው ተናግረዋል። የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ከጀመረ አንስቶ ምዕራባውያን ሀገራት ሩስያ ላይ እጅግ ከፍተኛ የሚባሉ ማዕቀቦችን እየጣሉ እንደሆነ ይታወቃል። ለእነዚህ ማዕቀቦችም ሩስያ ምላሽ ከመስጠት ወደኃላ አላለችም።

➡️ #ቱርክ #ፈረንሳይ - የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ከፈረንሳይ ፕሬዜዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የስውዲን እና ፊንላንድ ለNATO አባልነት ባቀረቡት ማመልከቻ፣ በዩክሬን ሩስያ ጦርነት፣ በቀጠናዊ ጉዳዮች እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ተገናኝተው መክረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#ቱርክ #ሶሪያ

በቱርክ እና ሶሪያ ድንበር አቅራቢያ ባሉ ከተሞች በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች ከ4,800 በላይ መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል።

የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል እየተነገረ ነው።

የነፍስ አድን ሠራተኞችም በፍርስ ራሾች ውስጥ ተቀብረው የሚገኙ ሰዎችን ለማትረፍ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን በቱርክ የሰባት ቀናት ብሄራዊ የሀዘን ቀን አውጀዋል።

ፕሬዝዳንቱ የሀዘን አዋጁን ያወጁት በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎችን ለማሰብ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት የሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

የሟቾች ቁጥር ከ45 ሺህ አለፈ።

ባለፈው ሳምንት #ቱርክ እና #ሶሪያን በመታው የመሬት መንቀጥቀጥ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ45 ሺህ ማለፉን አልጀዚራ ዘግቧል።

ምንም እንኳን በአደጋው ሳቢያ መጠለያ አልባ የሆኑ ሰዎች ይፋዊ ቁጥር ባይገለፅም በርካቶች መጠለያ አልባ ሆነው በተለያዩ ቦታዎች ውሎ እና አዳራቸውን ለማድረግ ተገደዋል። ከመጠለያ ባለፈ መሰረታዊ ነገሮችን ለማሟላት ተቸግረው እንደሚገኙ ተነግሯል።

ተጎጂዎችን ለማገዝ ዓለም አቀፍ የሆነ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

በሌላ በኩል ፤ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ በጠፋው የሰው ሕይወት እና በወደመው ንብረት የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ለፕሬዚዳንት ሬሴፕ ታይፕ ኤርዶጋን በስልክ መግለጣቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አሳውቀዋል።

" ኢትዮጵያ የተቸገረ ወዳጇን ለመርዳት ምንጊዜም ቁርጠኛ ናት። " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ " ባላት ዐቅምም የቁሳቁስ እና የነፍስ አድን ቡድን ለቱርክ አበርክታለች " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Turkey ትላንት ምሽት ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ ተመታች። እጅግ አስከፊው የመሬት መንቀጥቀጥ (7.8) ከተከሰተ ከሁለት ሳምንት በኃላ ቱርክ ትላንት ምሽት በሬክተር ስኬል መለኪያ 6.3 በሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መመታቷ ተሰምቷል። የመሬት መንቀጥቀጡ የመታው አካባቢ ከሁለት ሳምንት በፊት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ከባድ ጉዳት ባጋጠመው በሃታይ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ደቡባዊዋ ሳማንዳግ ከተማ አቅራቢያ…
#ቱርክ

አንድ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ባለስልጣን በቱርክ ከሁለት ሳምንት በፊት በተከሰተው የመሬት መቀጥቀጥ 1.5 ሚሊዮን ሰዎች #ቤት_አልባ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪ እኚሁ ባለስልጣን ፤ ሀገሪቱ ውስጥ ወደ 500,000 የሚጠጉ ቤቶች እንደገና መገንባት አለባቸው ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከትላንት ወዲያ በድጋሚ ቱርክን በመታት የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 8 ስለመድረሱ የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

@tikvahethiopia
#ቱርክ

ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ቤት አልባ ለሆኑ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዘጎቿ ቤት መስራት መጀመሯ ተሰምቷል።

የሀገሪቱ መንግስት በደረሰው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ የወደሙ የመኖሪያ ቤቶችን መልሶ የመገንባት ስራ መጀመሩን ገልጿል።

በመሬት መንቀጥቀጡ 520 ሽህ አፓርትመንቶችን የያዙ ከ160 ሽህ በላይ ህንጻዎች ፈርሰዋል ወይም ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።

ፕሬዝዳንት ሬሲጵ ጣይብ ኤርዶጋን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ቤቶችን ለመገንባት ቃል ገብተዋል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ባለስልጣን ለሮይተርስ በሰጡት ቃል ፤ " ለበርካታ ፕሮጀክቶች ጨረታዎች እና ኮንትራቶች ተከናውነዋል። ሂደቱ በጣም በፍጥነት እየሄደ ነው " ብለዋል።

በደህንነት ላይ ምንም አይነት ድርድር አይኖርም ሲሉም ተናግረዋል።

የቱርክ መንግስት የመጀመሪያ እቅድ 200 ሽህ አፓርትመንቶች እና 70 ሽህ ቤቶችን ቢያንስ በ15 ቢሊየን ዶላር መገንባት ነው ተብሏል። 

የአሜሪካው ባንክ ጄፒ ሞርገን አንካራ ቤቶችን መልሶ ለመገንባትና ለመሰረተ ልማት 25 ቢሊዮን ዶላር እንደምታወጣ ገምቷል። 

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ / ሮይተርስ

@tikvahethiopia
#ቱርክ

ቱርካውያን የቀጣይ አምስት ዓመታት መሪያቸውን ለመምረጥ ዛሬ ድምፅ ሲሰጡ ዋሉ።

ዛሬ የቱርክ ፕሬዝዳንታዊና የፓርላማ አባላት ምርጫ እየተካሄደ ሲሆን የድምፅ አሰጣጡም ተጠናቆ ወደ ድምፅ ቆጠራ ተገብቷል።

በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ላይ ፕሬዝዳንት ሬስፕ ጣይብ ኤርዶሃን እና ዋነኛ ተቀናቃኛቸው ከማል ክሊችዳሮግሉ ብርቱ ተፎካካሪ ናቸው።

የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ዛሬ እሁድ ወደ በኃላ ይታወቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ይፋዊው ውጤት ለማረጋገጥ ግን እስከ ሶስት ቀናት ሊወስድ ይችላል ተብሏል።

አንድ ተወዳደሪ ለማሸነፍ በመጀመሪያ ዙር ከ50 በመቶ በላይ ድምጽ ያስፈልገዋል።

ተወዳዳሪዎች 50 በመቶውን ድምፅ ማለፍ ካልቻሉ ፤ ከሁለት ሳምንት በኋላ በሁለተኛ ዙር ምርጫ ይገናኛሉ።

እስካሁን ያለው ውጤት ምን ይመስላል ?

64.36 በመቶ የምርጫ ሳጥን ተከፍቶ የተቆጠረ ሲሆን ፤ ኤርዶጋን በ51.40 በመቶ እየመሩ ናቸው።

ተቀናቃኛቸው ክሊችዳሮግሉ 42.77 በመቶ ድምፅ አስመዝግበዋል።

ምንጭ፦ አናዱሉ

@tikvahethiopia